Get Mystery Box with random crypto!

የሺህ ዘመን ቀጠሮ ደራሲ - - - እሙሼ 'ተንስኡ ለፀሎት' ለሚለው የቄሱ የፀሎት ጥሪ በ | የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

የሺህ ዘመን ቀጠሮ

ደራሲ - - - እሙሼ


"ተንስኡ ለፀሎት" ለሚለው የቄሱ የፀሎት ጥሪ
በግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ የተሰበ
ሰበ ምእመናን "እግዚኦ ተሰሃለነ" በማለት ተስጥኦ
ውን መለሱ።

ሶስት ወጣቶች ቅዳሴውን ከመስማት ውጪ ተስ
ጥኦውን አይመልሱም። ምን አልባትም ቤተ ክርስ
ትያኑ ግቢ ውስጥ ይቁሙ እንጂ ቅዳሴውንም
አይሰሙትም። ሶስቱም ወጣቶች የሚያስቡት
ከደቂቃዎች በኃላ ስለሚጀምሩት የስደት ጉዞ ነው

ቀኑ እለተ ገብርኤል ነው፣ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና
ሁለት አመተ ምህረት። ሶስቱ ወጣቶች የመጨረሻ
ቸውን የስንብት ቃል ለመተንፈስ እጅ ለእጅ ተያይ
ዘው አይኖቻቸውን ወደ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክር
ስተያን ላኩ።

"ሀብታምም እንሁን በድህነትም ችግር ውስጥ
እንሁን ምንም ያህል ርቀት ከሀገራችን ርቀን ቢሆን
ም የምንኖረው መስከረም አንድ ቀን ሁለት ሺህ
አመተ ምህረት ማለዳ አንድ ሰሃት ላይ እዚች ቦታ
የግድ መገናኘት አለብን! ያ ቃላችን ነው!" አለ
ዳንኤል።

"ቃላችን ነው !እግዚያብሔር ይርዳን!ቅዱስ ገብሬ
ል ይከተለን።አሉ ንጉሱና ፍሰሃ
"እግዚአብሔር ሁላችንንም ከምንሰደድበት በሰላ
ም መልሶ እንዲያገናኘን አምላካችንን በፀሎት
እንጠይቀው" አለ ዳንኤል።

"አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ
መንግስትህ ትምጣ . . "በቅዳሴው መሀል ጮክ
ብለው መፀለይ ጀመሩ።ሲፀልዩ እንባቸው ከጉን
ጫቸው ይወርድ ነበር።

ጷግሜ ስድስት ቀን 1999 ዓ.ም

ዳንኤል ጷግሜ ስድስት የሚባል ቀን እረዝሞበት
ደጋግሞ "ምን አይነት የተንዘላዘለ ቀን ነው" ይላል
ሰሃቱን ተመለከተ ከምሽቱ ሁለት ከሃያ ሶስት ደቂ
ቃ ። ለቀጠሮው ስምንት ሰዓት ተኩል ይቀረዋል።
ስምንት ሰዓቱ ስምንት ሺ ዘመን መስሎ ታየው።
ስምንቱን ሰዓት የት ሄዶ እንደሚያሳልፈው ግራ ገ
ብቶታል ። መጠጥ ቤት መሄድ አልፈለገም።በአ
ጠቃላይ መጠጣትም አላሰኘውም። ጠጥቶ
እንቅልፍ ጥሎት የሺህ ዘመን ቀጠሮው እንዲያ
መልጠው አልፈለገም። አልጋው ላይ በጀርባው ጋ
ደም ብሎ መፅሀፍ ለማንበብ ሞከረ ነገር ግን ም
ንም የማንበብ ፍላጎት አልነበረውምና መፅሀፉን
አስቀምጦ በአፍ ጢሙ ተደፍቶ ተኛ።ምክንያቱ
ባልገባው ሁኔታ መላ ሰውነቱ በላብ ረጣጥቧል።

በደመ ነፍስ እጁን ሰዶ ስልክ አንስቶ ሁለት ቢራ
አዘዘ። ቢራው ካዘዘ በኃላ ነው "ምን ማድረጌ ነው
!?" ያለው።ሃሳቡን የመቀየር እንኳን እድል ሳያገኝ
የሂልተን ሆቴል አስተናጋጅ ሁለት ቢራ ይዞለት መ
ጣ። በሂልተን ሆቴል የመስተንግዶ ፍጥነት ተገረ
መ።

"በስንት ሰዓት ነው ከስራ የምትወጣው?"አለው
አስተናጋጁን።

"ጠዋት አንድ ሰዓት" አለ አስተናጋጁ።

"ዋው! ያማ ጥሩ ነገር ነው። ጠዋት አምስት ሰዓት
ኦ ማለቴ ጠዋት አስራ አንድ ሰዓት ላይ ትቀሰቅሰ
ኛለህ ? የማልቀርበት ቀጠሮ ስላለኝ ነው።"

"ምንም ችግር የለውም።ደውለው ሪሴፕሽን መቀ
ስቀስ የሚፈልጉበትን ሰዓት ከነገሩ በሰዓቱ ተደው
ሎ ሊቀሰቀሱ ይችላሉ።" አለ።

"ያ እሱንም አደርጋለሁኝ። ምን አልባት እነሱ ከረ
ሱት አንተ እንድትቀሰቅሰኝ ብዬ ነው"አለ ዳንኤል
አስተናጋጁ በአወንታ እራሱን ነቀነቀ።

ዳንኤል "እንካ ይቺን ያዛት!" ብሎ እጁን ወደ አስ
ተናጋጁ ዘረጋ። አስተናጋጁም በምስጋና ጎንበስ
ብሎ ከተዘረጋው እጅ ላይ ያለውን ነገር ተቀበለ።
አስተናጋጁም የተሰጠውን ነገር ገለጥ አድርጎ
ሲመለከተው የአንድ መቶ የአሜሪካ ዶላር መሆ
ኑን ተረዳ።

ዳንኤል ግንባሩን የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስት
ያን ላይ አስደግፎ እየፀለየ እያለ "ዳኒ!" የሚል
የሚጮህ ድምፅ ከፀሎቱ አናጠበው። ያንን ድም
ፅ ሰምቶ የሚቀጥለው ፀሎት አልነበረውም።የፀ
ሎቱ አንዱ ምክንያት ይህን ድምፅ መስማት ነው
ና።

ንጉሱ ተንደርድሮ መጥቶ ዳንኤል ላይ ተጠመጠ
መበት። አንዳቸው የአንዳቸዎን አካል ጥብቅና
ጭምድድ አድርገው ወደራሳቸው ስበው ለአፍታ
ተቃቅፈው ቆሙ። ቃላት ከአንደበታቸው አልወጣ
ም።እንባ በጉንጫቸው እየወረደ ለአፍታ አይን ለአ
ይን ይተያዩና ደግመው ይተቃቀፋሉ።መተቃቀፋቸ
ውን እንባቸው ያጅበዋል። የአንዳቸው እንባ የአንዳ
ቸውን ገላ ያርሰዋል። ተቃቅፈው ቆመው በሃሳብ
ነጎዱ። በሃሳብ ወደኃላ ስምንት ዓመት ተጉዘው
የተለያዩበትን ጊዜ አስታወሱ።ሌላ የሚያቅፋቸው
እጅ በቶሎ እንዲመጣ ጓጉ። የፍሰሃ እጆች።

ዳንኤል ሰዓቱን መልከት አደረገና "ሃያ ደቂቃ አረ
ፈደ እኮ ምን ሆኖ ይሁን !?" አለ የንጉሱን ፀጉር
እንደማስተካከል ዳበስ እያረገ።።

"ይመጣል!" አለ ንጉሱ በርግጠኝነት።

"ለማንኛውም እንገናኝ የተባባልንበት ቦታ እንሂድ"
አለ ዳንኤል።የተቀጣጠሩበትን የደውል ማማ
ከቆመበት ቦታ ቢያዩትም ቦታው ላይ ለመገኘት
መራመድ ጀመሩ።

"አምሮብሃል ካናዳ ተስማምቶሃል ማለት ነው?"
አለ ንጉሱ ወደ ዳንኤል እያየ።

ዳንኤል መልስ ከመስጠቱ በፊት አንዲት ቆንጆ
ሴት በነጠላ እንደተከናነበች አጠገባቸው መጥታ
ቆማ "ዳኒና ንጉሱ ናቹ አይደል?"አለች በፎቶ ላይ
ካየቻቸው ቢለወጡም እነሱ እደሆኑ ግን እርግጠ
ኛ ነበረች።

"አዎ! አዎ!" አሏት በቅደም ተከተል በወጣ ድምፅ

"እፎይ!"አለች በረጅሙ። የውስጥ እፎይታዋ የፈ
ነቀላቸው የሚመስሉ የእንባ ዘለላዎች ነጠላ ላይ
ተንጠባጠቡ።

"ምንድን ነው?ማነሽ አንቺ? ለምን ታለቅሻለሽ?"
ጠየቀ ንጉሱ።

"ፍሰሃ ነው አይደል ምጠብቁት?"

"አዎ ታውቂዋለሽ!?የት ነው ያለው?"በጥድፊያ
ጠየቀ ዳንኤል።

እንግዳዋ ሴት አይኖችዋን በነጠላዋ ሸፍና ጮሃ
ማልቀስ ጀመረች።"አንተ ነህ ፍሰሃዬ ቃልህን
ያልጠበከው አንተ ነህ ለአገርህ መሬት ያልበቃል
ው!" ማልቀስዋን ቀጠለች።

ንጉሱ አንገቷን ጨምድዶ ያዛት። በድንጋጤ ማልቀ
ስዋን አቁማ ፈጣ ተመለከተችው።
"አንድ ችግር ገጠመው እንዳትዩኝ ! ፍሰሃ ይመጣ
ል!" አለና ጨምድዶ አንቆ እንደያዛት ሲረዳ ይቅር
ታ ብሎ ለቀቃት ።

ዳንኤል እንባው ከጉንጩ እየወረደ።

"ምንድን ነው የሆነው ?ፍሰሃ የት አለ?" አለ ወደ
እንግዳዋ ሴት እያየ።

****ይቀጥላል*******

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯