Get Mystery Box with random crypto!

✿ ቅዱሳት አንስት ✿

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusananist — ✿ ቅዱሳት አንስት ✿
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusananist — ✿ ቅዱሳት አንስት ✿
የሰርጥ አድራሻ: @kidusananist
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 177
የሰርጥ መግለጫ

"የቅዱሳንን ዜናቸውን ለመናገር ፍቅር ያስገድደኛል::"
---አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
.
.
.
.
༺ፀሎታቸው በረከታቸው አይለየን!༻

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-06 22:38:04
35 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 07:56:35 ከእመቤታችን የዘመናችን ድንቅ ተአምራት አንዱ
(በፈረንጆች ጥር/2014 የተደረገ ድንቅ ተዓምር)

ቅልጥ ያለ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ባለባት ሶርያ ውስጥ አንድ የሴቶች ገዳም አለ። አክራረሪዎች ገዳሙን ለማውደም ሮኬቶችን ተኮሱ። የተኩስ ንውጽውጽታም ገዳማውያኑን ለሞት እንደተቃረቡ አረዳ። ነገር ግን ከፍርሃት ሰቀቀን ባይላቀቁም ምንም ሳይሆኑ ቀሩ።

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ምን እንደሆኑ ለማየት የመጣው አንድ መኮንን መነኮሳያቱን ደኅና ማግኘቱ አስደንቆት ሲጠይቃቸው የሆነውን አስረዱት። እርሱም ተኩሱን አይቶ ስለነበር ተዘዋውሮ ሲመለከት ሮኬቱ ሳይፈነዳ መቀመጡን አይቶ ደነገጠ። ገዳማውያቱ እናቶችም አይተው ደነገጡ፤ ፈሩም። በዚያው ቅጽበት ግን አንድ ነገር ድንገት ታየ። ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች፣ ግርማዋ የሚያስደንቅ ሴት ከሰማይ ወረደች እና ሁሉም እያዩ ተተኩሶና ገዳሙ ላይ ወድቆ ያልፈነዳውን የሮኬት ጥይት አንስታ ወሰደችው። መኮንኑ ተደነቀና ማን ነች ሲል መናኞቹን ጠየቃቸው። ከእመቤታችን ውጭ ሌላ ሴት ልትሆን እንደማትችል መለሱለት።

እመቤታችን ሆይ በእኛ ሀገርም ደራሽ ለሌቸው ሁሉ ድረሽላቸው። ጌታችን ሆይ ከእናትህ ጋር ስለመሰደድህ ብለህ ስደቱንና መከራውን መቋቋም ለሚያቅታቸው ራራላቸው፤ የጨካኞችን ልቡና መልሰህ ሕዝቡ በፍቅር እንዲኖር እርዳን፤ አሜን።

(ከዲያቆን ብርሃኑ አድማስ አንለይ የተወሰደ)

Source: (http://www.pravoslavie.ru/english/67980.htm)
47 views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 17:51:03 https://youtube.com/shorts/dWl7MPgWMqI?feature=share
111 views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 08:17:18 +++ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ።+++ (መዝ 59:3) ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኃቸው።
ማተብ የማሠር ልማድ የመጣው ከእስክንድርያው ኤጲስቆጶስ አባ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው።ያስጀመረውም ያዕቆብ ዘአልበርዲ ነው።እሱም የሐዋርያት የቀናች ኃይማኖት በሽሽግ ሲያስተምር ይህን የተቀደሰ ስራውን ለማሠናከል ቦዘንተኞች በስብሰባው ላይ በመገኘት ትምህርቱን ያስቱበት ስለነበር የእርሱ የሆኑትን ለይቶ ለማወቅ ሲል በአንገታቸው ላይ ማተብ አሠረላቸው።ይኸውም ቀይ-ደሜን አፈሳለሁ ፣ ጥቁር -መከራ እቀበላለሁ ፣ ነጭ ወይም ቢጫ -ትንሣኤን ተስፋ አደርጋለሁ ማለት ነው።እንጂ ምክንያቱን ሳናውቅ እንዲሁ በውርስ የምናረገው አይደለም።ይልቁንም ቅዱስ ዳዊት እንዳለው ምልክት የተባለ ቅዱስ መስቀልን የምንሸከምበት ነው።
+ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።+
133 viewsedited  05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:45:51
172 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 14:01:11
117 views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 18:25:11
152 views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 21:14:29
152 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 14:28:28
#ቅዳሜ (ቅዱሳት አንስት)
በዕለተ ትንሣኤ ሌሊቱን ሲመላለሱ ያደሩ ሴቶች የድካማቸውና ጌታን የመሻታቸው ዋጋ መታሰቢያቸው ናት። አንድም በጠቅላላው ከሕማማቱ እስከ ትንሣኤው ብዙ የእንባ መሥዋዕት ያቀረቡ እናቶች የሚታሰቡበት ስለሆነ ቅዱሳት አንስት ተብላለች።

✟ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን✟
✟አብይ ሀይል ወበስልጣን✟
✟አሰሮ ለሰይጣን✟
✟አግአዞ ለአዳም✟
✟ሰላም✟
✟እምይዜየሰ✟
✟ኮነ✟
✟ፍስሀ ወሰላም✟

እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ለሁላችንም!!!
ቤተ ተክለ ሃይማኖት
@beteteklehaimanot24
@beteteklehaimanot24
135 views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 12:25:54 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
107 views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ