Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የልደት ምስክር ወረቀት በመያዝ ለፈተና እንዲቀመጡ ሊደረግ ነው  በአዲስ | Ministry of education®

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የልደት ምስክር ወረቀት በመያዝ ለፈተና እንዲቀመጡ ሊደረግ ነው 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል የመታወቂያ አገልግሎት መቆሙ የሚታወስ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ እንደመሆኑ መጠን ለፈተና ለመቀመጥ ተፈታኞች የነዋሪነት መታወቂያ እየጠየቁ በመሆኑ በልደት የምስክር ወረቀት ለፈተና እንዲቀመጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ማንኛውም የመታወቂያ አገልግሎት አሁን ላይ  የቆመ በመሆኑና የዜጎችን ማንነት የሚገልፅ ገዢ ሰነድ የልደት ምዝገባ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለተፈታኞች በልደት የምስክር ወረቀት ለፈተና እንዲቀመጡ ለማድረግ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ማስተካከያ እንዲደረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የልደት ምዝገባ ያላከናወኑ ተፈታኞች ከወዲሁ ምዝገባውን አከናውነው የምስክር ወረቀት በእጃቸው እንዲይዙ ሲሉ አቶ ዮናስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER