Get Mystery Box with random crypto!

የባላገሩ ምርጥ የድምጻዉያን ውድድር በመጪው እሁድ የካቲት 17 ፍጻሜውን ያገኛል ! ለአሸናፊዎች | Top Mereja

የባላገሩ ምርጥ የድምጻዉያን ውድድር በመጪው እሁድ የካቲት 17 ፍጻሜውን ያገኛል !

ለአሸናፊዎች እስከ ስምንት ሚሊየን ብር ሽልማት ያዘጋጀውና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አሻራቸውን እያሳረፉ የሚገኙ በርካታ አዳዲስ ድምፃውያንን በማፍራት የሚታወቀው ባላገሩ ምርጥ የሁለተኛ ዙር የድምጻውያን የፍጻሜ ውድድሩን የካቲት 17 2016 አ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ከመላው የአገሪቱ ክፍል ከተውጣጡ ከሁለት ሺህ በላይ ከሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ውስጥ የመጨረሻ 7 ድምጻውያን አሸናፊ ለመሆን በመጪው እሁድ ከፍተኛ ፉክክር እንድሚያደርጉ ሲጠበቅ ለአሸንፊዎች ሽልማትም 8 ሚሊዮን ብር ተዘጋጅቷል።

በዚህም መሰረት አንደኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ አሸናፊ አንድ ሚልየን ብር የገንዘብ ሽልማት እና ሁለት ሚሊየን ብር የሚያወጣ አልበም እንደሚሰራለት በጥቅሉ የሦስት ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚሆን ሲሆን

ሁለተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 500,000 ብር ሽልማት እና አንድ ሚልየን አምስት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የሙዚቃ አልበም እንደሚሰራለት በአጠቃላይ የሁለት ሚሊዮን ብር አሸናፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ሶስተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ 250 ሺህ ብር ሽልማት እና ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የሚያወጡ ዘፈኖች በጥቅሉ የ አንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ያገኛል ነው የተባለው።

በእለቱ ልዩ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁባቸውን የሙዚቃ ስራዎች በማቅረብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ታውቋል።

የውድድሩን የተመደበውን ሽልማት ሶስት አገር በቅል
የፍጻሜ ውድድሩ በባላጉ ቴሌቪዥን፣በባላገሩ የዩቲዩብና ሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በኩል በቀጥታ በአገር ውስጥና በመላው አለም ለሚገኙ ተመልካቾች እሁድ የካቲት 17 ከ8 ሰአት ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ።

@topMereja