Get Mystery Box with random crypto!

በመከላከያ ሠራዊቱ የደረሰብን ምት መቋቋም አልቻልንም - ምርኮኞች ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) 'በ | Walta

በመከላከያ ሠራዊቱ የደረሰብን ምት መቋቋም አልቻልንም - ምርኮኞች

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) "በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የደረሰብን ምት ፈፅሞ የምንቋቋመው አልሆነም ሲሉ በሰቆጣ ግምባር እጃቸውን የሠጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ገለጹ፡፡

ምርኮኞቹ አያይዘውም ብዙዎች ከአጠገባችን ተደምስሰውብናል፣ አመራሮቻችንም ሞተዋል የተረፉትም ሸሽተዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

ጉዕዲ ገ/ኪዳን በሠቆጣ ግምባር እጃቸውን ለመከለከያ ሠራዊት ከሰጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች መካከል አንዷ ስትሆን አማራን መደምሰስ አለብን የሚል ተልዕኮ እንደተሰጣቸውም ተናግራለች።

በትግራይ ክልል ውስጥ ከፍተኛ አፈና እና የመብት ጥሰት በአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች እየተደረገ መሆኑን የገለጸችው ጉዕዲ ምንም እንኳን የጦርነት ፍላጎት ባይኖራትም በቤተሰቦቿ ላይ የሚደርሰውን ወከባ እና እንግልት ላለማየት አሸባሪውን ቡድን መቀላቀሏን ገልፃለች።

ሌላኛው ምርኮኛ ኤልያስ ገብረፃዲቅ የሦስት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሲሆን ከሚሰራበት ቦታ በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተገዶ ወደ ማሰልጠኛ እንደተወሰደ መናገሩን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!