Get Mystery Box with random crypto!

💖 ዕፀጳጦስ 💖

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsepatos — 💖 ዕፀጳጦስ 💖 ዕ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsepatos — 💖 ዕፀጳጦስ 💖
የሰርጥ አድራሻ: @tsepatos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.87K
የሰርጥ መግለጫ

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ዕፀጳጦስ።
👇ተቀላቀሉን👇
https://t.me/tsepatos
ለማንኛውም ሃሳብ፣አስተያየት
በ👉 @Elaa24u @Te_best 👈

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-15 21:48:23 ☞ወደ ዋላ ተመለስና ታሪክ አጥና ፦

ዮሴፍን ወንድሞቹ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን በጌታው በጲጥፋራ ቤት ከፍ ከፍ አደረገው።

በጌታው ሚስት ተንኰል ወደ ወኅኒ ቤት በተወረወረ ጊዜም ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከወኅኒ
ቤት አውጥቶ በባዕድ ሀገር ገዥ አደረገው።

ሙሴ በሕፃንነቱ ወንዝ ዳር ሲጣል ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከተጣለበት አንሥቶ በፈርዖን ቤተ
መንግሥት፥ የንጉሥ የልጅ ልጅ ተብሎ እንዲያድግ አደረገው። (ዘፍ 39፥1-23፤ 41፥1-50።)

ብላቴናው ዳዊት በኃያሉ በጐልያድ ፊት በቆመ ጊዜ ሰው አልነበረውም፥ ከወንጭፉ በስተቀር መሣሪያም አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ጐልያድን በአንዲት ጠጠር ግንባሩን ፈርክሶ ጣለለት።( ዘጸ 2፥1-10)

ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ ተማርከው ወደ ባቢሎን ሲወርዱ ሰው አልነበራቸውም፥ እግዚአብሔር ግን ጥበብን ሰጥቶ በባቢሎን ጠቢባን እና አውራጃዎች ላይ እንዲሾሙ አደረጋቸው። (1ኛሳሙ 17፥35-55።)

በሰዎች ተንኰል፥ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ ዕቶነ እሳት፥ ዳንኤል ደግሞ ወደ አናብስት ጉድጓድ በተጣሉም ጊዜ
ሰው አልነበራቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ቅዱስ ሚካኤልን እና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አዳናቸው። (ዳን 1 እና 2፤ )

አልዓዛር በሞት ተይዞ፥ ተገንዞ፥ ወደ መቃብር በወረደ ጊዜ ሰው አልነበረውም፤ ጌታ ግን ከመቃብር አወጣው። (ዳን 3፥24፣6፥6 )

ቅዱስ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታስሮ ወደ ጨለማው ወኅኒ ቤት ሲወረወር ሰው አልነበረውም፥ ጌታ ግን መልአኩን ልኰ ከወኅኒ ቤት አወጣው።(ዮሐ 11፥28-34)

ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወደ ወኅኒ ቤት ተወርውረው፥ ከግንድ ጋርም አጣብቀው ሲያስሯቸው ሰው አልነበራቸውም። (የሐዋ 12፥1-11)

►በመንፈቀ ሌሊትም ይጸልዩ፥ እግዚአብሔርንም በዜማ ያመሰግኑ ነበር።

►ጌታም የእግር ብረቱን፥ የእጅ ሰንሰለቱን ፈትቶ፥ በሩንም ከፍቶ አውጥቶአቸዋል።(የሐዋ 16፥16-30።)

<> <> <> <> <>

☞ታዲያ ወዳጄ ይህ ላንተም ነው ። ይህ ህግ ዛሬም በህይወትህ ዉስጥ ይሰራል ። ብቻህን አይደለህም ።

ዘመድ ላይኖርህ ይችላል ታማኝ ጓደኛ ላይወጣልህ ይችላል

እናት ወይም የስጋ አባት ላይኖርህ ይችላል

ግን ከሁሉ በላይ የሆነውን ወዳጅ ፣ ዘመድ ጓደኛ የሚተካ ፤ ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ የሆነ ወዳጅ "አባት" አለህ!! በዚህ ኩራት ይሰማህ !!!

ክብር ምስጋና ለዚህ ጌታ ለአባታችን ለፈጣሪያችን ለአምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን !!(አሜን)

[☞ወስብሐት ለእግዚአብሔር☜
893 viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:59:16 የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚኽ እግዚአብሔር ስለ እመቤታችን ጥንታዊ የልደቷን አመጣጥ በየጊዜው ምልክት እንደሚሰጥ ልብ አድርገን ማስተዋል ይገባናል) በማለት አብራርተው ተርጒመዋል፡፡

❖ ሊቁ አባ ሕርያስቆስም በቅዳሴው በቊ ፴፪ ላይ "ተናግዶቱ ለአብርሃም" (የአብርሃም እንግድነቱ አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን ጠቅልሎ የገለጠውን ይኽነን ድንቅ ምስጢር፤ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ በስፋትና በጥልቀት፡-

"ወዓዲ ኀይመት ዘአብርሃም ዘውስቴታ ተአንገደ እግዚአብሔር አኮ ከማሁ ዘኮነቶ ምጽላለ በእንተ ምዕር አላ ኮነቶ እመ ወተከድነ ሥጋሃ ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ" (ዳግመኛም እግዚአብሔር (በሦስትነት) በዕንግድነት ያረፈባት የአብርሃም ድንኳን አንቺ ነሽ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ መጠለያን፣ መጠጊያን የኾነቺው አይደለም፤ እናትን ኾናው ሥጋዋን ተዋሕዶ ከመለኮቱ አንድ አደረገው እንጂ) በማለት በአብርሃም ድንኳን ብትመሰልም እንኳ ክብሯ ከፍ ያለ፤ ለዘላለም የአምላክ ማረፊያውና እናቱ መኾኗን አብራርቶ ገልጧል፡፡

❖ ሊቅነትን ከንግሥና ጋር ያስተባበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሥላሴ መጽሐፉ ላይ፦
"ኦ ብእሲ ዘትትከሓድ አይኑ ዕለት ለአግዚአብሔር ሰገዱ ሎቱ ምስለ መላእክቲሁ በዕሪና እምነ ኩሉ ፍጡራኒሁ..." (ሥላሴን የምትክድ አንተ ሰው ሆይ ከፍጡሮች ወገን በመላ እግዚአብሔርን ከመላእክቱ ጋር በአንዲት ዕሪና የሰገዱለት በማናቸው ዕለት ነው? በማናቸው ዕለት እግዚአብሔር ከፈጠራቸው መላእክቱ ጋር ተካክሎ እግሩን ታጠበ? በማናቸው ዕለት በሰው መጠለያ በታች ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ ተጠለለ? በማናቸው ዕለት ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ እግዚአብሔር በላ? በማናቸው ዕለት ከአዳም ልጆች ወገን ሰው ወደ ፈጣሪው በለመነ ጊዜ መላእክቱ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ተካክለው እንዲኽ አድርግ መቼ አሉ? አንተ ሥላሴን የካድኽ ከሓዲ ፍጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር በመተካከል እንዲሰገድላቸው ለምን ታመጣቸዋለኽ? ፈጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር ተካክለው በአብርሃም ቤት እንደተጠለሉ፤ እግራቸውን እንደታጠቡ፤ ዐብረው እንደበሉ አድርገኽ ለምን ታስተካክላለኽ? አንተ ከእኛ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የኾንኽ ክርስቲያን አንዱ እግዚአብሔር ነው፤ ኹለቱ መላእክት ናቸው አትበል) በማለት አስፍቶ ይጽፋል፨

❖በቤተ አብርሃም የገቡ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዘወትር በቤተ ልቡናችን ውስጥ ግቡልን፨❖
[ለበለጠ ምስጢር "መልክአ ሥላሴ ንባቡና ትርጓሜው" መጽሐፌን ያንብቡ]፨
910 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:59:16 ❖የሐምሌ ሥላሴ በዓል ድንቅ ምስጢር❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖር በሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ዘፍ 18:1-10)፡፡ ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤ በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ።

❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰለዚኽ ነገር በድጓው ላይ፦
"ዮም አብርሃም ሰገደ ለፈጣሪሁ
ሶበ ነጸረ ዋሕደ በሥላሴሁ"
(ዋሕደ ባሕርይ የኾነ እግዚአብሔርን በአካላዊ ሦስትነቱ ባየው ጊዜ አብርሃም ዛሬ ለፈጣሪው ሰገደ) ይላል፨

❖ የተገለጡለት ሰዓቱ ቀትር (ስድስት) ሰዓት በዕንጨት ሥር በሰው አምሳል መኾኑ ቀደምት ሊቃውንት ሲያራቅቁት በአብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በራሱም ፈቃድ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የአብርሃምን ባሕርይ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ በስድስት ሰዓት በዕንጨት መስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የሚሰቀል መኾኑን ያጠይቃል ይላሉ፨

❖ ይኽነን ይዞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሕማማት ሰላምታው፦
"ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ
ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ
ተሰቀልከ ከመ እቡስ ስብሐት ለከ"
(ምስጋና የተገባኽ ጌታ ድርስ በሚባል የዛፍ ዐይነት ሥር በስድስት ሰዓት ለአባታችን አብርሃም ቀድሞ የተገለጥኽለት ክርስቶስ ሆይ እንደ በደለኛ ተሰቀልኽ) ይላል፨

❖ ከዚኽ በኋላ "አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…" በማለት ተናግሯል፡፡
"በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ" ብሎ አንድነታቸውን፤
"ውሃ ይምጣላችኍ፣ ዕረፉ፣ ትኼዳላችሁ" ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

❖ ይኸው ሊቅ ያሬድ ይኽነን ይዞ በድጓ ላይ፦
"ይቤሎሙ ዮም አብርሃም ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አመጽእ ማየ ወአሐጽብ እገሪክሙ ወእርከብ ሞገሰ በቅድሜክሙ" (አብርሃም ዛሬ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ባለሟልነትን በፊታችሁ አገኝ ዘንድ ውሃን አምጥቼ እግራችኹን አጥባለሁ አላቸው) ይላል

❖ ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ
"አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ"
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፦

❖ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
"እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት"
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡

❖ ከዚኽም ምስጢር የተነሣ አብርሃምም ሳራን “ሦስት መስፈሪያ የተሠለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ” በማለት የተገለጸለትን የሦስትነት የአንድነት ምስጢርን አጒልቶ ተናግሯል፡፡

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይኽነን ይዞ በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
"ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ነገሥተ ሰብዐቱ አብያት
እለ በላዕክሙ ውሣጤ ኀይመት
አሐደ ኅብስተ ትሥልስት"
(ከሦስት መስፈሪያ ዶቄት የተጋገረ አንድነት ያለው ኅብስትን በድንኳን ውስጥ የተመገባችሁ የሰባት ቤቶች (ሰማያት) ነገሥት ሆይ ለእናንተ መገዛት (ምስጋና) ይገባል) ይላል፨

❖ አብርሃምም በደስታ ኾኖ መዐር፣ ወተት፣ ያዘጋጀውን ጥጃ አመጣላቸው፤ እነርሱም ደስ ይበለው ብለው በግብር አምላካዊ ተመግበዋል፤ መላእክት ሎጥ ቤት፤ ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት ቤት ተመገበ የተባለው አንድ ነው፤ እሳት ቅቤ በላ እንደማለት ብቻ ነው፨

❖ ይኸውም ወተትና መዐር መመገባቸው ኦሪትን ወንጌልን መሥራታቸውን ሲያጠይቁ ነው፤ መዐር የኦሪት፤ ቅቤ የወንጌል ምሳሌ ነው፨ ማር ለጊዜው ሲይዝ የሚለቅ አይመስልም፤ ግን ይለቃል ኦሪትም ስትሠራ የምታልፍ አትመስልም ነበር ግን በኽዋላ ዐልፋለች፨ ወተት የወንጌል ምሳሌ ነው፤ ይኽ ወተት ለጊዜው የሚለቅቅ ይመስላል በኽዋላ ሲያጥቡት አይለቅም ወንጌልም ለጊዜው ስትሠራ የምታልፍ ትመስል ነበር፤ በኽዋላ ግን ጸንታ የምትኖር ኾናለችና በማለት መተርጉማን ያራቅቁታል፡

ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ወልድ አብርሃምን "የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለኍ፤ ሚስትኽ ሳራም ልጅን ታገኛለች" በማለት ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ወልድ ከቤተ አብርሃም ከተገኘች ከእመቤታችን የመወለዱንና፤ በሳራ የተመሰለች ወንጌል ምእመናንን እንደምታስገኝ በምስጢር ገልጾለታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም አካላዊ ቃል በሰጠው ተስፋ መሠረት ከነገደ አብርሃም የመወለዱን ነገር ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ "በሕይወታቸው ኹሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ኹሉ ነጻ እንዲያወጣ፤ በሥጋና በደም እንዲኹም ተካፈለ፣ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" በማለት ገልጾታል (ዕብ ፪፥፲፭-፲፮)፡፡

❖ ይኽቺ ሥላሴ የገቡባት ኀይመተ አብርሃም (የአብርሃም ድንኳን) የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ይኸውም ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ኹሉ፤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም፤ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመዋሐድ ዐድረዋል (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ በመኾኑም አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ብቻ ናት፡፡

❖ ሊቁም በነገረ ማርያም ይኽነን ምስጢር ሲገልጽ "ወይእቲ ኀይመት ትትሜሰል በድንግል ወዕደው አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሙንቱ፤ አብ አጽንኣ፣ ወወልድ ተሰብአ እምኔሃ፣ ወመንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ከመ ትጹር አምላከ በከርሣ" (ያቺ ድንኳንም በድንግል ትመሰላለች፤ ሰዎቹም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ አጸናት፣ ወልድም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል አምላክን ትሸከም ዘንድ ለያት) በማለት ተርጉሞታል፨

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰላምታ መጽሐፉ ላይ መጽሐፉ፦ "ኀይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ፤
ዘኮንኪ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ"
(እንደ ጥላ የኾንሽ የአባት አብርሃም ድንኳን ሰላምታ ይገባሻል) በማለት አመስግኗታል፡፡

❖ ይኽ አብርሃም የተቀበለውን የተስፋ ቃል ሊቃውንት ሲተረጒሙት "ኦ አኃውየ በይነ መኑ እንከ ዘይቤ እግዚአብሔር ለአብርሃም አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ አኮኑ እግዝእትነ ማርያም ይእቲ ዘወፅአት እምነ ሥርው ለአዳም ..." (ወንድሞቼ ሆይ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደዛሬው ኹሉ ወደአንተ ተመልሼ እመጣለኍ ያለው ስለማን ይመስላችኋል? ከአዳም ሥር ወጥታ፤ ከኖኅ አብራክ ተገኝታ፤ ወደ አብርሃም አብራክ ልትከፈል፤ ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ተገኝተው፤ ከአብርሃም ዘር ከእመቤታችን
736 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:56:22 ስሉስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ቤት የገቡበት እና የአብርሃምን ጥያቄ የመለሱበት ለችግሩ መፍትሔ የሰጡበት ታላቅ በዓል ነው
እንኳን ለቅድስት ስላሴ ዓመታዊ ክብረበዓል አደረሳችሁ

ስላሴና አብርሃም የሚተዋወቁበት ምስጢር

የአባቱን እና የእናቱን አገር ጥሎ እግዚአብሔርን ተከትሎ
ከወጣ በኋላ በብዙ መከራና ፈተና ላይ እያለ ነበር ያን ሁሉ መከራና ውጣውረድ በእግዚአብሔር ስም ይቀበል ነበር

ዮሐ 15 (14፤ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።ብሎ እንደተናገረ ሐዋርያው

እግዚአብሔር አብርሃምን የሚያውቀው እኛን እንደሚያውቀን አይደለም ምን አልባት እኛን የሚያውቀን ስንበላ ስንጠጣ ስንጫወት ስንዝናና ወዘተ ሊሆን ይችላል

እግዚአብሔር አብርሃምን የሚያውቀው ጣዖትን ሰብሮ ከቤተሰቡ ተለይቶ ከካራን ሲወጣ ነው የእንግዳ ቤት ሰርቶ እንግዳ ሲቀበል የእንግዳ እግር ሲያጥብ ነው

በእየቀኑ ኃጢአቱን እያሰበ መስዋዕት ሲያቀርብ ነው

በመጨረሻም ይህን አገልግሎቱን ያየ ሰይጣን እንግዶች ወደቤቱ እንዳይመጡ ሲከለክልበት አብርሃምም ያለ እንግዳ ስለማይመገብ እንግዳ በማጣት አዝኖ ተክዞ ሳለ
እግዚአብሔር በአንድነት በሶስትነት እንግዳ ሁኖ ከቤቱ ተገኝቷል

እግዚአብሔር ወዳጆቹ እንዲያዝኑ አይፈልግም ማንኛችንም እንድንፈተን መከራ እንድንቀበል እንድንጎዳ እንድራብ አይፈልግም

እግዚአብሔር በአብርሃም ህይወት ውስጥ ያደረገውን ታሪክ ያየነው ገደብ የሌለው ፍቅሩን ነው

ሰይጣን ትንሹንጉሥ ጠባቡን በር ሲዘጋው እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰፊውን በር ከፈተለት ሰይጣን ትንሹን ነገር ሲያበላሽበት እግዚአብሔር በእጥፍ ባረከው

ይህን ታሪክ ስመለከት አብርሃም ሰይጣን እንኳን እንግዶችን ከለከላቸው የሚል ይመስላል ምክንያቱም ሰይጣን እንግዶችን ባይከለክላቸው ስላሴ ከቤቱ በእንግድነት ላይገኙ ይችላሉ አብርሃም ከስላሴ ጋር በአንድ ማዕድ ተቀምጦ አይመገብም ነበር የይሳቅን ልደት በስላሴ አንደበት አይነገረውም የእግዚአብሔር ሰው መሆን በእራሱ በእግዚአብሔር አንደበት አይነገረውም ይህን ሁሉ ምስጢር አያገኘውም ነበር

በፈተና የጸና የተባረከ ነው የሚለው መጽሐፍ ለዚህ ነው እኛ ሳናውቀው ፈተና ለሌላ ማዕረግ ለትልቅ ክብር እያዘጋጀን ነው አብርሃም በመፈተኑ ለዚህ ታላቅ ክብር በቅቷል እግዚአብሔር ያጽናን

የአብርሃምን ቤት የባረከ እግዚአብሔር የእያንዳንዳችን ቤት ይባርክልን እንኳን አደረሳችሁ
737 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:42:20 Watch "አስገራሚው የአራቱ ጥንዶች ሰርግ በቦሌ መድሃኔአለም ቤ/ክ ሙሉ ስርአተ ተክሊል እና መርሀግብር#don't for get subscribe#share#like#" on YouTube


959 views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:24:20 Watch "አስገራሚው የአራቱ ጥንዶች ሰርግ በቦሌ መድሃኔአለም ቤ/ክ ሙሉ ስርአተ ተክሊል እና መርሀግብር#don't for get subscribe#share#like#" on YouTube


991 views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:42:17

አንድ ካህን አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት የንስሀ ልጅ ነበራቸው ።ይህ ወጣት በትንሹም በትልቁም ቱግ እያለ፤ሰዎችን ያስቀይም ነበር።ከአንደበቱ ክፉ ቃላቶችን ስለሚያወጣ ከሰው ጋር መስማማት አልቻለም።ትዕግስት ፈፅሞ የለውም።ይህ ነገር እጅግ ያሳሰባቸው አባትም፤ልጁን የሚለውጡበት ዘዴ ሲያወጡ ሲያወርዱ ቆይተው አንድ መፍትሄ ላይ ደረሱ።አንድ ቀንም በቀረጢት ሙሉ ሚስማር ያዙና ልጁን አስጠርተው እንዲህ አሉት“ልጄ ሆይ …ይህን በቀረጢት ያለውን ሚስማር ተቀበለኝ፤ሁሌም ትዕግስት በጎደለህ ጊዜ እና ሰው ባስቀየምክ ቁጥር አንድ ሚስማር የእንጨቱ አጥር ላይ ሰካ” አሉት።ልጁ ምንም ግራ ቢገባውም አባቱ እንዳዘዙት ማድረግ ጀመረ።በመጀመሪያ ሰሞን በጣም ብዙ ሚስማሮችን ሰካ….ቀስ እያለ ግን በቀን እንጨቱ ላይ የሚሰካቸው ሚስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ…. እያለ…እያለ….በመጨረሻ ምንም ክፉ ያልተናገረ ቀን አንድም ሚስማር ሳይሰካ ዋለ።ልጁ በጣም ታጋሽ ሆኖ ባህሪው ተስተካከለ ማለት ነው።ይህንንም ለአባቱ አበሰረ።
አባም “ እሰይ ልጄ……አሁን ደግሞ ምንም ያልተናደድክ ቀን እና ክፉ ያልወጣህ ቀን በፊት ከሰካሃቸው ሚስማሮች ውስጥ አንዱን ንቀል” አሉት።ልጁ እንደተባለው አደረገ፤ከቀናት በኋላ ሁሉንም ሚስማሮች ነቅሎ ጨረሰ።ወደ አባም ሄዶ ሚስማሮችን አስረከበ።አባም አንዲህ አሉት
“አየህ ልጄ……አሁን የሰካሃቸውን ሚስማሮች ነቅለህ ጨርሰሃል…..በጣም ታጋሽ ሆነሃል ማለት ነው፤ነገር ግን እስቲ አጥሩን ተመለክት….ፈጽሞ እንደ ድሮው ሊሆን አይችልም፤ሚስማሩ ቢወጣም ተበሳስቷል።ክፉ ንግግርም ልክ እንደ ሚስማር ነው፤ሺህ ጊዜ ይቅር ብትልም፤እንደሚስማሩ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ፤እናም ልጄ……..በህይወት ትዕግስት ይኑርህ…..አንደበትህን ቆጥብ” ብለው አስተማሩት።

-ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤
1ኛ የጴጥሮስ 3:10

-ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 18:21

-የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፤ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።
መጽሐፈ ምሳሌ
1.2K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:43:53 https://www.facebook.com/117159900989698/posts/138595835512771/?flite=scwspnss
978 views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ