Get Mystery Box with random crypto!

ሚኒስቴሮቹ የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በጋራ እያከበሩ ነው ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የጤና፣ የትምህር | Walta

ሚኒስቴሮቹ የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በጋራ እያከበሩ ነው

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም የስራና ክህሎት ሚኒስቴሮች የበጎ ፈቃደኝነት ቀንን በጋራ እያከበሩ ነው፡፡

ሚኒስቴሮቹ በጋራ የሚያዘጋጁት የሙሉ ቀን መርኃ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል።

የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ በማድረግ እንደዚሁም የተተከሉ ችግኞችን በማረም፣ በመኮትኮት እና በመንከባከብ ነው መርኃ ግብሩ እየተካሄደ ያለው።

በመርኃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መርኃ ግብሩ ለ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ መገለፁን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!