2022-06-27 19:08:17
#ሚስዮናዊነት
ደህንነትን በእርግጥ አግኝተናል ወይስ ደህንነት የሚመስለውን ቅብ ነው ያገኘነው??? ዛሬ ቱንቢያችንን በደህንነታችን ላይ ጥለን እንለካለን
ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ትክክለኛውን ቤት እንሰራለን
በፍጥረት መጀመሪያ ላይ ሰውን ሲፈጥር የነበረውን መልክ በኃጢአት ምክንያት ጠፋ፤ ያንን መልክ ለመመለስ ለተመረጠው ህዝብ ሕግ ተሰጠ። ሕግን በራስ አቅምና ችሎታ ለመፈፀም ግን በጣም ከባድ ሆነ ሕጉ ወደ እግዚአብሔር ከማስጠጋት ይልቅ ኃጢአትን በደንብ እንዲያውቁ አደረገ። ከዚያም መሲሁን ክርስቶስን ወደ ምድር ሰው ሆኖ በመገለጥ ሕግን ሁሉ በመፈፀም ኃጢአትን አሸነፈ። እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ማስተዋል ያለብን; ኢየሱስ ክርስቶስ ሕግን ሁሉ ፈፀመ ስንል ሻረልን (ከሕግ በላይ) ሆንን ህግን መጠበቅ አይጠበቅብንም ማለት አይደለም። ይልቁንስ ሊያጠፋን የሚችለውን ኃጢአትን ማሸነፍ የምችልበትን ሕግን ሁሉ መፈፀም የሚያስችለውን #ፀጋ በመንፈሱ አማካኝነት አለበሰን ሕጉንም አጠበቀው። እንኳን ህግን ሻረ ልንል ይልቁንም አጠበቀው ምክንያቱ ደግሞ በፊት አታመንዝር ያለው አሁን ግን ያየ የተመኘ ኃጢአተኛ ነው አለ: ባልንጀራችሁን ውደዱ ያለው የሚጠሉአችሁን ውደዱ አለ፤ ግን ህጉን ብቻ ሰቶን ራሳችሁ ተወጡት አላለንም ማድረግም የምንችልበትንም #ፀጋ ሰጠን።
እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል፤ ይቀጣልም። አንዴ አምኜ ድኛለው ስለዚህ ኃጢአትን ብሰራ እንኳን (Continuously) የደህንነት አክሊሌን አላጣም" በሚል እምነት ዋናቸውን ይነጥቃቸዋል። ይሄንንም እውነት እንዲመስል የወልድን ስራ በጣም አልቆና አጉልቶ ያሳዩናል፤ እኔ አሁን ለደህንነቴ የምሰራው ስራ አይኖርም ኢየሱስ ሰርቶ ጨርሶልኛል ይላሉ ልክ ናቸው እኛ ለመዳን ማመን ብቻ ነው የሚጠበቅብን ከዳንን በኃላ ግን እንድንቀደስና እንደሚገባ እንድንኖር መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል። መንፈስ ቅዱስ እኛን ገና ሰርቶን አልጨረሰንም ደህንነታችን አላለቀም። (ኤፌ 2፥21-22)
#የክርስቶስ_ፀጋ ሕግን መፈፀም እንድንችል ይረዳናል።ፀጋው በክርስቶስ አምነን፣ ኃጢአትን ክደን ፣ ተቀድሰን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ያደርገናል።
ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
#ፀጋው ኃጢአትን እንዳናደርግ ብቻም ሳይሆን መልካም ነገርን እንድናደርግ ያግዘናል። “እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።”
— ያዕቆብ 4፥17
ይህ ፀጋ እምነታችንን በስራ እንድንተገብር ያደርጋል።እምነትና ስራ ተነጥለው የሚታዩ አይደሉም።
ያዕቆብ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
¹⁸ ነገር ግን አንድ ሰው፦ አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
ስለዚህ ሊገባን የሚገባው ነገር እምነታችን ስራም አለው፤ ኃጢአትን ክደን ኃጢአተኛ ሆኖ መቀጠል አያድንም። እግዚአብሔር በምንም ሁኔታ ለኃጢአት ስፍራ ኖሮት አያውቅም የለውምም። ነፍሴና መንፈሴ ድነዋል በስጋዬ ኃጢአት ብሰራ Nothing አይባልም በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ አንዱን ከአንዱ ነጥሎ አይቀድስም!“የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” — 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥23
#ሁለት_ነገሮችን_እናስተውል!!
፩. ኢየሱስ ሕግን ፈፅሞልናል ኃጢአት ብንሰራም አንዴ አምነናልና ደህንነታችን አይጠፋም ማለት እምነትን ከስራ ለይተን ለማሳየት መሞከርና የፀጋውን ባለጠግነት ማሳነስ ነው።
ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
²³ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
፪. የፀጋውን ጉልበት ተረድተን ግን ደግሞ ስፍራ ያልሰጠን ደግሞ በተሰጠን ፀጋ መልካም ነገሮችን ለማድረግ መጣጣር እንጀምር። ፀጋው አድኖናል ደግሞም ያድነናል።
JOIN JOIN JOIN
------------------------------------
@TUNBI_LOVE_MEDIA
@TUNBI_LOVE_MEDIA
------------------------------------
306 viewsMeti Mulugeta, 16:08