Get Mystery Box with random crypto!

Reflection of True light

የቴሌግራም ቻናል አርማ truelight_reflection — Reflection of True light R
የቴሌግራም ቻናል አርማ truelight_reflection — Reflection of True light
የሰርጥ አድራሻ: @truelight_reflection
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

…መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
ኤፌ 2:10
ለማንኛውም አስተያየት እና ሀሳብ 👉 @True_light_bot

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-05 07:08:01 ተስፋ ለመቁረጥ የተለየ ችሎታ አያስፈልግም፡፡ ማንኛውም አለማዊ ተነስቶ ከዚህ በኋላ ‹‹አለቀልኝ›› ብሎ መናገር ይችላል፡፡ ተስፋ ቆራጭ ሰው ለመሆን የግድ ክርስቲያን መሆን አያስፈልግም፡፡ ማንም ሰው ተስፋውን በአንድ ጊዜ መቁረጥ ይችላል፡፡ ዳሩ ግን ኢየሱስን ያወቀ ሰው እንዲሁ እንደዋዛ ብድግ ብሎ ተስፋ መቁረጥ አይችልም፡፡ በውስጡ ያለው የኢየሱስ መንፈስ ወደ ተስፋ መቁረጥ ውሳኔ ከመምጣቱ በፊት አበርትቶና እንደገና የትንሳኤ መንፈስ ሰጥቶ ያቆመዋል፡፡ አለቀለት በቃው ሲባል አማኝ እንደ ንስር ኃይሉ ታድሶ ማንሰራራት ይጀምራል፡፡

By Joyce Mayor
..................................

@truelight_reflection
@truelight_reflection
512 views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 21:14:51 በአንድ ወቅት የምወዳት ልጄ ለሰርጓ ዝግጅት እያደረገች ነበር፡፡ ምርጥ ቀለበት አዘጋጀች፡፡ ገንዘብም በሚገባ አጠራቀመች፡፡ የሠርጓንም ቀን በሚገባ አዘጋጀች፡፡ ከጥቂት ጊዚያት በኋላ የሰርጓ ዜና ለሠዎች ሁሉ ታወጀ፡፡ ይሁን እንጂ ከጥቂት ቀናት በኋላ የታሰበው የሰርግ ዝግጅት ተሰረዘ፡፡ በሙሽራው አለመታመን ምክንያት!በእውነት ለረጅም ዘመን ራሷን በንፅህና ጠብቃ ለኖረች ሙሽራ እንዲህ ያለው አሳዛኝ ክስተት ልብ ሰባሪ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሴት ልጄ ልቧ ይጎዳል ብለን ስናስብ እርሷ ግን በሰይጣን ላይ የድል ቃል ማውጣት ጀመረች ፤‹‹እግዚአብሔር ሆይ እጮኛዬ ብዬ የያዝኩትን ሰው ባህሪይ አስቀድመህ ስለገለጥክልኝ አብዝቼ አመሰግናለሁ፤ እጮኛዬ የነበረው ሰው ይህንን ባህሪይውን ትዳር ይዤ ቢገልጥ ኖሮ ብዙ ጉዳት ይደርስብኝ ነበር፤ አሁን ግን አስቀድመህ አድነኸኛልና አመሰግናለሁ›› ማለት ጀመረች፡፡

ወገኖቼ በልጄ ጥልቅ መንፈሳዊ ብስለት ኮራሁኝ፡፡ ህይወቷን ሊያጨናግፍባት የተነሳውን ሰይጣንን ላቅ ባለ መንፈሳዊ ማንነት ማሸነፍ ቻለች፡፡ ምንም እንኳን የደረሰባት ነገር ለመልካም ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ሰይጣን እንደተሸነፈች አድርጎ ማቅረቡ አልቀረም፡፡ በዚህ ጊዜ እኔና አባቷ አብረናት እየቆምን ያንን መራራ ጊዜ በድል ማሸነፍ ተችሎናል፡፡ ልጄ ስእተት በተሞላው የሰው ልጅ ላይ ሙሉ በሙሉ እምነቷን ጥላ ቢሆን ኖሮ ይሄን ጊዜ በብዙ አቅጣጫ ህይወቷ ተሰባብሮ ለብዙ ጉዳት በተዳረገ ነበር፡፡ ዳሩ ግን እምነቷን በማይነቃነቀው የእምነታችን መሰረት ላይ ማለትም በኢየሱስ ላይ በመጣሏ ምክንያት ዛሬ ህይወቷን በድል መምራት ተችሏታል፡፡ ዛሬ ልጃችን እግዚአብሔር አብዝቶ የሚወድ ለጌታ ሥራ ከእኛ አገልግሎት ጋር ቀን ከሌት የሚደክም ባል አግብታለች፡፡ ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን።

#ምንጭ- #ከጆይስ_ማየር መጽሐፍ የተወሰደ (ስማኝ ተስፋ መቁረጥ)

..................................
@truelight_reflection
492 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 15:03:04
ወረው ሁለ የሚያስፈራ
የምሆነው በምድር ዙርያ
እየከፋ ስሄድ ጊዜው
መሸሸግያ ኢየሱስ ነው
ለእኛ ግን መጠለያች እግዚአብሔር
ነው እና የዋርካ ጥላችን እግዚአብሔር

@ደረጄ ከበደ
532 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 06:42:33 አንደ ነክታችሁ አሜን በሉ

ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦

እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።

እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ። ዘኍል 6:23-27
524 views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:21:48
ሩሃማ ማለት ምን ማለት ነው?
Anonymous Quiz
6%
ሕዝቤ አይደለም።
19%
ምሕረት የማይገባት።
5%
ሕዝቤ ነው።
70%
ምሕረት የምገባት።
79 voters583 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 09:16:29 በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ አሁንም እንቆያለን

#ጥበብ እና #እድሜ ምን ያገናኛቸዋል?

የኢዮብ ወዳጆች በኢዮብ ሕይወት ላይ የሆነውን ለማየት መጥተው ኢዮብን ስወቅሱት "እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ያመጣብህ በኀጥያትክ ምክንያት ነው" በማለት ስሟገቱት እንመለከታለን።
ኢዮብም ስመልስ፦

እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፤ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። ኢዮብ 23:11

ነገር ግን ላነሳ የፈለኩት የእድሜ እና የጥበብን ግንኙነት ነው። የኢዮብ ጓደኞች በእድመያቸው የሸመገሉ ስሆን ከኢዮብም ጋር ብዙ ምዕራፎችን በጽኑ ስከራከሩ ነበር፤ ነገር ግን ብዙ የመከራን ክርክር ያሳጠሬ በእድሜ ከእነርሱ አነስ የምል ምናልባትም ወጣት የነበረ ኤሊሁ ከምዕራፍ 32- 37 ተናገረ።

የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፡— እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። እንደዚህም አልሁ፡— ዓመታት በተናገሩ ነበር፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ባስተማረች ነበር። ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል።
ኢዮብ 32:6-8

ይሁን እንጅ በዚሁ መጽሐፍ ላይ ተቃራን ያልሆነ ነገር ተቃራን ምመስል ጥቅስ እናገኛለን፦
በሽምግልና ጊዜ ጥበብ፥ በዘመንስ ርዝመት ማስተዋል ይገኛል።
ኢዮብ 12 ፡12

እርግጥ ነው በእድሜ ርዝመት ብዙ ነገር ማወቅ ይቻላል ነገረ ግን ይህ የምሆነው እድሜ እንድያስተምረን ስንፈቅድ ብቻ ነው። ጥበብ እና ማስተዋል ከእድሜ ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ ለመማር ባለን ፍላጎት ላይ ይመሠረታል እንጅ እድሜያችን ቁጥር በራሱ ጥበብ ልሰጠን አይችልም።

እና ይገርማችኋል ከኤሊሁ ንግግር በኋላ ማንም ሳይሆን እግዚአብሔር ነበር የተናገረው፤ እግዚአብሔር ተናግሮ የኢዮብ መከራና አጠቃላይ ምዕራፉ ያበቃል።

#ተባረኩ ሰሞኑን በኢዮብ መጽሐፍ ላይ እንቆያለን።
...................................
@truelight_reflection
552 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:51:35 ከመጽሐፍ ቅዱሳችን ክፍል የኢዮብ መጽሐፍ ከሚያስተምረን ነገር አንዱን ላካፍላችሁ።

#ጥበብ እና #ማስተዋል

በብዙ ፊለጋ የምትገኝ ብትሆንም፤ ሰውም ይፈልጋት እንጅ ስፍራዋን(ያለችበትን ቦታ) ከቶ አያውቅም።

የሰው ልጅ በዘመኑ በረቀቀ አስተሳሰብ እና በረቀቀ መንገድ የፈለገውን ሁሉ ማግኘት ችሏል። እንድሁም ወርቅን እና የተለያዩ ውድ እንቁዎችን ፈልጎ ማግኘት ችሏል።

ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
ኢዮብ 28:12

ሰው መንገድዋን አያውቅም፤ በሕያዋን ምድር አትገኝም። ኢዮብ 28:13

በብዙ ገንዘብ አትገዛብም፤ በወርቅ እና ውድ በተባሉ እንቁዎችም አትለወጥም።
 
የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል። የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፥ በጥሩም ወርቅ አትገመትም። ኢዮብ 28:18-19
 
እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
ኢዮብ 28:20

እግዚአብሔር መንገድዋን ያስተውላል፥ እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።
ኢዮብ 28:20

ይህ ድንቅ ጥበብ ታድያ ምን ይሆን

ሰውንም፡— እነሆ፥ #እግዚአብሔርን_መፍራት ጥበብ ነው፤ #ከኃጢአትም_መራቅ ማስተዋል ነው፡ አለው። ኢዮብ 28:28

...................................
@truelight_reflection
498 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 20:20:43
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።

ማቴ 7: 7
482 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 07:15:02 ኢዮብ 42:1-7

1፤ ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፡—
2፤ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።
3፤ ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ።
4፤ እባክህ፥ ስማኝ እኔም ልናገር፤ እጠይቅህማለሁ፥ አንተም ተናገረኝ።
5፤ መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፤
6፤ ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።
546 views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 15:31:49
መልህቄ...
ያስከኝ ኢየሱሴ

@truelight_reflection
507 views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ