Get Mystery Box with random crypto!

፬ኛ. የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ ክርስትና በሰማያዊ ተስፋ የተሞላ ብርሃናማ ሕይወት ነዉ | ዋልድባ ገዳም

፬ኛ. የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ
ክርስትና በሰማያዊ ተስፋ የተሞላ ብርሃናማ ሕይወት ነዉና ይህን ተስፋችንን በማሰብ ነጭ ነጠላን እንለብሳን።
☞ @negeretewahido

✞☞ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን በማሰብ ነጠላችንን በትእምርተ መስቀል አጣፍተን መልበስ መንፈሳዊ ትርጉም አለውና እንዲሁ በዘፈቀደ የሚለበስ አለመሆኑን በመገንዘብ ሥርዓቱን ልንተገብር ይገባል። የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ እያሰብን በጸሎተ ኪዳኑም፣ በሥርዓተ ቅዳሴውና በበዓለ ንግሡም ላይ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠብቀን ነጠላ ለብሰን በቤቱ ብንገኝ መልካም ነው። «አባቶች የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ» /ምሳሌ ፳፪፥ ፳፰/ ሁላችንም ሥርዓተ ቤተክርስትያንን እንድንጠብቅ ልቦና ይስጠን።

✞☞ እግዚአብሔር ሁላችንንም እንደ ፍላጎታችን ሳይሆን እንደ እርሱ ፈቃድ እንድንመራ ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን! ይህ እራስን መግዛት ለቃሉ አለመታዘዝ ብዙዎቻችን ጋር ያለ ችግር ነው ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ሳይኖር የዓለምን ፍቅር አብልጠን ምን ችግር አለው? እያልን በእግር ብቻ በቤቱ መመላለስ ስለለመድን ነው። ትልቁ ችግር ያመጣው ምን ችግር አለው? ነው። ለዚህም ማሳያ እንደ ፕሮቴስታንት ተሃድሶ መና*ፍ*ቃን እምነት ያለ ዶግማና ቀኖና በራሳችን አስተያየት የምንጓዝ ቢሆን ብዙ ድርጅት በሆንን ነበር።

✞☞ እንደ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለመመላለስ የሚቸግረን ትክክል ያልሆነውን የዓለም ስርዓት ስለተለማመድን እንጅ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንማ በተገቢው ሥርዓት ኖረን ሰማያዊ ክብር የምናገኝበትና አንድ ሀሳብ አንድ ዓላማ የሚያረገንን ዶግማና ቀኖና ሰርታልናለች። ከመምህረ ንሰሃችን (ንስሃ አባታችን) ጋር በመመካከር፤ በግልና በማህበራዊ ጸሎቶች በመትጋት፤ አንዱ ለሌላው በመጸለይ፤ ሁልጊዜ ቅዱሳት መጽሐፍትን በመመርመር ሊያዘናጉን ከሚችሉ ሁኔታዎች በመራቅ ለእግዚአብሔር ሕግ መገዛት እንችላለን። ትእዛዙን ፈጽመን ለመኖር የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን!!!

አንድ እህታችን በውስጥ መስመር «ነጭ ነጠላ ለምን እንለብሳለን? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለውን?» ብላ ለጠየቀቺው ጥያቄ መልስ ለመስጠት እንጅ በሥርዓተ አበው መሠረት በአግባቡ ኖረን መንፈሳዊ ዋጋ ለማግኘት መጀመሪያ ሥጋንና ነፍስን ማንጻት ከዚያም ለፍጻሜ የምታበቃ ልብን ማንጻት እንዲገባ አረጋዊ መንፈሳዊ ይገልጣል። ጌታችን በወንጌል፦ “ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።” እንዳለ። ማቴ ፭፥ ፰

ቅዱስ ጳውሎስም አንድ በጎ ክርስቲያን በቀና እምነት የጸና የልብና የሕሊናን መንፈሳዊ ዝግጅት ከምግባራዊ ፍቅረ ቢጽ ጋር አስተባብሮ ከያዘ ትእዛዛትን ሁሉ መፈጸሙን በምሥጢር ገልጧል።
“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤” ፩ኛ ጢሞ ፩፥ ፭

በተጨማሪም የመንፈስ ልጁን ጢሞቴዎስን ሲመክር እንዲህ ብሏል፦
“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።” ፪ኛ ጢሞ ፪፥ ፳፪

ጻድቁ ኢዮብም የተወለደበት ቀን እስኪረግም ድረስ መከራው በላይ በላዩ ተደራርቦበት በተጨነቀ ጊዜ ቴማናዊው ኤልፋዝ እንዲህ ብሎ ነበር፦
“አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥
የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን? እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከልበ ቅንስ የተደመሰሰ ማን ነው?” ኢዮብ ፬፥ ፮- ፯

ስለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊትም፦ “አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።” ብሎ የዘመረው። መዝ ፶፥ ፲
ልበ ንጹሓን ሆነን በቅድመ እግዚአብሔር እንድንቆም አምላከ አበው ይርዳን። አሜን!

❖☞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✥☞ ወለወላዲቱ ድንግል
✞☞ ወለመስቀሉ ክቡር!
☞ @negeretewahido

✞❖✞ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን፣ መንፈሳዊ ጦማሮቻችንንና የመንፈሳዊ ጉዞዎቻችንን መርሐ ግብራት በሚከተሉት ሊንኮች ከፍተው ይከታተሉን፦

በቴሌግራም
☞ @waldiba እና
☞ @negeretewahido

በቲክቶክ
tiktok.com/@betewali

❖ በዩቲዩብ የሚከተለውን የ«መኮሬታ Mekoreta Tube» ማስፈንጠሪያ ተጪነው በመክፈት Subscribe & Join ያድርጉ።
☞ https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ