Get Mystery Box with random crypto!

ህልምና እውነት ----- እቴጌይት ቀኑን ሙሉ የፍሎሪዳን ሰማይ ተቆጣጥራ የዋልቸው ጸሀይ | የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

ህልምና እውነት

----- እቴጌይት

ቀኑን ሙሉ የፍሎሪዳን ሰማይ ተቆጣጥራ የዋልቸው ጸሀይ ከአድማሱ ጋር ፉክክር ገጥማ ላለመጥለቅ እየታገለች የምትፈነጥቀው ጮራ ለውሀው ዳር አካባቢ ልዩ ውበትን ለግሶታል:: ፍቃዱ የዘምባባው ዛፍ ስር አሸዋ ላይ ተንጋሎ ደረቱ ላይ ጋደም ያለቸውን የክርስቲናንእቴጌይቱና ይዳብሳል:: ከበረዶ የነጣ ቀለሟን ከእርሱ ጠይም ቆዳ ጋር አስተያየና ፈገግ ብሎ መዳበሱን ቀጠለ:: ሞቅ ያለውን አየር ለዘብ የሚያደርገው ንፋስ የውቅያኖሱን ውሀ አነስተኛ ማእበል እያሰራ ከአሸዋው ጋር ሲያላትመው የሚፈጥረውን ልዩ ድምጽ በጥሞና እያዳመጠ ሳለ ክርስቲና ቀና ብላ እይታው እጆቹን በለስላሳ ጣቶቿ መዳበስ ጀመረች:: ከመቅጽበት እንደኮረንቲ የሚነዝር ስሜት መላ ሰውነቱ ውስጥ መሰራጨት ሲጀምር ተሰማው:: ጣቱን በጣቷ እያፈተለተለች አንገቱ ስር ስትስመው ትንፋሹ እጥር እጥር እያለ ወንድነቱ እየጨመረ መሄድ ጀመረ:: ከአንገቱ ወደጉንጩ.... ከዛም ወደከንፈሩ ጥግ መሄድ ስትጀምር በመግነጢሳዊ ስበት እሱም ከንፈሯን ፍለጋ መዞር እንደጀመረ ከመቅጽበት የሆነ ነገር ግንባሩ ላይ ጠብ ሲል ተሰማው:: ፍንትው ካለ የረፋድ ሰማይ የምን ጠብታ ነው የመጣው ብሎ ከላዩ ላይ የተዘረጋውን የዘንባባ ዛፍ ቅርንጫፍ ቢያማትር ምንም የተለየ ነገር አልታየውም:: ግንባሩን ጠረገና ሀሳቡን ሲያሰባስብ ክርስቲና አንገቱ ስር እንደተወሸቀች የደረቱን ጸጉር ማፍተልተል ጀመራለች:: አይኑን በስሜት ጭፍን አድርጎ ምትሀታዊ ዳበሳዋን ማዳመጥ ሲቀጥል ከበፊቱ የተለቀ ጠብታ ግንባሩ ላይ ከዛም ጉንጩ ላይ ጠብ ጠብ ጠብ.....ማለት ሲጀምር በእልህ ደስ ከሚለው ስሜት ላለመውጣት ቢታገልም አልቻለም::....ድንገት ከእንቅልፉ ብንን አለና ኩምሽሽ ባለ ስሜት 'ኡፍፍፍፍ' ብሎ ወደጣራው ተመለከተ:: ገዳም ሰፈር ያለው የቤቱ የቆርቆሮ ጣርያ ቀዳዳ ሙዝዝ ያለውን የአዲስ አበባ የሀምሌ ዝናብ እያሾለከ የሚያንጠባጥበው ነበረ ፊቱና እያረጠበው የነበረው:: እንጥብጣቤውን ለማምለጥ አልጋው ላይ ፎቀቅ አለና ኩምሽሽ አንዳለ የክፍሉን ግርግዳ ሲያይ ያለፈው ዓመት ከአሮጌ መጽሄት ላይ ቀዶ የለጠፈው የክርስቲና አጉሌራ ፖስተር አፈጠጠበት:: ወዲያውኑም ትናንትና ከአክስቱ ልጅ ጋር በቪዲዮ ያየወን ፍሎሪዳ ውሀ ዳር የተሰራውን የፍቅር ታሪክ አስታወሰና ቁና ተነፈሰ:: 'ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ....አይ ሕልምና እውነት"

*-----------አለቀ ------------*

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯