Get Mystery Box with random crypto!

'እምባ ማበስና የኑሮ ጫና ማቃለል የመንግስታችን ቀዳሚ ኃላፊነት ነው' - ከንቲባ አዳነች አቤቤ አ | Walta

"እምባ ማበስና የኑሮ ጫና ማቃለል የመንግስታችን ቀዳሚ ኃላፊነት ነው" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቤቤ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦስት በመከላከያ ኮንስትራክሽን አማካኝነትና በሄይንከን ኢትዮጵያ የተገነቡ ቤቶችን መርቀው ለአቅመ ደካማ ወገኖች የቀልፍ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ከንቲባዋ በሰው ተኮር ዕቅዳችንን ማዕከል በማድረግ በ2014 ዓ.ም በአጠቃላይ ስምንት ሺሕ ቤቶችን ድጋፍ ለሚሹ አቅመ ደካማ ወገኖች አስረክበናል ብለዋል፡፡

ባለፉት ጊዚያት በዓመት የነበረው ከፍተኛ ቤት የመገንባት አሃዝ ሶስት ሺሕ ነበር ያሉት ከንቲባ አዳነች ከበጎ ፈቃደኞችና ከአገር ወዳድ አካላት ጋር ከተቀናጀን ብዙ መሥራት እንደምንችል የተማርንበትም ምዕራፍ ነው ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 952 ቤቶችን ከበጎ ፈቃደኛች ጋር በቅንጅት ግንባታቸውን አጠናቀን ሙሉ በሙሉ ርክክብ እንፈጽማለን ብለው ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ዜጎች በሚፈለገው ልክ ከደገፉን ብዙ በመሥራት በጉብዝናቸው ወራት ለሀገር እጅግ የደከሙ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን መደገፍ እንችላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::

እምባ ማበስና የኑሮ ጫና ማቃለል የመንግስታችን ቀዳሚ ኃላፊነት ነው ያሉት ከንቲባዋ በዘላቂነት ተመሣሣይ ችግር ያለባቸውን ወገኖች ለመርዳት ከተማ አስተዳደሩ ከበጎ ፈቃደኞችን ጋር ይሰራል ማለታቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

የበለጠ እያሰፋን እንድንሰራ የእስካሁኑ የአቅመ ደካማ ወጎኖች ቤት ግንባታ ምሳሌ ሆኖናል ያሉት ከንቲባዋ የምናርፈው በሁሉም ረገድ ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ስናረጋግጥ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth