Get Mystery Box with random crypto!

ይጋጫልን? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 4፥82 ቁርኣንን አ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ይጋጫልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ፦
"አሏህ መልእክተኞች እኩል አድርጓል ወይስ አላደረገም?
A. እኩል አድርጓል፦
2፥285 "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ

B. እኩል አላደረገም፦
2፥253 "እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን"፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ

መልስ፦
ለአይሁዳውያን፦ «አላህም ባወረደው ሁሉ እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው ብቻ እናምናለን» ይላሉ፥ "በእኛ ላይ በተወረደው" ለሚሉት ለነቢያት ወሕይ አረጋጋጭ የሆነው ቁርኣን በመካድ በከፊሉ በማመን እና በከፊሉ በመካድ አስተባብለዋል፦
2፥91 ለእነርሱ «አላህም ባወረደው ሁሉ እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው ብቻ እናምናለን» ይላሉ፥ ከእርሱ በኋላ ያለው እርሱ ከእነርሱ ጋር ላለው አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ آمِنُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ قَالُوا نُؤْمِنُ بِمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَيَكْفُرُونَ بِمَا وَرَاءَهُ وَهُوَ الْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَهُمْ

አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን "ቁል" قُلْ በሚል ትእዛዛዊ ግሥ በእርሳቸው ላይ በተወረደው ቁርኣን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ በተወረደው ወሕይ "አመንን" እንዲሉ አዟል፦
3፥84 በል፦ "በአላህ እና በእኛ ላይ በተወረደው አመንን" قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا
3፥84 "በኢብራሂም፣ በኢስማዒል፣ በኢስሓቅ፣ በያዕቆብ፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፣ ለሙሳሣ እና ለዒሣ በተሰጡት፣ በዚያም ለነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን"። وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ

አምላካችን አሏህ ለዚያ ነው፦ "መልእክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ" በማለት የነገረን፦
2፥285 መልእክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ

ሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ አምላካችን አሏህ የተወዳጁ ነቢያችን ተከታዮች ምእመናን "ቁሉ" قُولُوا በሚል ትእዛዛዊ ግሥ በእነርሱ ላይ በተወረደው ቁርኣን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ በተወረደው ወሕይ "አመንን" እንዲሉ አዟል፦
2፥136 በሉ፦ "በአላህ እና ወደ እኛ በተወረደው አመንን" قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا
2፥136 ወደ ኢብራሂም፣ ወደ ኢስማዒል፣ ወደ ኢስሐቅ፣ ወደ ያዕቁብ እና ወደ ነገዶቹም በተወረደው፣ በዚያም ለሙሣ እና ለዒሣ በተሰጡት፣ በዚያም ለነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት አመንን"። وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ

አምላካችን አሏህ ለዚያ ነው፦ "ምእመናን እንደዚሁ አመኑ" በማለት የነገረን፦
2፥285 ምእመናን እንደዚሁ አመኑ፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ

"ሁሉም" ማለትም ተወዳጁ ነቢያችን እና ምእመናን «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ፦
2፥285 ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልእክተኞቹም «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ፡፡ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ
3፥84 "ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም" نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ
2፥136 "ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም" نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ

በሁሉም ነቢያት ላይ የተወረደው የመልእክቱ ጭብጥ ተውሒድ ስለሆነ ከእነርሱ መካከል አንድንም ሳንለይ እናምናለን፥ "ላ ኢላሀ ኢላ አና" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا የሚለው መገሰጫ ለነቢያችን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ የወረደ መገሰጫ ነው፦
21፥24 «አስረጃችሁን አምጡ፡፡ ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው» በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي
21፥25 ከአንተ በፊትም፦ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልእክተኛ አንድንም አላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"ዚክር" ذِكْر ማለት "መገሰጫ" ማለት ሲሆን ለሁሉም መልእክተኞች የወረደውን መልእክት ተህሊል ስለሆነ አይሁዳውያን በመልእክተኞቹ መካከል ሳይለዩ ማመን ሲገባቸው በተቃራኒው በመካድ «በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ እነዚያ በእውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው። ለእነርሱ አዋራጅን ቅጣት አሏህ አዘጋጅቷል፦
4፥150 እነዚያ በአላህ እና በመልእክተኞቹ የሚክዱ፣ በአላህ እና በመልእክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉ፣ «በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ፣ በዚህም መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ እነዚያ በእውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُوا بَيْنَ اللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ وَنَكْفُرُ بِبَعْضٍ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُوا بَيْنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ حَقًّا ۚ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا