Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኢጋድ አባል ሀገራት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ ሰኔ 5/2015 | AddisWalta - AW

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኢጋድ አባል ሀገራት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በኢጋድ አባል ሀገራት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ14ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሰ ብሔራት እና መንግሥታት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ መግባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።