Get Mystery Box with random crypto!

የመለኮት ሙላት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥59 እርሱ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የመለኮት ሙላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥59 እርሱ በእርሱ ላይ የለገስንለት እና ለእስራኤል ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ነገርን መጠምዘዝ የሚቀናቸው ሚሽነሪዎች ያልተፈለገ መባልን ሲሉና "አሃ! እንዲህ ለማለት እኮ ነው!" እያሉ መለኮት በትስብእት እንደተገለጠ አርገው ከሚጠቅሷቸው ቅሰራዊ እና ቅየጣዊ ጥቅሶች መካከል ቆላይስይስ 2፥9 ነው። ባይብል ላይ ኢየሱስ መሢሕ፣ ነቢይ፣ መልእክተኛ መሆኑት በክብር ተቀምጦ ሳለ መለኮትን ለማላበስ በመሞከር የአህያ ሥጋ አልጋ ሲሉት ዐመድ ነገር ሆነዋል። ቆላይስይስ 2፥9 ላይ ያለውን ዐውድ "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" የሚለውን አገርኛ ብሒል ይዘን እንሞግት!
"ሶማ" σῶμα ማለት "አካል" ማለት ሲሆን በጳውሎስ ትምህርት ውስጥ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ስለሆነች "ሶማ" σῶμα ተብላለች፦
ቆላስይስ 1፥18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። καὶ αὐτός ἐστιν ἡ κεφαλὴ τοῦ σώματος, τῆς ἐκκλησίας·

እነዚ አንቀጽ ላይ "ቤተ ክርስቲያን" ለሚለው የገባው ቃል "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία ሲሆን ትርጉሙ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብስብ" ማለት ነው፥ የምእመናን ስብስብ "ኤክሌሲያ" ይባላል። የመለኮት ሙላት ሁሉ በክርስቶስ በኤክሌሲያ ተገልጦ ይኖራል፦
ቆላስይስ 2፥9 "በ-"እርሱ" የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል ይኖራልና። ὅτι ἐν αὐτῷ κατοικεῖ πᾶν τὸ πλήρωμα τῆς Θεότητος σωματικῶς,

"በ-"እርሱ" የሚለው ይሰመርበት! "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም "ክርስቶስ" የሚለውን የሚተካ ነው፥ አብ ሙላቱን ሁሉ በክርስቶስ በኩል እንዲኖር ፈቅዷልና፦
ቆላስይስ 1፥19 ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር ፈቅዷልና። ὅτι ἐν αὐτῷ εὐδόκησεν πᾶν τὸ πλήρωμα κατοικῆσαι

ዐማርኛ ላይ "እግዚአብሔር" ወይም ኪንግጀምስ ቨርዢን ላይ "አብ" ብለው ያስቀመጡት በውስጠ ታዋቂነት አብን ወይም እግዚአብሔርን ስለሚያመለክት ነው፥ አብ መለኮት ሲሆን ሙላቱን በክርስቶስ በኩል ለቤተክርስቲያን ይገልጣል። በቆላስይ 2፥9 ላይ "አካል" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሶማቲኮስ" σωματικῶς ሲሆን በጳውሎስ ትምህርት ውስጥ "አንድ አካል አለ" ብሎ የሚናገርላት ቤተክርስቲያን ናት፦ ቆላስይስ 1፥24 ኤፌሶን 4፥4 ሮሜ 12፥4-5 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥12 ቆላስይስ 3፥15 ተመልከት!

"መለኮት" የተባለው አብ ሲሆን ሙላቱ ደግሞ ሰዎች የሚሞሉት ጸጋ ነው፥ እዛው ዐውድ ላይ በክርስቶስ በኩል አማኞች ይህንን ሙላት እንደሚሞሉ ይናገራል፦
ቆላስይስ 2፥10 ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ "ተሞልታችኋል"። καὶ ἐστὲ ἐν αὐτῷ πεπληρωμένοι, ὅς ἐστιν ἡ κεφαλὴ πάσης ἀρχῆς καὶ ἐξουσίας,

"ተሞልታችኋል" የሚለው ይሰመርበት! "የመለኮት ሙላት" ማለት እና "መለኮት" ማለት ይለያያል፥ መለኮት አብ ሲሆን ሙላቱ ጸጋው ነው። ይህንን ስታውቁ ሙግቱ እግረ ሰረሰር እንደሚሆንባችሁ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ቢመራችሁም ዋጡት። መለኮትን ሰው አይሞላም፥ ነገር ግን ጸጋውን ይሞላሉ፦
ኤፌሶን 3፥19 እስከ አምላክም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ነው። ἵνα πληρωθῆτε εἰς πᾶν τὸ πλήρωμα τοῦ θεοῦ.

ጋንጩር እንዳለበት ክልው ክልው የሚያደርጋቸው ሚሽነሪዎች ነገርን አቅሎ ማርገብ እና አጃምሎ ማራገብ ስለሚወዱ እንጂ እዚህ አንቀጽ ላይ አማኞች የአምላክ ፍጹም ሙላት እንደሚሞሉ በግልጽ ይናገራል። በክርስቶስ በኩል የአብን ሙላት የሚሞሉት ሰዎች ከሆኑ የመለኮት ሙላት በክርስቶስ በኩል የሚኖረው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፥ ስለዚህ ቆላስይስ 2፥9 "መለኮት በትስብእት ተገለጠ" ለሚል የክርስትና ተሠግዎት"Incarnation" ትምህርት ማስረጃም መረጃም መሆን አይችልም። እኛ ሙሥሊሞች አይሁዳውያን የሚጠብቁት መሢሕ ኢየሱስ ነው ብለን እናምናለን፥ ኢየሱስ አሏህ መጽሐፍ እና ነቢይነት የለገሰው ባሪያ እና ያለ አባት በመወለድ ለእስራኤልም ልጆች ተአምር የተደረገ ባሪያ ነው፦
43፥59 እርሱ በእርሱ ላይ የለገስንለት እና ለእስራኤል ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ለኢየሱስ ነቢይነትን እና መጽሐፍን የሰጠውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም