Get Mystery Box with random crypto!

እኔ እና እኔ 'ባዶ እግሬን ነኝ። ጥርሴ ከከንናፍሬ እየተገጫጨ ይመለሳል ሰዉነቴ ያለ ፍቃዴ ይ | የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

እኔ እና እኔ

"ባዶ እግሬን ነኝ። ጥርሴ ከከንናፍሬ እየተገጫጨ ይመለሳል ሰዉነቴ ያለ ፍቃዴ ይንቀጠቀጣል፣ ይሄ ነዉ የማልለዉ ወላፈን ፊቴን ይለበልበኛል ለከሰለዉ ነፍሴ ትንፋሼ ይነድለታል፤
ገርጥጦ ወዜን የቀማኝ ስብራት አመድ አስመስሎኛል።

ዝናብ የለም ፣ፀሀይም የለም፣ ሙቀትም የለም፣ ቅዝቃዜም የለም፣ ለምን የሚለዉ ቃል ግን ሃሳቤ ላይ አለ፤
ለምን?እንዲህ ሆነ? ለምን አልዘነበም? ዘንቦስ ለምን ህመሜን አላጠበም? ለምን ፀሀይ ጠለቀች?በሙቀቷስ የበረደዉን ሆዴን ለምን አታሞቅም? ለምን አልቀዘቀዘም? ቀዝቅዞስ ጥዝጣዜዉ ከድብርቴ አያነቃኝም? ለምን? ለምን? ለምን?.....ጠያቂ እንጂ መላሽ በሌለበት መላጣ አስፋልት እኔ እና እኔ እየተቦቃቀስን ወደ ገደላማ ስፍራ ሄድን፤
ድንገት ቀና አልኩኝ፤ ሰማዩ ደብሮታል፣ ያልነበረችዋ ፀሀይ ጀምበሯን ወጣ አድርጋ በሰማዩ ቁርጭራጭ እየተሸፈነች ጫፏ ብቻ ይታያል።

"ምነዉ ተፈጥሮም አሽሟጠጠችብኝ? አሁን እቺ ፀሀይም በአቅሟ የኔን ነፍስ መምሰሏ ምን ይሉታል? ለነገሩ አራጋቢዉ ካለ አቃጣዩም ሞልቷል" አልኩ የኔ በማይመስል ኑሮ በመረረዉ ሸካራ ድምፅ....."

**************
"ድርግም" አደረኩት አይኔ ያለ ልክ ከቀኝ ወደ ግራ ከላይ ወደ ታች ይጉረጠረጣል፤ በጣም ግራ ገብቶኛል ከዚህ በላይ ማንበብ አልቻልኩም፤
የማነባት(ሲጠብቅም ሲላላ) ደራሲው በሆነ መመርመሪያ መሳሪያ ሙሉ ታሪኬን እየተከታተለ ሳያዛንፍ የፃፈ መሠለኝ፤ የራሴዉ ሀሳብ ለራሴ ገርሞኝ ሆ! አስባለኝ!

ገፀባህርይ ላይ ያለችዉ "ማክዳ" ትርጉሙን ባላዉቀዉም ማ-ክዳ ሆነልኝ፤ ማ?-ክዳ? እንደዚህ ተቀጣች? ይሄ ሁሉ ታመመች? እንዴትስ ማንም ስብራቷን ሊጠግንላት አልዳዳዉም?
ስብራትን፣ ህመምን፣ ስቃይን....ለሰዉ ሲያጋሩት ይቀላል የሚባል ነገር አይገባኝም።(መብቴ ነዉ) ምክንያቴን ልንገርህ?
ስንት ያስጨነቁኝ ህመሞች እሾኾች ነፍሴን ሲወጉት....አቅላይ ተብዬጋ ሲቀርብ ቀልድ መሠለ? ስንቱስ "አይዞን" በሚል አጭር ቃል ተዳፈነ?....ስለዚህ አይቀልም፤ ለሁለተኛ ወገን መንገር ልክ እንደ "ኡፍፍፍ" እንደ ማለት ነዉ። ትንፋሽ እንጂ ብሶት አያወጣም አለቀ!
"Life is resycle" ከሆነ ታመህም ድነህም ተሹመህም ተሽረህም ትኖራለህና ስትታመም....አጋጣሚዉን ጠብቀህ አይንህ "ለነገህም አትል" እስኪልህ አልቅሰህ አፍንጫህ "ምነዉ ስራዬን ባታበዛዉ?" እስኪልህ ተነፋርቀህበት፣ ሰዉነትህ ተንዘፍዝፎ በእንባህ ሲታጠብ ነፍስህን ባያክማት እንኳ ፋታ ይሰጥሃል።

እንባህን ጥርግርግ አድርገኸዉ
"እስቲ ጥርስህን" ተብለህ እንደምታሳየዉ ከንፈርህን ካላቀቅክ በቃ ደስተኛ ነህ አሉ!(ጥልሳም አለች ሚሚ)

አንተም ትላለህ አዎን ደስተኛ ነኝ። ነፍሴ የቤትህ መጋረጃ አይደለምና ገልጠህ አታየዉም። ግን እንድታየዉ የፈቀድኩልህን ጥርሴን ብቻ ስለማሳይህ ደስተኛ ነኝ። ...የነፍሴን ዜማ በራሴዉ መድረክ እያዜምኩ፥ ዝናን (ጥንካሬ) አተርፋለሁ።
በቀሪው ደግሞ "ኢኝኝኝኝኝ"እልሃለሁ



………… ፈትሒያ

ስለ-ፅሁፉ ሃሳብ አስተያየት ካላቹ ፦ @Fethetulletiya
ይጠቀሙ………………


ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯