Get Mystery Box with random crypto!

# ሲጨልም ደራሲ - እንዳለጌታ ከበደ ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ 'ልጄ' አ | የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

# ሲጨልም

ደራሲ - እንዳለጌታ ከበደ

ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ
"ልጄ" አሉት አስተናጋጁን ፤"የገዛሁትን መድሀኒት
ይዤብህ መጣሁ ፣ እባክህ የሰጠኸኝ ወስደህ.."
አላስጨረሳቸውም።ግድግዳው ላይ ወደተለጠፈ
ው ፅሁፍ አመለከታቸው።

'የተሸጠ መድኃኒት አይመለስም' አረጋዊው በለሰለሰ ቃላት መማፀን ያዙ።

"ሰውዬ ዞር በል!ስራ ልስራበት!ለእንቶ ፈንቶ ጉዳይ የማባክነው ጊዜ የለኝም..."አለ ቁጣው እየተወለደ" ዛሬ በዚህ ሰውዬ እንድጨቀጨቅ ተፈርዶብኛል ልበል?"

"እባክህን ልጄ አሳፋሪ ነገር ደርሶብኝ ነው።...
ዘመድና ዕድር የሌለኝ ከርታታ ሽማግሌ ስለሆንኩ
እንጂ..."አሉት ትሁት በሆነች ፈገግታ ሊያባብሉት
እየሞከሩ፤ " ቅናሽ ዋጋ ብትከፍለኝም..."

"ይሄ ሰውዬ ነካ ያረገዋል ልበል?" አለና ሌሎች
መድኃኒት ገዥዎችን ያስተናግድ ገባ።"ከያዙ
አይለቁ"

"ድህነት ቢፈትነኝ ነው ልጄ" አሉ - ያደፈና የነተበ
ነጠላቸውን እያሳዩት። ነጠላው ከሰውነታቸው
በከፋ ሁኔታ ያረጀ ኮታቸውን ደብቆላቸዋል፤

"አቅሜ የደከመ ባይሆን ኖሮ..."አሉት፤ጫማ ካገኘ
የከረመ እግራቸውን እያዪ። አንዲት ተስተናጋጅ

"አልመልስም ካለ አልመልስም ነው። ለምንድነው ሚነዘንዙት?" አለች በሚነጫነ
ጭ ድምፅ ፤"ይሄኮ ፋርማሲ እንጂ አዛውንቶች
የሚጦሩበት የድኩማን መርጃ ድርጅት አደለም"

አነጋገሯን ያልወደደው የሚመስል ሌላኛው
ጎልማሳ ደግሞ፤ "መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ የገዙ
ከዚሁ መደብር ነው?"የሚል ጥያቄ አመጣ።

"አዎ ዶክተሩ ፅፎ በሰጠኝ መሠረት" ብለው መለሱለት።

"ምን ያህል ፈጀብዎ?"

"ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም።መድኃኒቱን ወስዶ ግማሹን እንኳን ቢሰጠኝ ምን አለበት?" አሉ በሃዘኔታ

"የሁለታችንንም የጋብቻ ቀለበት
አስይዤ ነው ከማምነው ሰው የተበደርኩት"

"መድሀኒቱን ለምን መመለስ ፈለጉ ?" ዘንቢል
ያንጠለጠሉ አንዲት አሮጊት። በዚህ ጊዜ አስተናጋጁ ጣልቃ ገባ ፤

" ባህላዎሕክምና ብትከታተል ኪስ እደማታራቁት ገብቷቸው ይሆናል!ወይ ፀበል ሊያጠምቋት!ወይ..."

"አይ ልጄ ! ጉዳዩን ብታውቀዎ ኖሮ ያፌዝክበት
ምላስህን ታፍርበት ነበር..." አሉ እንባ እየተናነቃቸ
ው ።"መድኃኒቱን ምን ላርገው ልዋጠው ወይስ?
ሽንት ቤት ልጨምረው?"

"ለባለቤቴ ነው ምገዛላት ብለው አልነበር?......
በጠና ታማብኛለች፤የእድሜዬ ጀምበር እየጠለቀ
ባለበት ሰዓት ለእህል ያላነሱና ለትምህርት
ያልደረሱ ሦስት ልጆች በትናብኝ እዳትሄድ
ፀልይልኝ ፤ ብለውኝ አልነበር?"

"ማለቱንስ ብዬህ ነበር ልጄ!.....ብዬ ነበር"

"እና ሩብ ሰዓት ያህል እንኳን ሳይቆዩ ሃሳብዎን
አሰርዞ ፤ የገዙትን መድኃኒት የሚያስመልስ ምን
ተዓምር ተፈጠረ?!" ቅድም የማይመለከተኝን ነገርሲዘላብዱልኝ ነበር እኮ"አረጋዊው አንገታቸውንደፉ። "እኮ ምን ቢፈጠር ነው.....?"

"ቤቴ ሳልደርስ ነው አንተ ዘንድ የመጣሁት"

"ለምን?" አሉ ሌሎቹ

"ሰፈርተኞቼ ደጄ ላይ ሲጯጯሁ ዐየው።ባለቤቴን
በህይወቷ ልደርስላት አልቻልኩም!"አሉ አረጋዊው
ድምፃቸው እየሻከረ፤እንባቸው እየወረደ።

የመድሀኒት ሻጭው ፊት ላይ ፀፀትና ድንጋጤ
እየታየ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ በሻከረ እጃቸው
ላይ አኖረ። ሌሎቹም ኪሳቸውን ይፈታትሹ ጀመር

"ይባርካቹ ልጆቼ! ከፈን መግዣ ስላልነበረኝ እንጂ
........"እንባ ተናነቃቸው።መንሰቅሰቃቸውን እየቀጠሉ ወጡ።

ፀጥታ!!!!!!

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ !ለምንድነው?
ለማዘን ወይም መልካም ለመሆንና ሰዎችን
ለመውደድ ምክንያ ምንፈልገው?????
እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ???

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯