Get Mystery Box with random crypto!

#ደብረ_ስብሐት_አቡነ_ኢዮስያስ_ገዳም ★ Forward & Pin በማድረግ ገዳሙን እናስተዋውቅ ☞ @ | ዋልድባ ገዳም

#ደብረ_ስብሐት_አቡነ_ኢዮስያስ_ገዳም
★ Forward & Pin በማድረግ ገዳሙን እናስተዋውቅ
☞ @negeretewahido

★ ገዳሙ በዓድዋ አውራጃ ራህያ አካባቢ ይገኛል። ይህንን በታላቅ ቃልኪዳን የከበረ ገዳም የመሠረቱት ጻድቁ አባታችን መናኔ መንግሥት አቡነ ኢዮስያስ ሲሆኑ ጻድቁ የሸዋው ንጉሥ የአጼ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጻድቁ በልደታቸው ዕለት ጥር 6 ቀን ከእናታቸው ማሕፀን ሲወጡ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡

★ ጻድቁ መናኔ መንግሥት ተብለው ይጠራሉ፤ ምክንያቱም የንጉሥ ልጅ ሆነው ሳለ በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በምናኔ ሕይወት በብሕትውና ኖረዋልና። በዚህ የምናኔ ሕይወታቸውም በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ በሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና በደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳማት ገብተው ለብዙ ዘመናት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኮሳትን እና መጽሐፈ ሊቃውንትን ከሥርዓተ ገዳምና በቅድስና ከተሞላ የብሕትውና ሕይወት ጋር ተምረዋል።

★ ጻድቁ በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ለብዙ ጊዜ በአርድእትነት አገልግለው ሥርዓተ ምንኩስና ከተፈጸመላቸው በኋላ ወደ ትግራይ ደብረ በንኮል አቡነ አድኃኒ (መድኃኒነ እግዚእ) ገዳም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሄዱ፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ ጻድቅ በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ አስኬማ መላእክት ተፈጸመላቸው፡፡

★ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩኣቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና የራሳቸውን ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ታቦተ ማርያምን ይዘው ወደ ዓድዋ አውራጃ በመምጣት አሁን ክቡር ዐጽማቸው ያለበትን ቦታ በመገደም በርካታ መናኒያንን አፍርተውበታል።

★ ጻድቁ ታቦተ እግዝእትነ ማርያምን ይዘው መጥተው ስለገደሙት ቦታው ማርያም ስረዊቶ ይባል ነበር። በኋላ ደግሞ የጻድቁ ተከታዮች መናኒያን ከመብዛታቸው የተነሳ ማኅበረ ማርያም ተብሎ ይጠራ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን "ደብረ ስብሐት አቡነ ኢዮስያስ ገዳም" ተብሎ ተሰይሟል።

★ በገዳሙ ላይ ከተራራው ወረድ ብሎ ጻድቁ ያፈለቁት ፈዋሽ ጠበል አለ። በተጨማሪም የጻድቁ የእጅ መስቀል በገዳሙ ውስጥ ይገኛል፤ ገዳሙን ለመሳለም የሚመጣ ኦርቶዶክሳዊ እንግዳ ይህንን መስቀላቸውን ተሳልሞና በመስቀሉ ታሽቶ ልቡ በሃሴት ተሞልቶ መሻቱ ተፈፅሞለት ይመለሳል።

★ ጻድቁ እንደ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ አንበሳ በረዲእነት የሚያገለግላቸው እጅግ ተአምረኛ አባት ናቸው። በቅዱስ ገድላቸው ላይ ከተጻፈው በርካታ ተአምራቸው ውስጥ ጎላ ባለ መልኩ በስእለ አድኅኗቸው ላይ የተሳለው እንዲህ ነው።

ከደብረ በንኮል ተነስተው አክሱም ጽዮንን እጅ ነስተው ቃልኪዳን ወደተቀበሉበት ወደዚህ ገዳም ሲመጡ በመንገድ ላይ አራት ሰዎች ያለአግባብ ሞተው ቢያገኙ በጸሎታቸው አስነስተዋቸዋል።

በአንድ ወቅት አላዊያን ሠራዊት (ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን) የጻድቁን ገዳም ለማጥፋት ጦር ሰራዊት አስከትለው ጋሻ ታጥቀው ጦር ሰብቀው መጥተው ቢያስቸግሯቸው ጻድቁ በጸሎታቸው አምላከ አበው ቅዱስ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም በዚህ ጊዜ ጸዓዳ ነጭ የሆነ የንብ መንጋ ላከላቸው። ንቦቹም የአመጣጣቸው ነገር ተአምረኛና በሚገርም ፍጥነት ሲሆን የጻድቁን ጠላት የአረማውያን ሠራዊትን አንድ በአንድ እየነደፉ በመግደል መሉ በሙሉ አጥፍተውላቸዋል፡፡

በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡

★ ጻድቁ በዓለ ዕረፍታቸው ነሐሴ 6 ቀን ሲሆን በዕረፍታቸው ጊዜ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዕረፍታቸው ማግስት (ማለትም ከነሐሴ 5 እስከ 7 ድረስ) ለ3 ቀናት ለረጅም ጊዜ ቆመው ይጸልዩበት በነበረውና ኋላም ባረፉበት ሶሀባ ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ዘንቦላቸዋል፡፡

★ ወደ ታላቁ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 30 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ይህንን ቃልኪዳናቸውን አስቦ ልጁን በስማቸው ለሰየመ መልአከ ሞትን ፈጽሞ እንደማያይ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡ በተጨማሪም ከመቃብራቸው ታፍሶ ለምዕመናን የሚሰጠው እምነት ከማንኛውም አደጋ ሁሉ ይጠብቃል። የጻድቁ አባታችን የአቡነ ኢዮስያስ በረከት ረድኤታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን። አሜን!!!
☞ @negeretewahido

★ የገዳሙ አድራሻ፦
ከዓዲዋ ከተማ ወደ ዕደጋ ዓረቢ ወርዒለኸ ከተማ እና ነበለት ከተማ በሚወስደው መንገድ ራህያ ከምትባለው አነስተኛ ከተማ ላይ በተተከለው የገዳሙ ታፔላ በኩል ወደ ግራ ታጥፈው እስከ 10 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ከተጓዙ በኋላ ለጎምት ግድብን እንዳለፉ በእግር ከ35 ደቂቃ አይበልጥም።

★ በአክሱም ጽዮን ማርያም ንግሥ የ21 ቀናት ልዩ የዙር ጉዞ ከተሳለምናቸው በቃልኪዳን የከበሩ አስደናቂ ገዳማት መካከል አንዱ ነው። በመንፈሳዊ ጉዞዎቻችን ለመሳተፍ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ይደውሉ፦
☞ 0901070707 / 0911289877
☞ @negeretewahido

❖ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

በቴሌግራም ይቀላቀሉን
☞ @waldiba
☞ @waldiba
☞ @waldiba

በቲክቶክ ይከታተሉን
☞ tiktok.com/@betewali

❖ የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
☞ https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ