Get Mystery Box with random crypto!

በቻይና የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን የቱሪዝም ሃብቶች አስተዋወቁ ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) | AddisWalta - AW

በቻይና የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን የቱሪዝም ሃብቶች አስተዋወቁ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) በቻይና ጂሊን ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን የባሕልና የቱሪዝም ሐብቶች ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ማስተዋወቃቸው ተገለጸ።

ተማሪዎቹ የሀገራቸውን የባሕልና ቱሪዝም ሐብቶች ያስተዋወቁት በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባባር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ዝግጅታቸውን ያቀረቡት በዩኒቨርሲቲው ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በማስተዋወቂያ ዝግጅቱ ላይም የኢትዮጵያን ባሕላዊ ምግቦች፣ የቱሪዝም መስኅቦችና አጠቃላይ የኢትዮጵያን ታሪክ በተለያየ ዘዴ ማቅረብ ተችሏል፡፡