Get Mystery Box with random crypto!

ከዕባህ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 105፥1 በዝሆኑ ባለቤ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ከዕባህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

105፥1 በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ

"ከዕባህ" كَعْبَة ማለት "አንኳር“cube" ማለት ሲሆን አንኳር "ምልዓት" ነው፥ ምልአት ባለ ሦስት ቅጥ ነው። ይህም ቁመት፣ ርዝምት እና ስፋት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከዕባን የተቀደሰ ወይም የተከበረ ቤት አደረገው፦
5፥97 "ከዕባን የተከበረውን ቤት፣ ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፡፡ جَعَلَ ٱللَّهُ ٱلْكَعْبَةَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ قِيَٰمًۭا لِّلنَّاسِ وَٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَٱلْهَدْىَ وَٱلْقَلَٰٓئِدَ
3፥96 ለሰዎች መጀመሪያ የተኖረዉ ቤት ቡሩክ እና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው። إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍۢ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِى بِبَكَّةَ مُبَارَكًۭا وَهُدًۭى لِّلْعَٰلَمِينَ

ከዕባህ ለሰዎች መጀመሪያ የተኖረዉ ቤት ቡሩክ እና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሆኖ ሳለ የአክሱም መንግሥት ንጉሥ ካሌብ እስከ የመን ድረስ ይገዛ ነበር። በጃሂሊያህ ጊዜ የካሌብ ጦር መሪ አብረሃህ አል አሽረም በ 527 ድኅረ ልደት በየመን ውስጥ ከአሏህ ቤት ጋር በማፎካከር ቤተክርስቲያን አሠርቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 49
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “በዘመነ-ጃሂሊያ ዙል-ኸለሷህ የሚባል ቤት ነበረ፥ የቀኝ ከዕባህ ወይም የግራ ከዕባህ ተብሎ ይጠራ ነበር”። عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ كَانَ فِي الْجَاهِلِيَّةِ بَيْتٌ يُقَالَ لَهُ ذُو الْخَلَصَةِ، وَكَانَ يُقَالُ لَهُ الْكَعْبَةُ الْيَمَانِيَةُ، أَوِ الْكَعْبَةُ الشَّأْمِيَّةُ

“ኸለሷህ” خَلَصَة ማለት “ቀሊሥ” قَلِسْ ማለት ነው፥ “ቀሊሥ” ከግሪኩ ኮይኔ “ኤክሌሲያ” εκκλεσια የመጣ ሲሆን በተለምዶ “ቤተ ክርስቲያን” ይባል እንጂ “ጉባኤ” “ማኅበር” “ተጠርተው የወጡ” ማለት ነው። ይህንን ቤት ከከዕባ ጋር ለማመሳሰል “አል ከዕበቱል የማኒያህ” الْكَعْبَةُ الْيَمَانِيَة ወይም “አል ከዕበቱሽ ሸእሚያህ” الْكَعْبَةُ الشَّأْمِيَّة ብሎታል። በ 570 ድኅረ ልደት "አብረሃህ አል አሽረም" أَبْرَهَة ٱلْأَشْرَم እና ጭፍሮቹ የአሏህ ቤት ለማፍረስ በዝሆን ጋልበው ወደ መካ መጡ፥ አሏህም እነዚህን የዝሆን ባለቤቶችን ተንኮል በጥፋት ውስጥ ከንቱ አደረገ፦
105፥1 በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ
105፥2 ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ ከንቱ አላደረገምን? أَلَمْ يَجْعَلْ كَيْدَهُمْ فِي تَضْلِيلٍ

አምላካችን አሏህ በእነርሱም ላይ ከተጠበሰ ጭቃ በኾነ ድንጋይ ማለትም በሸክላ”brick” የሚወረውሩባቸው መንጎች የኾኑን አዕዋፍን በመላክ ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራም አደረጋቸው፦
105፥3 “በእነርሱም ላይ መንጎች የኾኑን አዕዋፍን ላከ”፡፡ وَأَرْسَلَ عَلَيْهِمْ طَيْرًا أَبَابِيلَ
105፥4 “ከተጠበሰ ጭቃ በኾነ ድንጋይ የምትወረውርባቸው የኾነችን አዕዋፍ”፡፡ تَرْمِيهِم بِحِجَارَةٍ مِّن سِجِّيلٍ
105፥5 “ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራም አደረጋቸው”፡፡ فَجَعَلَهُمْ كَعَصْفٍ مَّأْكُولٍ

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቁረይሾች ጊዜ ሲቆጥሩ እራሱ “ዓሙል ፊል” عامُ الْفِيلِ ማለትም “የዝሆን ዓመት” እያሉ ነበር።
የአብረሃህ አል አሽረም አድራጎት ይህን ያህል ከተወገዘ ዘንዳ ከዕባን አስመስሎ ሠርቶ "ከዕባህ ነው" ማለት ከላይ እንዳየነው ዋጋ ያስከፍላል፥ የአላባ ሙሥሊሞች በቅንነት ኢሥላምን ለማስተዋወቅ ብለው የከዕባህ ቅርጽ በጊዜአዊነት መሥራታቸው ለማስተማሪያነት እንጂ በቋሚነት መሥጂድ ለማድረግ አልነበረም። ስህተታቸውን በትህትና ከማረም ይልቅ በስድብ ማጥረግረግ ጉዳዩን እንዲጦዝ እና እልክ መግባባት አርጎታል፥ ይህ ደግሞ አሏህ አደራ እንድንባባል ካዘዘን ጋር ይጋጫል፦
90፥17 ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ
103፥3 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ

አንድ ሰው ሐቅ ስለያዘ ብቻ ሐቁን ለማስተላለፍ ስድብ መፍትሄ አይሆንም፥ ከዚያ ይልቅ አደራ መባባል በሐቅ ብቻ ሳይሆን በትግስት እና በማዘንም ጭምር ቢሆን የተሳሳተው ሰው ከስህተቱ ሊመለስ ዝግጁ ይሆናል። ኢሻሏህ ጠርዝ ይዘው የሚጠዛጠዙ እነዚህ ሁለቱም ጽንፎች ከዚህ ድርጊታቸው እንደሚታረሙ ተስፋ አለኝ!
አምላካችን አሏህ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም