Get Mystery Box with random crypto!

💖 ዕፀጳጦስ 💖

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsepatos — 💖 ዕፀጳጦስ 💖 ዕ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsepatos — 💖 ዕፀጳጦስ 💖
የሰርጥ አድራሻ: @tsepatos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.87K
የሰርጥ መግለጫ

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ዕፀጳጦስ።
👇ተቀላቀሉን👇
https://t.me/tsepatos
ለማንኛውም ሃሳብ፣አስተያየት
በ👉 @Elaa24u @Te_best 👈

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-08 19:49:24 እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሴት የተወለደ ልጁን ሊልክ የዘመኑ ፍጻሜ ቀረበ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር።
ቀድመው ልጅ ቢወልዱ ኖሮ ይህችን የፍጥረት ደስታ የሆነች ልጅ አይወልዱም ነበር:: የእርስዋ የልደት ቀን የፍጥረት ደስታ ቀን ነው::

ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ መድኃኒት ከሆነ ዛሬ የመድኃኒቱ ሙዳይ የተገኘችበት ዕለት ነው::

ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል።

እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
1.1K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:42:57 ✞በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን✞

እንኳን ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን አሜን።

ሰኔ 30

በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው ሐዋርያው ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው አንገቱ ከተቆረጠ በኃላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመት በሳውዲአረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት
አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።ጨካኝ ሄሮድስ የቤቴልሔም ህጻናትን ሲጨፈጭፍ መጥምቁ ዮሐንስ ከአናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ ኤልሳቤጥ በጣም አርጅታ ነበር ያን በርሃ ታዲያ እንዴት ቻለችው ያውም ልጅ አዝላ ልጅ ተሸክማ ረዳት ሳይኖራት ብቻዋን አባቱ ዘካርያስ በምኩራብ በመሰዊያው ፊት ልጅህን አምጣ ብለው አንገቱን ቆርጠው ገደሉት። ኤልሳቤጥም ሲና በርሃ ላይ ሞተች ህጻኑ ዮሐንስ ብቻውን ቀረ የእናቱን በድነ ስጋ አቅፎ አለቀሰ ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያይ ሁሉን የሚመረምር ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን እናቴ ሆይ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በበርሃ አርፋለች እንቀብራት ዘንድ እንሂድ አላት ደመና ጠቅሰው ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትለው ሄደዋል ገንዘውም ቀብረዋታል ከዚህ በኃላ እመቤታችን ልጄ ወዳጄ ሆይ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው የለም እናቴ እርሱ እዚው ይቆያል መንገዴን ጠራጊ ነው ኑሮው በዚሁ በርሃ ነው ጊዜው ሲደርስ ወደ ዮርዳኖስ ይመጣል ያጠምቀኝማል ያኔ አንድነቴ ሶስትነቴ ይገለጣል አላት ትተውት ተመለሱ ከመሞቱ በፊት እናቱ ያሰፋችለትን የግመል ቆዳ አገልድሞ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በበርሃ ኖረ 30 ዓመት ከ 6 ወር ሲሆነው “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ከበርሃ ወጣ ሉቃ 3፥3። "እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 11፤11። ይህ የጌታችን ምስክርነት ነው።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
1.6K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:36:38 ባለ ውለታዬ
ሊቀ.ቴድሮስ ዮሴፍ
===============
ባለውለታዬ /2/
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
አዝ------------------------------//
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አደርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘኝ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /2/
አዝ------------------------------//
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
አንድ ወርድ ከዛፉ አዘዘኝ ጌታዬ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /2/
አዝ------------------------------//
ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አያቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሠላም ሂድ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ /2/
አዝ------------------------------//
የማምነውም አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ሥራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ /2/
1.2K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:33:15 <<ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ>>
ማር 13፡18


ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው

#ክረምት የብሉይ ኪዳን ዘመን ምሳሌ ነው

የክረምት ገበሬ ጠዋት ጾሙን ይወጣል
ቀን ከላይ ዝናም እየወረደበት ከታች ጭቃ እየሆነበት ሲሠራ ውሎ ማታ እራት ጎመን ይቀርብለታል
ድካምና ረኃብ
ፍርሃትና ስቃይ ይፈራረቁበታል!
ነቢያት በዘመነ ብሉይ እንዲሁ ነበሩ።
ያለ ልጅነት ወጥተው ያስተምራሉ ፤ትንቢት ይናገራሉ
ሲመሽ ማታ (ሲሞቱ) በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደሲኦል ይወርዳሉ(የጎመን እራት)!


#ክረምት የቃል ኪዳን መገለጫ ነው

ክረምት በብሉይም በሐዲስም ከተደረጉ ኪዳናት ጋር ተያይዞ ይገለጻል
በተለይም ቅዱስ ያሬድ ክረምትን ከኖኅ ኪዳን ጋር እያነጻጸረ የገለጸው የዜማ ድርሰት አስደናቂ ነው
"ያከርም በበዓመት ተዘኪሮ ዘመሐለ ለኖኅ ገብሩ" የሚያስደንቀኝ ገለጻ ነው! (ዘፍ 8፥22)

#በክረምት፦

መብረቅ
ነጎድጓድ
በረድ (በረዶ)
ማዕበል ሞገድ አለ

ሰማዩ ይጠቁራል
ደመናው ይከብዳል
መሬቱ ይላላል
ወንዙ ይሞላል
ዘመድ ከዘመድ ሳይጠያየቅ ይከርማል
ስለዚህም በዚህ ወቅት ወርኀ ክረምቱን በሰላም እንዲያሳልፍልን ጸሎት/አስተምሕሮ ይደረጋል
ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው የአስተምህሮ ጊዜው የዚሁ አካል ነው።

ዝናሙ ዝናመ ምሕረት
ጠሉ ጠለ በረከት
ነፋሱ ነፋስ ምሕረት እንዲሆን አስተብቁዖት(ምልጃ) ሊደረግ ይገባል።

#ክረምት የምጽአተ እግዚእ ምሳሌ ነው
ማቴ 24፥27

ክረምት የጌታ መምጣት የዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ሆኖም ይነገራል
በክረምት ከሚሰማው ነጎድጓድ በላይ የሆነ ነጎድጎድ በዕለተ ምጽአት ይሰማል
ጌታም እንደ መብረቅ ብልጭታ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ያለ ወሰን በምልዓት በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ይገለጣል
ይህን እያሰብን በጎ እንድንሠራ ክረምት አስፈሪ ምልክቶች ይታዩበታል!
ምልክቶቹም አቅማችንን አውቀን፣ ተፈጥሮ ከእኛ አቅም በላይ መሆኑን ተገንዝበን ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ የሚያሳስቡ ናቸው!

#በዚህ ክረምት መርከብ መሥራት በመርከቡ መቀመጥ ያስፈልጋል

#መርከቡም፦
ሃይማኖት
ቤተ ክርስቲያን
ጸሎት
ንስሐ
በጎ ሥራ ነው!

"ግበር ታቦተ በዘትድኅን" የምትድንበትን መርከብ ሥራ!
አምላካችን እግዚአብሔር ክረምቱን በሰላምና በጤና ያሳልፈን!!!

አሜን!
1.4K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:47:35 ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::
https://t.me/zmaremelaekt
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 27 2013 ዓ.ም
1.6K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:04:34 ከሰይጣን ዓላማዎች አንዱ፦
ወደ ክርስቶስ የሚያሳዩ ምልክቶችን ማጥፋትና እርሱን የሚያሳስቡ ሕያዋን ሐውልቶችን ማፍረስ ነው፡፡
==========================
★ 2ቆሮ. "በሰይጣን እንዳንታለል ፣
የእርሱን አሳብ አንስተውም"

ሰይጣን በእባብ ገላ ተሰውሮ ክፋት ያላወቁትን አዳምንና ሔዋንን አታሏቸዋል፣ ያላቸውንም ሁሉ አሳጥቶ ባዶ አስቀርቷቸው ነበር ፡፡
እንደ ተስፋው ቃል የአዳምና የሔዋን ዘር የቅድስት ፣ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ፍጹም ሰው ሆኖ ምንም የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት በምድረ በዳ ከሰይጣን የቀረበለትን ፈተና ሁሉ ድል አደረገ፡ ይልቁኑ ሰይጣን ራሱ ተሸንፎ አፎሮ ባዶው ተመለሰ እንጂ፡፡

እኛም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆን የእግዚአብሔር ልጆች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ነንና በሰይጣን አንታለልም ፣ ከሰይጣን ተንኮል የሚበልጠው የመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በውስጣችን ስላለ፡፡
=========================
✿ በሰይጣን ወጥመድ ፈጥነው
የሚወድቁት እነ ማናቸው?

1ኛ ወደ እወነት ያልመጡ ፍጥረታውያን ሰዎች፡፡
2ኛ በክርስትና ትምህርት ሕጻናት የሆኑ ወይም ያልበሰሉ ክርስቲያኖችን ናቸው፡፡
ማቴ 13፥18-23
===========================
★ የሰይጣን መንገድ ፦

ፍጥረታውያን ሰዎች ጭራሹኑ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ዘለዓለም ሕይወት እንዳያስቡ ፣ ራሳቸውን እንዳያውቁ እንዲሁ እንደ እንስሳት እንዲኖሩ ዐይነ ልቡና ቸውን ያሳውራቸዋል ፣ ያደነዝዛቸዋል ያደነቁራቸዋል፡፡

ይህ እኳ ባይሳካለት ከክርስትና ውጪ የሆነ ክርስቶስን የሚጠላ ሃይማኖት እንዲመሰርቱ ያደረጋቸዋል ይህም በተዘዋዋሪም እርሱን እንዲያመልኩ ማለት ነው ፡፡

ስለ እግዚአብሔር ፣ ስለ ዘለዓለም ሕይወት ፣ ስለ ክርስቶስ መምጣት ፣መከራ ፣ሞትና ትንሣኤ ማሰብና መናገርን እንደ ሞኝነት እንዲቆጠሩ፣ እንዲፀየፉት ያደርጋል፡፡

ወደ ኢየሱስ ክርስቶሰቶ ሊያመለክቱ የሚችሉ ምልክቶችን ፣ እርሱን የሚያሳስቡ ነገሮችን ሁሉ ማስረሳት ፣ ማጥላላትና ማጥፋቶ ነው፡፡

በአንድ ወቅት የኢየስስ ክርስቶስ ስም በምድር ላይ ዳግመኛ እንዳይነሣ ፣ በይሁዳና በአይሁድ ልብ አድሮ ንጹሁ ክርስቶስ ለኃጢአተኞ ተላልፎ እንዲሰጥ ፣ ዘግናኝ መከራ እንዲቀበል ፣ ከሞት ሁሉ የከፋውን የመስቀል ሞት እንዲሞት አደረገ፡፡

ክርስቶስ ግን መሞቱ ለመነሣት ነበርና አስቀድሞ እንደሚነሣ በተናገረው መሰረት ሙስና መቃብርን አጥፍ መግነዝ ፍቱልኝ ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል " ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም" ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረውየይሁዳው አንበሳ ሞትንና ሲኦልን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ ሐዋ 2 ፥ 24

ከበፊቱ ይልቅ የትንሣኤው ዜና
ያስደነገጣቸው ሰይጣንና አይሁድ የትንሣኤውን ብርሃን በገንዘብና በሐሰት በተፈጠረ ተረት ለመቅበር ሙከራ አደረጉ፡፡

ይኸውም ለመቃብር ጠባቂዎቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት "እኛ ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ" በማለት (ማቴ.28 ፥13) በሐሰት ትርክት የትንሣኤውን መልካም ዜና ለመቅበር ሞከሩ።

ሰይጣን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰዎች የክርስቶስን የመምጣቱን ፣ የመከራውን ፣ የሞቱንና የትንሣኤውን ዋና ዓላማ እንዳያያዩና እንዳይረዱ የሚጠቀመው በዋናነት ገንዘብንና በገንዘብ ፍቅር የሰከሩ የሐሰት አሰተማሪዎች ነው፡፡

★ሰይጣን ሰዎች ክርስቶስን እንዳያዩ የትኛውንም መጋረጃ ይጠቀማል ፣ ወደ ክርስቶስ እንዳይደርሱ መንገዶቹን ሁሉ ለመዝጋት ሰከንድ ሳያባክን ይሞክራል፡፡

★ የሰይጣን ትልቁ ፈተና ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዳያወሩ አይደለም አጥብቆ የሚታገለው ሰዎች ክርስቶስን በትክክል እንዳይረዱ ፣ እንዳያዩ ፣ በእምነት ፣ በንስሓ ወደ ክርስቶስ እንዳይቀርቡ ነው፡፡ ማቴ.7 ፥21

> ገላ .3 ፥1 "የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ከዐይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር ፣ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማነው? "

ለዚህ ጥያቄ መልሱ ከሰይጣን ውጪ ማን ሊሆን ይችላል!? የሚል ነው ። በዐይናቸው ፊት ያለውን ማየት እንዳይችሉ አደንዝዟቸዋል፡፡

★ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ጥቂት መረጃ ስላገኙ ብቻ ክርስቶስን እንዳወቁ እንዲሰማቸው አደረጋቸው ይህ አንዱ የሰይጣን ማደንዘዣ ወይም አዚም ነው፡፡

★ አንዳዳንዱን ደግሞ በየመንገድ ዳርና በተመቻቹ ፣ ባሸበረቁ አውደ ምሕረቶች ስለ ኢየሱስ ስለተናገሩ ብቻ ወንጌል እንደሰበኩ እንዲያስቡና በዚህ ረክተው አርፈው እንዲቀመጡ በውዳሴ ከንቱ ጠላልፎ እግረ ልቡናቸውን ሽባ አድርጎ አስቀመጣቸው፡፡

በየ አውደ ምሕረቱም ሆነ ባገኘነው አጋጣሚ ሰዎች ክርስቶስን አምነው ፣ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ማድረግ መልካም ቢሆንም ይህ ብቻውን ግን ወንጌል መስበክ አይደለም፡፡ ወንጌል ሕይወት ነው፡፡ ክርስቶስ መገለጥ ያለበት በአንደበታችን ብቻ ሳይሆን በሕይወታችንም ነው፡፡
★ላልዳነውና እየጠፋ ላለው ዓለም የክርስቶስን ፍቅርና ማዳን የምንገልጠው ባማረ አንደበትና ልብስ ሳይሆን በፍቅርና በቅድስና በተሞላ ሕይወት ነው፡፡

★ ሰይጣን ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አንንዳይመለከቱ ምልክቶችን ያጠፋል ፣ ክርስቶስን የሚያሳስቡ ሕያዋን ሐውልቶችን ያፈርሳል ካልን ፦

እስኪ እነዚህ ምልክቶችና ሕያዋን ሐውልቶች ምንድናቸው የሚለውን እንመልከት ..........(ይቀጥላል)



24/10/2014 ዓ/ም
1.6K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:15:46 ተወዳጆች ሆይ በመንፈሳዊው ህይወታችን
:ስለ ሰላም ዋጋ የምንከፍለው ፣ወንጌል የምንሰብከው፣ መከራ የምንቀበለው፣ የራሳችንን ክብር በሰዎች ዘንድ ለመገንባት ነው? ወይስ በወንጌል ስም ታዋቂ ለመሆን?
ወይስ በኛ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ብርሃን አለምን ለማሳየት?
በእውቀት ልካችን ወንበር ለማደላደል?
ወይስ ዓላማችን ሰላምን በህዝብ ልብ ውስጥ ለማስረጽ ነው?
ስለክርስቲያኖች መገለጫ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል።
''በእኔ ሳላችሁ ... በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ... '' ዮሃ 16፣13
ደግሞም
''በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ....።'' ይላል።
ማር 13;13
አይገርምም በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ይላል:
ወንድሜ ግን አንተ ስለስሙ ትጠላ ይሆን? የተጠላሃውስ በየትኛው ግብርህ ነው? በርባንነትህ ነው? ወይስ በህያው ብርሃን ስም አይን ስላበራህ?
የተጠላኸው ሠላምን የተጠማች አለም የህይወትን ውሃ ከሆድህ ስላፈለክላት? ወይስ ስለ እኔነትህ ውበት ብቻ እየተናገርክ?
የተጠላኸው በምድር ስላለችው የእግዚአብሔር መንግስት ተልዕኮ ለመፈጸም አቅም አጥተህ ነው? ወይስ አንደበትህ ስለተሳሰር ይሆን?
ወንድሜ አንተን አለም ስትጠላህ ስንፍናህ ሸክም ሆኖባት ነው። ስንፍናህን የእግዚአብሔር ቸርነቱ ተጨምሮበት ፣ በትጋትህና በትምህርት ልትለውጠው ትችላለህ። ይሄ ግን የሰማዩን በር አይከፍትልህም። ሸክምህን ተሸክሞ ነጻ ስላወጣህ እውነት የተጠላህ ጊዜ ግን በምድርም በሰማይም ባለጸጋ ነህና በእግዚአብሔር ዘንድ ትከብራለህ።ደስ ይበልህ፡፡
ቃሉ ህያው ፣ ዘመንም ተሻግሮ የሚሰራ ነውና በእውነት ደስ ይበልህ፡፡ አለም የምትመስልህና የምትወድህ ከሆነ እንደ ማስቲካ አኝካ ሳትተፋህ አስቀድመህ በሞተልህ ክንድ ተደገፍ።ምንም ብትጠላህ ጣዕሟ አንተ ነህና። በመውጣት በመግባት ዘመንህ ሁሉ የሰማይ ቤትህን ለመስራት እሩጥ።
መከራም የሚበረታው ስለ ወንጌል ስለ ስሙ መከራ በሚቀበሉት ላይ ነው። ስለዚህም የማዕዘኑ ራስ ዲንጋይ ስለሆነው ክብር ፣ ስለ ሃይማኖት የሚከፈል ዋጋ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን፣ የክብሩም ተካፋይ ያደርጋል፡፡ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብራለች እንዳለች እመቤታችን። ለመክበር እግዚአብሔርን በህይወትህ አክብር። እግዚአብሔር ውለታ አይረሳምና ብድራትንም ይከፍላል። ስሙ ቡሩክ ይሁን።አሜን፡፡
2.0K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:49:32 #ኪዳነ_ምህረት_እናቴ

ኪዳነ ምህረት እናቴ
ሚስጥረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሰአይወጣ ሳልነግርሽ /2/

#አዝ
አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውሃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ በአንቺ ታበሰ /2/

#አዝ
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልርሳሽም እናቴ /2/

#አዝ
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የእኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደ ሚፈፀም አውቃለሁ
ሁሉን በግዜው አያለሁ /2/

#አዝ
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባየ ቀድሞ ዝም አልኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂኝ /2/
1.8K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 22:36:24 https://www.facebook.com/117159900989698/posts/122630307109324/?flite=scwspnss
1.9K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 13:22:39 https://www.facebook.com/117159900989698/posts/128282659877422/?flite=scwspnss
1.9K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ