Get Mystery Box with random crypto!

የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታ አበረከተ ጳጉሜ 1/2014 | Walta

የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታ አበረከተ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡

ስጦታው የተበረከተላቸው ጽህፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው 35 ልጆችና ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው 119 የፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ተፈሪ ፍቅሬ የበጎነት ቀንን በማስመልከት የተበረከተው ስጦታ ለአዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በጎነት ከአመለካከት የሚነሳ በመሆኑ ሁሉም ባህሉ ሊያደርገው እንደሚገባና ቀኑን ጠብቆ ሳይሆን የዘውትር ተግባራችን መሆን ይገባዋልም ብለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!