Get Mystery Box with random crypto!

ፈተና አላሰራከኝም በሚል ምክንያት ድብደባ የፈጸሙት ተማሪዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የሀ | Ministry of education®

ፈተና አላሰራከኝም በሚል ምክንያት ድብደባ የፈጸሙት ተማሪዎች

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እየተለመዱ የመጡ ነውረኛ ድርጊቶች ተበራክተዋል። በብዙ ዩንቨርሲቲዎቻችን ላይ ሎካል በመባል የሚታወቁ ዩንቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች ላይ አለፍ ሲልም በግቢው ሰራተኞች ላይ መምህራንንም ጨምሮ ጫና ሲያሳድሩ ይስተዋላል። ሎካል የሚባሉት ስብስቦች ያደርሷቸዋል ከሚባሉት ጫናዎች መካከል በብዛት የሚደርሱን ጥቆማዎች በፈተና ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ናቸው።

አንዳንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ግልፅ በሆነ መልኩ ሎካል ለሚባሉት ተማሪዎች የፈተና ጥያቄዎች ቀድመው እንደሚወጡ በተለያዩ ጊዜያት ከሚደርሱን ጥቆማዎች ለመረዳት ችለናል።

አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ወዲህ በብዛት የሚፈለጉ የትምህርት መስኮችን ለመቀላቀል በሚደረገው ውድድር ላይም የሎካሎች ተጽዕኖ ቀላል እንዳልሆነ በርካታ ተማሪዎች በምሬት ጭምር ነግረውናል።

ሎካል የሚባሉ ተማሪዎችን የተለያዩ ፀያፍ ድርጊቶች በሌላ ሰፊ ዳሰሳ የምንመለስበት ይሆናል።

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የምትመለከቱት የተንቀሳቃሽ ምስል በትላንትናው ዕለት የ atc ቤተሰቦች ያካፈሉን መረጃ ሲሆን ድርጊቱ የተፈፀመው በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ሎካል ተማሪዎች መሆኑን አረጋግጠናል።

ተማሪው ላይ ድብደባ የፈጸሙት ተማሪዎች በቪድዮው ላይ መስማት እንደሚቻለውም #ፈተና_አላሰራከኝም በሚል ምክንያት ነበር። የተማሪውን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልን ሲሆን ዩንቨርሲቲው በተማሪዎቹ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንዲሁም የተማሪውን የደህንነት ጉዳይ ተከታትለን እናሳውቃቹሃለን።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER