Get Mystery Box with random crypto!

ጭንብሊቲ እና አጋጣሚዉ አቶ ኮረና ሀገራችንን ከጎበኛት በኋላ ጭንብል መልበስ ግ | የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

ጭንብሊቲ እና አጋጣሚዉ


አቶ ኮረና ሀገራችንን ከጎበኛት በኋላ ጭንብል መልበስ ግድ ሆኗል፤ እኔም ከለባሾቹ ታጭቼ መልበስ ስጀምር መጀመሪያ ላይ ጆሮዬን ያቃጥለኝ ነበር ዳገት ስወጣ ደግሞ አንገቴን የታነኩ ያህል ያፍነኛል፤ በኋላ ላይ ግን ወደድኩት አቦ እንዴት መሠላችሁ

፦ የሆነ ቀን ነዉ በጣም ተናድጄ ነበር፤ ሰአቱም ደረሰና ወደስራ ለመሄድ በፍጥነት ለብሼ(ጭንብሉንም) ጉዞ ጀመርኩ፤

ወደ ስራ በዛ አካሄዴ ንዴቴ ተጨምሮበት እብድ አስመስሎኛል፤(ለነገሩ አለመሆኔን በምን አዉቃለሁ)
ለማንኛዉ እየለፈለፍኩ መሆኔን ያወኩት የራሴ ትንፋሽ ሲያቃጥለኝ ነበር ። እጄንም ሳየዉ ይንቀሳቀሳል፤

"አቤት ቅሌት" አልኩ የታወቀኝ ምናልባት ስራ ቦታዬ ስለደርስኩ ይሆናል (መድረሰኔም ልብ አላልኩ)
ትንሽ አሰብ አድርጌ "ወይኔ አሁን ማክስ ባለብስ ኖሮ ሰዉ አበደች እንዴ? አይለኝም" ነበር አልኩ ትዝ ይለኛል የሆነ ቀን መንገድ ስሄድ ኤርፎን ሰክቼ የበእዉቄን(በእዉቀቱ ስዩም) ወግ እየሰማሁ ሲሄድ አለመሳቅ አልቻልኩምና ሳቄን ለቀኩት!

መሃል አስፓልት ላይ መሆኔ እራሱ አልታወቀኝም ለነገሩ መሆኔንም ያወኩት "ምፅ እቺን የመሠለች ልጅ ስታሳዝን" ብላ አንድ ጎልማሳ ሴት በእዝነት አንገቷን ስታንቀሳቅስ ነዉ። (ይኸዉ ከዛ ወዲህ በኋላ መንገድ ላይ የበእዉቄን መስማት ትቻለሁ) ይሄንኑ በግርምት እያሰብኩ ንዴቴ እንደረገበልኝ አልታዘብኩም ነበር፥

"ፐለዉ! በቃ እቃ ማጠብ ሊቀር ነዋ(ስናደድ እቃ ነዉ ማጥበዉ )
ኦ! ይሄ ነገር ለካስ ትንፋሽ ላለማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ለንዴትም ሃሪፍ ነዉ። ፐ!"

ጭንብሊቲ አሁንም ቀጥላለች
በሁለተኛው ቀን ከመደብራችን ፊትለፊት የሆኑ ሰዎች ይጣላሉ ከመጣላታቸዉ የበለጠ ግን የሚጣሉበት መንገድ ስለተመቸኝ ቆሜ መሾፍ ጀመርኩ፤ የአዋቂ እርምጃ ተራርቀዉ ጭንብላቸዉ አፋቸዉን ብቻ ሸፍኖት በአፍንጫቸዉ እያነፈነፉ፣ አንደኛው እግሩን ልክ ካራቴ ፊልም ላይ እንዳሉት በሩቁ እያንጠራራ ይማታል(ደግሞ አልደረሰበትም ምፅ) ያኛዉ ደግሞ በምርኩዝ ወገቡጋ ይለዋል፤

"ኮሮናዊ መጣላት መሆኑ ነዉ አልኩ" ለካስ ድምፅ አዉጥቻለሁ ማዉጣቴንም ያወኩት "ሂሂሂሂ አንቺ ቀዉስ" የሚል ድምፅ ስሰማ ነዉ። የኔ ጉድ አያልቅም!

"ኢሺሼ ሲያስጠላ" አለች አጠገቤ ያለችዉ
"ምነዉ" አልኳት
"አታይዉም" ብላ እጇን ወደሚጣሉት ጠቆመችኝ!
ጉዴን ሳስብ ረስቼዉ ነበር፤ ሳየዉ ለካስ አንደኛው "አኽኽ ቱ" ብሎ ሊተፋበት ሲል የራሱ ጭንብል ላይ ለድፎታል!

አመሌ ተነሳብኝና ሆዴን እስኪያመኝ ተንከተከትኩ!

ገና በጭንብሊቲ የማየዉ ጉድ እየታየኝ፦"ባንቺ ምክንያት ነዉ በአንቺዉ ምክንያት" ብዬ ለጭንብሊቲ መዝፈን አሰኘኝ፣ ያዉ ለብቻችን ስንሆን ሚስጥረኛዬም አይደለች


………… ፈትሒያ

ስለ-ፅሁፉ ሃሳብ አስተያየት ካላቹ ፦ @Fethetulletiya
ይጠቀሙ………………

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯