Get Mystery Box with random crypto!

HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamernoah — HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamernoah — HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው
የሰርጥ አድራሻ: @hamernoah
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.54K
የሰርጥ መግለጫ

እግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ ( ፩ ተሰሎ ፭÷ ፳፭ ) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ትክክለኛ አድራሻዎቼ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
ቴሌግራም 👉 -https://t.me/hamernoah
My -email ☞nhamere@gmail.com
መካነ ድር፡https:hamernoah.wordpress.comሁላችሁም ተሳታፊ ሁኑ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 15:53:05
273 viewstemesgen Zegeye, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:56:04 "#ምሥጢር ሦስት" በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ተመረቀ!
༺ ༻
"#ምሥጢር ሦስት"በሚል ርእስ በልሳነ ክርስቶስ መ/ር ጳውሎስ መልከዓ ሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው በዮድ አቢሲኒያ የምግብ አዳራሽ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ጠቅላይ ጸሐፊ ፤ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጠቅላይ ጸሓፊ ፣ መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤቶች እና ሕንጻ አስተዳደር ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የቅኔ ሊቃውንት ፣ አንጋፋ ሰባክያነ ወንጌልና ዘማርያን ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለማት ያሉ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተመረቀ !
#"#ምሥጢር ሦስትን " መጽሐፍ የተጻፈበት የተመለከቱትን አንድ ክፍተት ለመሙላት፤ያልታወቀው እንዲታወቅ፤የተሠወረው ገሀድ እንዲወጣ፤ጸሓፊው ትንተና አድርጓል።
ማር ይስሐቅ "#መጻሕፍትን አዘውትረህ አንብብ መጻሕፍት እግዚአብሔር ን ወደ ማድነቅ ልብህን ይመሩታልና "ይላል።
ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በንጉሡ ዘመን አያሌ ሊቃውንትን ሲያስተምሩ “#ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ ፣ ሰውን በመልካችንና በአርአያችን እንፍጠር….”(ዘፍ.፩ ፥ ፳፮ ) በሚል ርእሰ ተነሡና ይህን ኃይለ ቃል በመያዝ የቅድስት ሥላሴን አንድነትና ሦስትነት መተንተን ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ይህን ኃይለ ቃል እኛንም እንደሚመለከት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ! እኛም በአርአያችን እና በአምሳላችን ለታላቋ ቤተ ክርስቲያን በትምህርት ሰው እንፍጠርላት ፡ብለዋል፡፡
_ልሳነ ክርስቶስ መ/ር ጳውሎስ መልከዓ ሥላሴ ለምሥጢረ ሦስት መጽሐፍ የቃላት አመራረጡ፣የዕረፍተ ነገር መዋቅርና የአንቀጽ አደረጃጀቱ በሞዴልነት ይወሰዳል።
_የመጽሐፉ መታሰቢያነት፦ "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ"(ዕብ.፲፫÷፯) እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ፣ልሳነ ክርስቶስ መ/ር ጳውሎስ መልከዓ ሥላሴምየመጽሐፉን መታሰቢያነት ፩ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ከዚህ ዓለም ለተለዩን ፬ቱ አባቶቻችን መሆኑ ተገልጧል ።
_የኅትመት ዘመን _ሰኔ ፳፻፲፬ ዓ.ም
_የመጽሐፉ መሸጫ ዋጋ_220( $20 )
_የገጽ ብዛት_238
#"ምሥጢር ሦስትን " መጽሐፍ በ፲፭ ክፍላት ተካተውበታል ፣የዘመኑ ወጣቶች ሊገባቸው በሚችሉት መልኩ በግልጽ ቋንቋ የቀረበ ሥራ ነው። መጽሐፉ በኀዳግ ማስታወሻ በሥነ ሥርዓት የተዘጋጀ ፣ብዙ ምሥጢራትን አምቆ የያዘ ፣ውስጠ ትርጉም ያላቸው ቃላትን እንዲሁም ክርስትና ሲነኩት ጣዕሙ የሚታወቅ እና መዓዛው የሚያውድ መሆኑን የምንረዳበት መጽሐፍ ነው።
በአጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት፦
1.ነገረ ሃይማኖት (ለምሳሌ ከገጽ 9_15)
2.ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በመዳሰስ የቤተ ክርስቲያናችን የፀጋው ግምጃ ቤት መሆኗን ያሳያል።
3.በትምህርተ ሃይማኖት ዙሪያ ቅድሚያ ስለሚሰጠው ስለ ሦስት ቁጥር የማናውቀውን ለማሳወቅ ፣የምናውቀውን በምሥጢርና በማስረጃ በማስደገፍ ያቀርባል።
4.መንፈሳዊ ሕይወትን የተመለከቱ ጉዳዮች ተካተውበታል ።
“#ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የ፳፬ ሰዓት አገልግሎቷ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልወጣ ነው፡፡ ……የእርሷ በሆነው ቅዱስ ያሬድ ትምህርቷ በሙሉ በዜማ ቀርቦ የትውልዱን ልብ እያረካ ኅሊናውን ወደ ሰማይ እንዲያሻግር ታደርጋለች”( ገጽ -129)
“#ስለጾምና የሰዓት ገደብ ሲነገር ማስተዋል የሚገባን ቁም ነገር ከእኽል ውኃ ከመከልከል አኳያ ጾም በቍጥርና በጊዜ የተወሰነ ይኹን እንጂ ከክፉ ተግባር ከመራቅ አንጻር ክርስቲያን እስኪሞት ድረስ ጾመኛ ነው” ይላሉ ፡( ገጽ-142)
"#ምሥጢረ ሦስት" ርቀው የነበሩትን ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር የሚያገናኝ መጽሐፍ ነው።ሰለዚህ መጽሐፉ እንድናነበው እየፈለገን እንዳንጠፋ፤እየተመኘን እንዳንሸሸው መልእክቴ ነው።
ቅዱስ አግናጥዮስ "ሰው በቀመሳቸው ጊዜ ከሚመሩ ፍሬዎች ሽሹ፤እነዚህ ፍሬዎች የእግዚአብሔር አብ ተክሎች አይደሉምና"ይላል።
★ ★ ★

መ/ር ተመስገን ዘገዬ

ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ዩቲዩብ subscribe and share https://www.youtube.com/channel/UCJKl-fJ4qKtLKfva2ufSc-A
ሰብስክሪያብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
392 viewstemesgen Zegeye, 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:55:59
198 viewstemesgen Zegeye, 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:55:59
202 viewstemesgen Zegeye, 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:10:43 ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ክፍል አማካኝነት በመቄዶንያ ማእከል ሥር ለሚገኙ አረጋውያን የሥጋ ወደሙ መቀበያ ልብስ እና የጸሎት መጽሐፍ ከ120,000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ ማበርከቱን አስታውቋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎትና ትብብር አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት ውስጥ ለአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊዎች በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ሥልጠና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ሲያዘጋጅ አስፈላጊው እገዛ ተደርጓል።

በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ክብካቤ ማእከል ጉዞ በማድረግ በማእከሉ ሥር ለሚገኙ አረጋውያን የሥጋ ወደሙ መቀበያ የሚሆን ነጭ ልብስ እና የጸሎት መጽሐፍ ከ120,000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተገዝቶ ተበርክቷል፡፡

የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ከምርቃታቸው በኋላ በቤተ ክርስቲያን የታችኛው መዋቅር ማለትም በሰ/ት/ቤት እና በሰበካ ጉባኤ ውስጥ ገብተው ማገልገል እንዲችሉ “ዕውቀቴ እና ጉልበቴ ለቤተ ክርስቲያን እናቴ” በሚል መሪ ቃል ተደጋጋሚ ምክክሮች ተደርጓል። እንዲሁም የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ ተከትሎ ዝክረ አበው በሚል ርእስ ያረፉ ፓትርያርኮችንና ሊቃነ ጳጳሳትን የሚዘክር መርሐ ግብር ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት አከናውኗል።

የማኅበረ ቅዱሳን 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር ላይ የምሥጋና ቀን፣ ዐውደ ጥናት፣ ዐውደ ርእይ፣ ዘጋቢ ፊልም፣ ክብረ በዓል የተከናወኑ ሲሆን የማኅበሩን 30 ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ የሚያስቃኝ መጽሐፍ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

@፦ ማኅበረ ቅዱሳን
. ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ዩቲዩብ subscribe and share https://www.youtube.com/channel/UCJKl-fJ4qKtLKfva2ufSc-A
ሰብስክሪያብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
400 viewstemesgen Zegeye, 03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:10:41
254 viewstemesgen Zegeye, 03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:10:17 ማኅበረ ቅዱሳን በ2013 እና 2014 ዓ.ም በማኅበራዊ ድጋፍ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ 17.9 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ ለተፈናቀሉ ምእመናን፣ ካህናት፣ የአብነት ት/ቤቶችና ገዳማት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች ምክንያት ለችግር ለተጋለጡና ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና ቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከልና አካባቢው ለሚገኙ ምእመናን፣ ካህናት፣ የአብነት ት/ቤቶችና ገዳማት ባለፉት 2 ዓመታት የተለያዩ ማኅበራዊ ድጋፎች ተደርገዋል፡፡ ለድጋፉም 17.9 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በሙያ አገልግሎት ዘርፍ ሙያዊ ግምታቸው 29.33 ሚሊዮን ብር የሚሆኑ 85 ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው ዲዛይኖች በነጻ ተሠርተው ለጠየቁ የቤተ ክርስቲያን አካላት ተሰጥተዋል።

እንዲሁም ሙያዊ ግምታቸው 1.5 ሚሊዮን የሆኑ ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ልማት ፕሮጀክቶች ተሠርተው ለጠየቁ አካላት በነጻ ተሰጠተዋል።

@፦ ማኅበረ ቅዱሳን
. ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ዩቲዩብ subscribe and share https://www.youtube.com/channel/UCJKl-fJ4qKtLKfva2ufSc-A
ሰብስክሪያብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
290 viewstemesgen Zegeye, 03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:09:57
241 viewstemesgen Zegeye, 03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:51:28
319 viewstemesgen Zegeye, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:51:23 ★ ★ ★
አዕምሮ ምግቡ መጽሐፍ ነው። የሚያስተምር ሰው መማር ማንበብ አለበት። ካለበለዚያ ያለ ጥሬ እቃ ወፍጮ ማስነሣት ትርፉ እቃ መስበር ነው። (መ/ር #ንዋይ ካሳሁን #ከአሜሪካ )

↳ መ/ር ተመስገን ዘገዬ ↲
ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ገጹን ይጎብኙ :-
ቴሌግራም -https://t.me/hamernoah
https://www.facebook.com/hamernoah/?ref=pages_you_manage
https://www.instagram.com/temesgenzegeye175/
https://www.youtube.com/channel/UCJKl-fJ4qKtLKfva2ufSc-A
324 viewstemesgen Zegeye, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ