Get Mystery Box with random crypto!

የዘካህ አወጣጥ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 2፥110 ሶላት | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የዘካህ አወጣጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

የዘካ ገንዘብ ከተቀማጭ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5 ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 2.5 ይሆናል፥ ስሌቱ 5፥2=2.5 ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል። በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት ጊዜ የሸቀጥ ገንዘብ”commodity money” ነው። “ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያስቀመጠው ካፒታል ዓመት ከሞላው እና ያም ካፒታል 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው።
ዘካቱል ማል የሚወጣበት አነስተኛ ዋጋ የብር ኒሷብ ስለሆነ አብላጫው ምሁራን የብር ኒሷብን መሠረት ባደረገ መልኩ ከዚያ እንዲወጣ ፈትዋ ሰተዋል፥ ስለዚህ አንድ ሰው ዓመት የተቀመጠ 89,250 ብር(ገንዘብ) እና ከዛ በላይ ካለው ዘካህ ማውጣት ግዴታ አለበት።

እንዴት? ካላችሁ የብር ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ብርን ዛሬ ባለው የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል። በኢትዮጵያ አንድ ግራም ብር"silver" አሁን ባለኝ መረጃ 150 ብር"ገንዘብ" ነው፥ ስናሰላው 150×595= 89,250 ብር(ገንዘብ) ይሆናል።
ለምሳሌ፦ እኔ 100 ሺህ ብር ቢኖረኝ ከ 100 ሺህ ብር ላይ 2.5 % ዘካህ ሲሰላ 2,500 ይወጅብብኛል፥ ስናሰላው 100,000×2.5፥100= 2,500 ይሆናል።
ዘካህን መስጠት አንርሳ፦
2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

አምላካችን አሏህ ዘካን ከሚሰጡ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም