Get Mystery Box with random crypto!

ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከማዋል በላይ ሀገርን የመው | Walta

ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከማዋል በላይ ሀገርን የመውደድ መገለጫ የለም - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከማዋል በላይ ሀገርን የመውደድ መገለጫ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ ከተከተልናቸው መርሖች አንዱ በማኅበራዊ ኃላፊነት ማኅበራዊ ችግሮችን መፍታት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማዕድ ማጋራት፣ የድኾችን ቤት መሥራት፣ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን መገንባት፣ የችግረኛ ገበሬዎችን እርሻ ማረስ፣ አካባቢን አረንጓዴ ማድረግ ባህል እንዲሆኑ ሠርተናል ብለዋል።

ሚልዮኖችም የዚህ ተሳታፊ ሆነዋል፤ ከሕጻናት እስከ አረጋዊያን ባህላቸው አድርገውታል ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ዓመት በተደረጉት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፋችሁትን ሁሉ በራሴና በመንግሥት ስም አመሰግናችኋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገልግሎቱን ያገኙት ወገኖች እንደሚመርቁንና እንደሚጸልዩልን አምናለሁም ብለዋል።

ኢትዮጵያችን በእነዚህ ወገኖች ምርቃትና ጸሎት ፈተናዎቿን አሸንፋ እንደምትጓዝ እርግጠኛ ነኝ ሲሉም አመልክተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!