Get Mystery Box with random crypto!

ስለዚህ ከመነሻው 'ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም' ያለው አሏህ ሳይሆን አሏህ ተወዳጁ ነ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ስለዚህ ከመነሻው "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ያለው አሏህ ሳይሆን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችን እና ምእመናን እንዲሉ ያዘዘው ትእዛዝ ነው፥ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ብለው የሚያምኑት ምእመናን ሆነው ሳለ አሏህ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ብሎ እንደተናገረ አርጎ መረዳት ዓረፍተነገሩን ከዐውዱ ማፋታት ነው። "አመነ" آمَنَ እና "አመና" آمَنَّا የሚል ኃይለ ቃል ከአንቀጹ በማውጣት እና የራስን አሳብ መክተት በሥነ አፈታት ጥናት"hermeneutics" ፈቲሆት"exegesis" ሳይሆን ሰጊዎት"eisegesis" ነው።
አሏህ እኛን፦ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" "በሉ" ያለበት ምክንያት አይሁዳውያን አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው ማውረዱን በምቀኝነት በመካዳቸው ነው፦
2፥90 ነፍሶቻቸውን በእርሱ የሸጡበት ነገር ከፋ! እርሱም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡ بِئْسَمَا اشْتَرَوْا بِهِ أَنفُسَهُمْ أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ችሮታ" ለሚለው የገባ ቃል "ፈድል" فَضْل ሲሆን ሲሆን "ስጦታ" "ችሮታ" "ጸጋ"Bounty” ማለት ነው፥ ሥርወ-ቃሉ "ፈዶለ" فَضَّلَ ማለትም" ሰጠ" "ቸረ" ነው። አምላካችን አሏህ በሚያወርደው ፈድል መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አብልጧል፦
2፥253 እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ
17፥55 ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አበለጥን፡፡ وَلَقَدْ فَضَّلْنَا بَعْضَ النَّبِيِّينَ عَلَىٰ بَعْضٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "አበለጥን" ለሚለው የገባ ቃል "ፈዶልና" فَضَّلْنَا መሆኑን ልብ ብለካልን? አንደ መልእክተኛ ጋር የተወረደለት ፈድል ሌላው ጋር ሰለሌለ ከፍሉ በከፊሉ ላይ ይበላለጣሉ፥ ለምሳሌ፦ አሏህ ሙሣን በቀጥታ ሲያናግር ሌላውን በመልአክ ወይም በራእይ በማናገር ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አብልጧል፦
2፥253 ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አለ፡፡ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ
4፥164 አላህ ሙሣን ማነጋገርን አነጋገረው፡፡ وَكَلَّمَ اللَّهُ مُوسَىٰ تَكْلِيمًا

ይህ የደረጃ ልዩነት እንጂ የኑባሬ ልዩነት አይደለም። ለምሳሌ፦ አሏህ ለመርየምን ልጅ ለዒሣ ግልጽ ተአምራትን በመስጠት እና በቅዱሱ መንፈስ በማበረታታት አብልጧል፦
2፥253 ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሣን ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፥ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ ۚ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ
2፥87 የመርየምን ልጅ ዒሣን ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ

ግጭት ማለት አሏህ እኛን፦ "እኩል አርጋችሁ እመኑ" ብሎን በተቃራኒው "አንዱን መልእክተኛ ከሌላው አስብልጡ" ቢለን ወይም አሏህ፦ "መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን" ብሎ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል ስንለይ እኩል አርገናል" ቢል ኖሮ ግጭት ነበር። ነገር ግን ቁርኣን የፈጣሪያችን የአሏህ ንግግር ስለሆነ እና የሰው ንግግር ስላልገባበት የእርስ በእርስ ግጭት የለውም፦
4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

"ኢኽቲላፍ" اخْتِلَاف ማለት "ግጭት" ማለት ሲሆን ቁርኣን ከአሏህ ዘንድ በግልጠተ መለኮት የመጣ የአሏህ ንግግር ስለሆነ እርስ በእርስ አይጋጭም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም