Get Mystery Box with random crypto!

፨ሲቀጥል 'ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

፨ሲቀጥል "ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር" በሚል አንቀጽ ውስጥ "ሲቀር" "በቀር" ለሚለው የገባው ቃል "ኢላ" إِلَّا ሲሆን ኢሥቲስናእ ነው። "ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء‏ የሚለው ቃል "ኢሥተስና"  اِسْتَثْنَى ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "በስተቀረት"exception" ማለት ነው፥ ኢሥቲስናእ በሁለት ይከፈላል። አንዱ "ኢሥቲስናኡል ሙተሲል" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُتَّصِل ሲሆን "ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት "የተያያዘ"attached" ማለት ነው፦
43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢላ" إِلَّا የሚለው ኢሥቲስናኡል ሙተሲል ስለሆነ ተመሳሳይ ጥንተ ተፈጥሮን ያሳያል፥ ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት የሚሆነው እና አሏህን ፈሪዎች ጥንተ ተፈጥሯቸው ተመሳሳይ ነው። ተጨማሪ ይህንን ጥቅስ መመልከት ይቻላል፦
103፥2 ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡ إِنَّ الْإِنسَانَ لَفِي خُسْرٍ
103፥3 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ

ሁለተኛው ደግሞ "ኢሥቲስናኡል ሙንቀጢዕ" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُنقَطِع ሲሆን "ሙንቀጢዕ" مُنقَطِع ማለት "ያልተያያዘ"detached" ማለት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፥ ግን የዓለማት ጌታ "ሲቀር"»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም "እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው" ያላቸው እና "ሲቀር" ያለው "የዓለማት ጌታ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች እንደሆኑ ሁሉ በተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር "መላእክት" እና "ኢብሊሥ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች ናቸው። በተጨማሪ አንድ ጥቅስ እንመልከት፦
17፥67 በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው ሁሉ ይጠፋሉ፥ እርሱ(አላህ) "ሲቀር"፡፡ وَإِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فِي الْبَحْرِ ضَلَّ مَن تَدْعُونَ إِلَّا إِيَّاهُ

ጣዖታዊያን በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛቸው ጊዜ የሚጠሩዋቸው ጣዖታታት የሰው እጅ ሥራዎች ሲሆኑ ይጠፋሉ፥ አሏህ ግን ሕያው ፈጣሪ ስለሆነ አይጠፋም። ስለዚህ "በቀር" "በስተቀር" ስለተባለ ዐውዱ እና አጠቃላይ አሳቡ ሳይታይ "አንድ ምድብ ነው" ማለት ስህተት እንዳለው ከተረዳን ዘንዳ "በቀር" ስላለ ኢብሊሥን የመላእክት ጥንተ ተፈጥሮ ውስጥ ማካተት ስህተት ነው።
ኢብሊሥ ከጂን እንጂ ከመላእክት አለመሆኑ ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ከሲር በመቀጠል በተፍሢሩ ላይ አድ-ደሓክ፣ ሠዒድ ኢብኑ ጀቢር፣ ኢብኑ ኢሥሐቅ ወዘተ "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" ያሉት ከኢሥራዒልያት ትርክት እንደሆነ ተናግሯል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው፦ "ኢብሊሥ ከመላእክት አይደለም፥ ለአንዲት ቅጽበት እንኳን አልነበረም። ልክ አደም"ዐ.ሠ." ለሰው ሥረ-መሠረት እንደሆነ ሁሉ ኢብሊሥም ለጂን ሥረ-መሠረት ነው"። ይህ በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው።  قال الحسن البصري : ما كان إبليس من الملائكة طرفة عين قط ، وإنه لأصل الجن ، كما أن آدم ، عليه السلام ، أصل البشر . رواه ابن جرير بإسناد صحيح
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"በእርግጥ በዚህ ሪዋያህ ከቀደምቶቹ የተተረከው ዘገባ አብዛኛውን ከኢሥራኢልያት እንደሆነ ይጤናል"።  وقد روي في هذا آثار كثيرة عن السلف ، وغالبها من الإسرائيليات التي تنقل لينظر فيها

፨ሢሰልስ መላእክት የተፈጠሩበት ንጥረ ነገር ብቻ ሳይሆን ባሕርያቸውም ይለያል፥ መላእክት ፆታ የላቸውም፦
43፥19 "መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ"፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው "መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ

ከመላእክት መካከል ሴቶች ቢኖሩ ኖሮ ቁሬሾች፦ "መላእክት ሴቶች ናቸው" ማለታቸውን አይቃወምም ነበር፥ አሏህ መላእክትን ሴቶች አድርጎ አልፈጠረም። ጂኒዎች ግን ጾታ አላቸው፥ ዝርያ ስላላቸው የሚራቡ ወንድ እና ሴት ናቸው፦
18፥50 "እርሱን እና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲኾኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ! أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ ۚ بِئْسَ لِلظَّالِمِينَ بَدَلًا
72፥6 እነሆም "ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጂኒ ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ"፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡  وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፥ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ "አሏህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው" ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏