ከጨረቃ ስር. . . . . . . ኢዛና . . . . . . .ክፍል . . . . . . . . "አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ ድንገት በሕልሜ አይቼሽ ብነቃ …" የዳዊትን ዜማ ጮክ ብላ ታዜማለች : ስታዜም ወደጨረቃዋ አንጋጣ ነው ከጀርባዋ የተከፈተው የመጠጡ ቤት የሚንቦገቦግ መብራት ከፊል የፊቷን ገፅ እየቀያየረ ያሳየኛል ከፊል ፊቷን ደግሞ በጨለማው ውስጥ ያበራችው የምታዜምላት ጨረቃ ብረሐን ታሳየናለች :: ሲጋራዋን አንዴ ስትስበው እሳቱ ፈመ :: ከሷ ጎን አንዲት ሌላ ሴት ፀጉሯን እንደማስተካከል እያለች ድራፍቷን ትጎነጫለች ከመጠጥ ቤቱ ውስጥ ”ልጁን ያያችሁ አዬ እስቲ ን .ገ .ሩኝ …” ‘ሚለውን ዜማ ብዙ ድምፆች አጅበው ያዜማሉ :: የምሽቱ አየር ሞቅ ያለ ስለሆነ ከውስጥ ይልቅ በረንዳው ተመችቶኛል :: እዚህ ናዝሬት ከመጣው 1ሣምንት ሆነኝ የመጣዉበት ዓላማ ስላልተሳካ ዛሬ በተለይ ምርር ብሎኝ ነው የዋልኩት እዚች ቤት ሆኜ የምሽቱን ንግስቶች መልክ ሳጠናና ሳስተውል ይሄው ዛሬ 3ኛ ቀኔ ነው :: አንዲት አጭር ሞንዳላ ሴት ከማጨሠው ሲጋራ‘ወጋው ‘ ስትለኝ ሌላ ሲጋራ ስሰጣት ”ፍሬንድ ምነው አንተ ደግሞ ቺክህ ጥላህ ኮበለለች እንዴ … የሆነ ትካዜ ምናምን ነገር … አቦ ግባና ወዝወዝ በልበት ካስፈለገም ድብርቱን ….” አለችና ሌባ ጣቷን ካጣበቀቻቸው ሁለት ጣቶቿ ጋር ጧ ! አድርጋ እያማታች ”እኛ እንነቅልልሀለን ” ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች : በፈገግታዬ ሸኘዋት ያቺ ልጅ አሁንም ታዜማለች ሢጋራው አልቆ አመድና ቁራሽ ስፖንጅ ሆኖ ተወርውሮዋል … ”መስኮት ከፍቼ ውጪ ባይሽ ጨረቃም የለች አንቺም ጠፋሽ ዳግም አልተኛ ምን አደርጋለሁ እስክትመጪ እጠብቃለሁ ” ስታዜም ወደ ጆሮዎቿ ጥግ ተንጋደው ቀልበስ ያሉ ዓይኖቿ ይጨፈናሉ ቀለም የቃሙ ከናፍርቷ ይሾላሉ … የምጠጣዉን ድራፍት ያዝኩና አጠገቧ ሄድኩኝ ”ይቻላል …?” አልኳት አጠገቧ ያለዉን ወንበር ድራፍት በያዘ እጄ እያመላከትኳት አልመለሰችልኝም … ከራሷ ጨማምራበት ካልሆነ መቼም የዳዊት ግጥም እንደሆን አልቅዋል ተቀመጥኩኝ ”ጨረቃ ትወጂያለሽ ?” አልኳት እንደመፍራት ብዬ : ያቺ የቅድሟ ከመፀዳጃ ቤት ስትመለስ ገላምጣኝ ፈንጠር ብላ ተቀመጠች : ”እ … እኔን ነው ?” አለችኝ ያቺ ጨረቃ አፍቃሪ ”እንግዲያ … ጨረቃዋማ እንኳንስ እኔን ልትሰማ አንቺንም ስታዋራ አላየዋት ለሷ ማወራው ” አልኳት : ሳቀች ስትስቅ ሸራፋ ጥርሷ ሳቋን ቄንጠኛ አደረገላት : ”ከመጣህ 1 ሠዓት አልፎሀል እንዴት አሁን ታየውህ ?” አለችኝ ተቀምጬ የነበርኩበትን ወምበር ገልመጥ አድርጋ ቀይ ፊቷ ስጠጋው እንደቅድሙ ሲጋራዋ ፍም ቦግ ብሎ ታየኝ : ”አሁን አይደለም የታየሽኝ ቅድም ነው ዘፈንሽን ማቋረጥ አልፈለኩም ነበር ” አልኳት። * ይ * ቀ * ጥ * ላ * ል * ውብ አሁን ╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮ @tsihofoch @tsihofoch ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯ 332 views03:48