Get Mystery Box with random crypto!

ኢንጂል ክፍል አንድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 57፥2 | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ኢንጂል

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሣንም አስከተልን፥ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ

ኢየሱስ ከአምላኩ ግልጠተ መለኮት በተቀበለበት በዐረማይስጥ ቋንቋ "ኢዋንገሊዎን" ܐܘܢܓܠܝܘܢ ማለት "ብሥራት" "የምስራች" "መልካም ዜና" ማለት ሲሆን "ኢዋንገሊዎን" ܐܘܢܓܠܝܘܢ ወደ ዐረቢኛ ሙዐረብ ሆኖ ሲገባ "ኢንጂል" إِنْجِيل ሲባል፣ ወደ ግሪክ ሲገባ "ዩአንጌሎስ" εὐάγγελος ሲባል፣ ወደ ግዕዝ ሲገባ ደግሞ "ወንጌል" ተባለ። አምላካችን አሏህ ለዒሣ ኢንጂልን በመስጠት መልእክተኛ አርጎ ልኮታል፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሣንም አስከተልን፥ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ

በባይብልም ቢሆን ኢየሱስ ከላከው ከአምላክ መልእክት እየሰማ የሚያስተላለፍ መልእክተኛ ነበር፦
ዮሐንስ 8፥26 የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ "የሰማሁትን" ይህን ለዓለም እናገራለሁ።
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ "የሰማሁትን" እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። νῦν δὲ ζητεῖτέ με ἀποκτεῖναι, ἄνθρωπον ὃς τὴν ἀλήθειαν ὑμῖν λελάληκα, ἣν ἤκουσα παρὰ τοῦ Θεοῦ·

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" አሰሚ ባለቤት ሲሆን "ሰው" ሰሚ ተሳቢ ነው፥ በአምላክ እና በሰው መካከል "የሰማሁት" የሚል አጫፋሪ ግሥ"transitive verb" አለ። መልእክተኛው ኢየሱስ የሚናገረው የላከው እንደነገረው እንጂ ከራሱ ምንም አልተናገረም፦
ዮሐንስ 12፥50 ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን "የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ"።

"ትእዛዝ ሰጠኝ" የሚለው ይሰመርበት! ይህቺም ትእዛዝ ታላቂቱ እና ፊተኛይቱ ትእዛዝ "ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" የምትል ተውሒድ ስትሆን የዘላለም ሕይወት ናት፦
ዮሐንስ 12፥50 "ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች" አውቃለሁ።
ማቴዎስ 22፥38 ታላቂቱ እና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ "እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው"..የምትል ናት።

ጥንትም በቅዱሳን ነቢያት ቀድሞ የተባለውን ቃል እና በሐዋርያትም ከኢየሱስ የተገኘው ትእዛዝ "ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" የሚል ጭብጥ ነው፦
2 ጴጥሮስ 3፥2 በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል እና በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታን እና የመድኃኒትን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።

ኢየሱስ "የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ" ሲል ይህንን የአምላክ ትእዛዝ ከአምላክ ተቀብሎ ለሐዋርያት የሰጠው ቃል የአምላክ ቃል ነው፦
ዮሐንስ 17፥8 "የሰጠኸኝን ቃል" ሰጥቻቸዋለሁና።
ዮሐንስ 17፥14 እኔ "ቃልህን" ሰጥቻቸዋለሁ።

ኢየሱስ ወደ አምላኩ ሲጸልይ በሁለተኛ መደብ "ቃልህን" ማለቱ በራሱ የተሰጠው "ቃል" የአምላክ ቃል ነው፥ ሕዝቡም ሲሰማ የነበረው ቃል የላከው የአምላክ ቃል እንጂ የመልእክተኛው የራሱ ቃል አይደለም፦
ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም"።
ዮሐንስ 14፥24 "የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም"።
ሉቃስ 5፥1 ሕዝቡም "የአምላክን ቃል" እየሰሙ ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር።
ዮሐንስ 8፥47 ከአምላክ የሆነ "የአምላክን ቃል" ይሰማል።
ዮሐንስ 3፥34 አምላክ የላከው የአምላክንን ቃል ይናገራልና።

ኢየሱስ መልእክተኛ ነቢይ ሆኖ ከአምላኩ የተሰጠውን የአምላክን ቃል ይናገር ከነበረ እና ከራሱ ምንም ካልተናገረ ኢየሱስ ሙሉ ዕውቀት የለውም፥ ምክንያቱም ከአምላኩ የሚሰማው እርሱ ጋር ከሌለ እና ከአምላኩ ሰምቶ ከተናገረ ከላከው ዕውቀት ጋር እኩል ዕውቀት አይሆንም። እንግዲህ ኢየሱስ ከአምላኩ እየሰማ የተሰጠው የአምላክ ቃል ወንጌል ይባላል፥ ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለዚህ ወንጌል እናያለን........

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም