Get Mystery Box with random crypto!

የመውጫ ፈተና ለግልና ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጋራ መመዘኛ መሆኑ ተገለጸ | Walta

የመውጫ ፈተና ለግልና ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጋራ መመዘኛ መሆኑ ተገለጸ

ነሐሴ 30/2014 (ዋልታ) የመውጫ ፈተና ለግልና ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጋራ መመዘኛ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የመውጫ ፈተናን ውጤት መሰረት በማድረግ የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እርስ በርሳቸው እንደሚወዳደሩ ሚኒስትር ደኤታው አመልክተዋል፡፡

በመሆኑም ጥሩ ውጤት ሊገኝ የሚችለው ጥሩ ሂደት ሲኖር በመሆኑ ተቋማቱ ተማሪዎች ለውጤት እንዲበቁ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደሩ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻዎች እንደሚሳተፉበትና በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በማእከል እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ለምረቃ መብቃትና የትምህርት ማስረጃዎቻቸውንም መውሰድ የሚችሉት የመውጫ ፈተናውን ካለፉ በኋለ መሆኑን ጠቁመው በፈተናው ያላለፉ ተማሪዎችም ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ደግመው መፈተን የሚችሉበት አሰራር እንደሚኖር  አስታውቀዋል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለሚያደርጉት ዝግጅትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!