Get Mystery Box with random crypto!

«አቶ ታዬ ደንደዓ ይቅርታ ቢደርግላቸው» የጨፌ አባል «አቶ ታዬ ደንደዓ በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ | Top Mereja

«አቶ ታዬ ደንደዓ ይቅርታ ቢደርግላቸው» የጨፌ አባል

«አቶ ታዬ ደንደዓ በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የፃፉት አሳፋሪ እና ኦሮሞን የሚበትን ነው» አቶ ፍቃዱ ተሰማ

አንድ የምክር ቤት አባል የሚከተለውን ብሏል «አቶ ታዬ ሰው ናቸው ሊያጠፉ ይችላሉ፣ ለፓርቲውም ለሀገርም የሰሩት በርካታ ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉ፣ በምርጫ ወቅትም ወጣቶችን የፓርቲውን ማኒፌስቶ በማስገንዘብ ትልቅ ስራ ሰርቷል፣ አንድ ጊዜ ይቅርታ ብናደርግላቸው አሪፍ ነው፣ ለምሳሌ በትግራይ ክልል በሀገር ደረጃ ትልቅ ወንጀል እራሱ የፈፀሙ ሰዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደ ፌዴራል ስልጣን ሊመጡ ነው፣ እኛ ለምን እንጨካከናለን አሁን ይቅርታ ተደርጎላቸው ከስልጣን ዝቅ ብለው ቢሰሩ እላለሁ» ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግሯል።

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል «ውስጣችን ማፅዳትን አለብን የሚለው የሁል ጊዜ ጥያቄ ነው፣ ውስጣችንን ካላፀዳን ጠላትን ማሸነፍ አንችልም፣ የትግራይ ሌላ ጉዳይ ነው እዛ እያስተዳደረ ያለው የኛ ፓርቲ አይደለም። አቶ ታዬ በተደጋጋሚ በከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በክልልም በፌዴራልም ምክር ተሰጥቶት ነበር፣ እልህ አስጨራሽ በሚባል መልኩ እሱን ለመመለስ ጥረት ተደርጎ ነበር በመጨረሻም እርምጃ መውሰድ ግድ ሆኖ ነው የተወሰነው፣ በምርጫ ወቅት ቅስቀሳ አድርጓል ለተባለው ለእሳቸው ብቻ የተሰጠ አይደለም ሁሉም የሰራው ስራ ነው። የሰላም ስምምነት ጥረት ሲደረግ ግጭት በመቀስቀስ ተሳትፏል፣ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የፃፉት የሚያሳፍር እና ኦሮሞን የሚበትን ስለሆነ እዚህ የምትገኙ የምክር ቤት አባላት በግል ተወክላችሁ ሳይሆን ፓርቲውን ወክላችሁ የተገኛችሁ ስለሆነ ዛሬ የቀረበው ያለመከሰስ መብት ማንሳት በዚህ እንዲታይ እላለሁ» ሲሉ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።

@topMereja