Get Mystery Box with random crypto!

ኢብሊሥ መልአክ ነበርን? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 18፥50 | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ኢብሊሥ መልአክ ነበርን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس  የሚለው ቃል "በለሠ" بَلَسَ ማለትም "ተስፋ ቆረጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተስፋ የቆረጠ" ማለት ነው፥ "ኢብሊሥ” إِبْلِيس  የሚለው ቃል 11 ጊዜ በ 11 ቦታ ከጂን ለሆነ ፍጡር የተሰጠ የግብር ስም ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር። ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ከጂን ነበር" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት "ጂኒ" جِنِّيّ የሚለው ቃል "ጀነ" جَنَّ ማለትም "ሰወረ" "ደበቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስውር" "ድብቅ" ማለት ነው፥ "ጂን" جِنّ ደግሞ የጂኒ ብዙ ቁጥር ነው። ኢብሊሥ ጥንተ ተፈጥሮው ከጂን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፣ ጃን ከእሳት ነበልባል ተፈጥሯል፣ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል"፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

"ጃን" جَانّ ልክ እንደ "ሰው" ለጂኒዎች ጥቅላዊ ስም ነው፥ መላእክት እና ጃን "ወ" وَ ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር መጠቀሙ በራሱ መላእክት እና ጂን ሁለት የተለያዩ ፍጥረታት እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። እዚህ ድረስ ከተግባባን "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" ብለው ሚሽነሪዎች የሚሞግቱት በዚህ ጥቅስ ነው፦
17፥61 ለመላእክትም "ለአደም ስገዱ" ባልናቸው ጊዜ አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ

፨ሲጀመር "ለ" የሚለው መስተዋድድ "መላእክት" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ መግባቱ አሏህ "ስገዱ" ያለው "ለመላእክት ብቻ" እንደሆነ ማስረጃ መሆን በፍጹም አይችልም። ይህንን በአንድ ተመሳሳይ ሙግት እንሞግት፦
7፥79 "ለ"-እነርሱም ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፣ "ለ"-እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፣ "ለ"-እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

ዐውዱ ላይ "እነርሱ" የተባሉት "ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፥ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው" የተባሉትን ነው፥ ቅሉ ግን "ለ" የሚለው መስተዋድድ "እነርሱ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መምጣቱ ልቦች፣ ዓይኖች፣ ጆሮዎች አሉዋቸው የተባሉት ዘንጊዎቹ እና የተሳሳቱት ብቻ ናቸው እንደማንል ሁሉ አሏህ "ስገዱ" ያለው ለመላእክት ብቻ ሳይሆን ለኢብሊሥም ጭምር ነው፦
7፥12 አላህ፦ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ

አሏህ ያለው "ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ሳይሆን "ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ነው፥ "ባዘዝኩህ" የሚለው ኃይለ-ቃል አሏህ ለአደም "ስገድ" ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" ማለቱ በራሱ እንዲሰግድ የታዘዙት መላእክት ብቻ አለመሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
18፥50 ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ