Get Mystery Box with random crypto!

#NationalExam ለ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና አስፈፃሚዎች ስልጠና ተሰጣቸው። የትምህርት | Ministry of education®

#NationalExam

ለ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና አስፈፃሚዎች ስልጠና ተሰጣቸው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ማጠናቀቂያ ፈተና አስፈጻሚዎች ሥልጠና እንደተሰጣቸው ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ የፈተና አስፈፃሚዎች ትልቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በመገንዝብ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ በማሳሰብ ዝርዝር የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ፤ የፈተና አስፈፃሚዎች በቂ ትኩረት በመስጠት ያለ ምንም አድልዎ ሙያዊ በሆነ አግባብ እንዲሁም በቁርጠኝነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

ዝርዝር ስልጠና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና በዘርፉ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የ2014 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከመጪው መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በሁለት ዙር ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ፎቶ : የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER