Get Mystery Box with random crypto!

ማር 13፡18 ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው #ክረምት የብሉይ ኪዳ | 💖 ዕፀጳጦስ 💖

<<ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ>>
ማር 13፡18


ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው

#ክረምት የብሉይ ኪዳን ዘመን ምሳሌ ነው

የክረምት ገበሬ ጠዋት ጾሙን ይወጣል
ቀን ከላይ ዝናም እየወረደበት ከታች ጭቃ እየሆነበት ሲሠራ ውሎ ማታ እራት ጎመን ይቀርብለታል
ድካምና ረኃብ
ፍርሃትና ስቃይ ይፈራረቁበታል!
ነቢያት በዘመነ ብሉይ እንዲሁ ነበሩ።
ያለ ልጅነት ወጥተው ያስተምራሉ ፤ትንቢት ይናገራሉ
ሲመሽ ማታ (ሲሞቱ) በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደሲኦል ይወርዳሉ(የጎመን እራት)!


#ክረምት የቃል ኪዳን መገለጫ ነው

ክረምት በብሉይም በሐዲስም ከተደረጉ ኪዳናት ጋር ተያይዞ ይገለጻል
በተለይም ቅዱስ ያሬድ ክረምትን ከኖኅ ኪዳን ጋር እያነጻጸረ የገለጸው የዜማ ድርሰት አስደናቂ ነው
"ያከርም በበዓመት ተዘኪሮ ዘመሐለ ለኖኅ ገብሩ" የሚያስደንቀኝ ገለጻ ነው! (ዘፍ 8፥22)

#በክረምት፦

መብረቅ
ነጎድጓድ
በረድ (በረዶ)
ማዕበል ሞገድ አለ

ሰማዩ ይጠቁራል
ደመናው ይከብዳል
መሬቱ ይላላል
ወንዙ ይሞላል
ዘመድ ከዘመድ ሳይጠያየቅ ይከርማል
ስለዚህም በዚህ ወቅት ወርኀ ክረምቱን በሰላም እንዲያሳልፍልን ጸሎት/አስተምሕሮ ይደረጋል
ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው የአስተምህሮ ጊዜው የዚሁ አካል ነው።

ዝናሙ ዝናመ ምሕረት
ጠሉ ጠለ በረከት
ነፋሱ ነፋስ ምሕረት እንዲሆን አስተብቁዖት(ምልጃ) ሊደረግ ይገባል።

#ክረምት የምጽአተ እግዚእ ምሳሌ ነው
ማቴ 24፥27

ክረምት የጌታ መምጣት የዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ሆኖም ይነገራል
በክረምት ከሚሰማው ነጎድጓድ በላይ የሆነ ነጎድጎድ በዕለተ ምጽአት ይሰማል
ጌታም እንደ መብረቅ ብልጭታ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ያለ ወሰን በምልዓት በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ይገለጣል
ይህን እያሰብን በጎ እንድንሠራ ክረምት አስፈሪ ምልክቶች ይታዩበታል!
ምልክቶቹም አቅማችንን አውቀን፣ ተፈጥሮ ከእኛ አቅም በላይ መሆኑን ተገንዝበን ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ የሚያሳስቡ ናቸው!

#በዚህ ክረምት መርከብ መሥራት በመርከቡ መቀመጥ ያስፈልጋል

#መርከቡም፦
ሃይማኖት
ቤተ ክርስቲያን
ጸሎት
ንስሐ
በጎ ሥራ ነው!

"ግበር ታቦተ በዘትድኅን" የምትድንበትን መርከብ ሥራ!
አምላካችን እግዚአብሔር ክረምቱን በሰላምና በጤና ያሳልፈን!!!

አሜን!