Get Mystery Box with random crypto!

ዩንቨርስቲዎች በፌደራል ፓሊስ ብቻ ይጠበቃሉ ================== ኢሳት (መስከረም 13/2 | Ministry of education®

ዩንቨርስቲዎች በፌደራል ፓሊስ ብቻ ይጠበቃሉ
==================
ኢሳት (መስከረም 13/2015) አዲስ አበባ:- በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መደረጋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት አመታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጠሩ ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ ፣ ወላጆች በእምነት ልጆቻቸውን እንዲልኩና ተማሪዎች ደህንነት ተሰምቷቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት በዩኒቨርስቲዎች ያጋጥሙ ከነበሩ የፀጥታ ችግሮች በመነሳትም በአዲሱ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶች ከወዲሁ ለመከላከል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መደረጋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በተለይም ለኢሳት ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ በቆዩባቸው ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የፈተና ስርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ሲባል በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎም የፀጥታቸው ሁኔታ አስተማማኝ ባልሆኑ አካባቢዎች በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተመደቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር በማንሳት ስጋታቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል።

ለዚህ የተማሪዎች አለፍ ሲልም የወላጆች ስጋትም የፀጥታ ችግር አለባቸው በሚባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ተማሪዎች ያለስጋት ፈተናቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ እንዲፈተኑ ለማስቻል የሚመለከተው አካል እየሰራበት እንደሆነ እና የፀጥታ ስጋቱን ለማስወገድ መፍትሄ እንደተቀመጠለት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ አክለው ለኢሳት ተናግረዋል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER