Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሓት በጦርነት ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው ህጻናት፣ አረጋዊያንና ሴቶች ላይ አሰቃቂ | Walta

አሸባሪው ህወሓት በጦርነት ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው ህጻናት፣ አረጋዊያንና ሴቶች ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽሟል - ተጎጂዎች

አሸባሪው ህወሓት በጦርነት ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው ህጻናት፣ አረጋዊያንና ሴቶች ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽሟል ሲሉ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በቡድኑ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ተጎጂዎች ገለጹ።

ቡድኑ በለኮሰው ጦርነት የመከላከል አቅም የሌላቸውን ንጹሃንን የማይምር አረመኔ እንደሆነም አመልክተው ድርጊቱን በመገንዘብ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዘው እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቡድኑ ጥቃት ሰለባዎች እንዳሉት የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በከፈቱት ጦርነት አስከፊ ጉዳት አድርሰዋል።

ታጣቂዎቹ በከባድ መሳሪያ ታግዘው በንጹሃን ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱም ተናግረው በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ህጻናትና አረጋውያን እንዳሉ ተናግረዋል።

ከአንድ ቤተሰብ ሰባት ሰዎች እንደተገደሉና በሬ፣ ላምና በጎችም በጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን እንዳስተዋሉም ገልጸዋል።

ንጹሐንን ከመጨፍጨፍ ወደኋላ የማይለልውን አሸባሪ ቡድን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊዋጋው እንደሚገባ አስገንዝበው ''የህወሓት የሽብር ቡድን ለንፁሃን ዜጎች ግድ የሌለውና ሃላፊነት የማይሰማው ነው” ብለዋል።

የብሄረሰብ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ከፍያለው ደባሽ ቡድኑ በከፈተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ንፁሃን ዜጎች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ ለንፁሃን ዜጎች የማያስብ እንደሆነ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው ጥቃት በቂ ማሳያ ነው ብለዋል።

ቡድኑ በተፈናቃይ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች በሚገኙ ወገኖች ላይም አረመኔያዊ ተግባር ፈፅሟል ብለዋል።
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth