Get Mystery Box with random crypto!

ኢፍጣር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 33፥35 'ጦመኛ ወን | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ኢፍጣር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥35 "ጦመኛ ወንዶች እና ጦመኛ ሴቶችም፣ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶች እና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶች እና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"፡፡ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

“ፊጥር” فِطْر የሚለው ቃል "ፈጦረ" فَطَرَ ማለትም "ገደፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ጦም መግደፊያ" ማለት ነው፥ የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው። ለምሳሌ፦ የረመዷን ጦም ማብቂያ በዓል እራሱ "ዒዱል ፊጥር" عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል፥ "ዘካቱል ፊጥር" زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው። በተመሳሳይ “ኢፍጣር” إِفْطَار የሚለው ቃል "አፍጦረ" أَفْطَرَ ማለትም "አፈጠረ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ጦም መግደፍ" ማለት ነው፥ ጦመኛን ያስፈጠረ ጦመኛው ከሚያገኘውን ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ጦመኛው ሊያገኘው የሚችለውን ምንዳ ያገኛል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 109
ዘይድ ኢብኑ ኻሊድ አል ጁሀኒይ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጦመኛን ያስፈጠረ ጦመኛው ከሚያገኘውን ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ጦመኛው ሊያገኘው የሚችለውን ምንዳ ያገኛል"። عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ الْجُهَنِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ فَطَّرَ صَائِمًا كَانَ لَهُ مِثْلُ أَجْرِهِمْ مِنْ غَيْرِ أَنْ يَنْقُصَ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏"‏ ‏.‏

አደባባይ ላይ እዩልኝ እና ስሙልኝ በማለት ከመበሻሸቅ፣ ከመነታረክ፣ እልህ ከመገባባት፣ ከመፎካከር ይልቅ ከወለጋ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን በካምፕ ውስጥ ያሉትን የወሎ ሙሥሊሞችን ማስፈጠር አንርሳ! እነዚህ ተፈናቃዮች ዱንያህ ላይ ተስፋ ቆርጠው አኺራቸውን በመጠባበቅ ላይ በሞት እና በሕይወት መካከል ያሉ የሊላሂ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ናቸው። እውነት ለአሏህ ከተባለ እነዚህን ስደተኞች ባለን አቅም መጎብኘቱ እውነተኛ አጅር አለው። አሏህ ይቀበላችሁ!

አምላካችን አሏህ ጦመኛ ወንድ ባሪያውን "ሷኢም" صَّائِم ሲለው ጦመኛ ሴት ባሪያውን ደግሞ "ሷኢማህ" صَّائِمَة ይላታል፥ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፦
33፥35 "ጦመኛ ወንዶች እና ጦመኛ ሴቶችም፣ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶች እና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶች እና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምሕረትን እና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"፡፡ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

አሏህ "ሷኢሚን" صَّآئِمِين እና "ሷኢማት" صَّآئِمَٰت ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም