Get Mystery Box with random crypto!

በገዳም በበረሓ ያሉት አበውም ምስጋናዋን በማድረስ ፍጹም በረከቷን ሽተው በፊቷ ይማለላሉ፤ ርሷም ለ | ዋልድባ ገዳም

በገዳም በበረሓ ያሉት አበውም ምስጋናዋን በማድረስ ፍጹም በረከቷን ሽተው በፊቷ ይማለላሉ፤ ርሷም ለሱባኤዋ በወደቁበት በረሐ እየተገለጸች በረከቷን ታድላቸዋለች፤ ክቡራን ምእመናንም ከልጅ እስከ ዐዋቂ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሰብሰብ ቅዳሴ ማርያምን በማስቀደስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በመቀበል፤ እጅግ ድንቅ በኾነ መልኩ ሱባኤውን ይፈጽሙታል፤ በመኾኑም ትውልድ ኹሉ ብፅዕት የሚላት አጋንንትን የምታሸብራቸው የአምላካችን እናትም በቀንም ኾነ በሌሊት ከእኛ በረድኤት ባለመለየት ረድኤቷን በረከቷን ልታትረፈርፍልን የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ ደርሷልና በእጅጉ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ!!!፡፡

የምእመናን ወዳጅ የመስቀል ሥር ሥጦታችን በዚኽ የፍልሰታ ሱባኤ ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን!!! መልካም የበረከት ሱባኤ!!!