Get Mystery Box with random crypto!

#ብሔራዊ_ፈተና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል። ፈተናው በዩኒቨርሲ | Ministry of education®

#ብሔራዊ_ፈተና

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ተማሪዎች መብታቸው ፣ ግዴታቸው፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የሚችሉት እና የተከለከሏቸው ነገሮችን ከላይ በምስሉ በዝርዝር ተቀምጧል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER