Get Mystery Box with random crypto!

በክፍል ዉስጥ የነበሩ 85 ተማሪዎችን ከጎርፍ አደጋ መታደጉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮ | Ministry of education®

በክፍል ዉስጥ የነበሩ 85 ተማሪዎችን ከጎርፍ አደጋ መታደጉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታዉ ፊጋ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኘዉ ኒዉ ፖራዳይ መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት በክፍል ዉስጥ የነበሩ እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 7 የሆኑ 85 ተማሪዎች ከዋናዉ መንገድ ጥሶ በክፍል ዉስጥ በገባዉ ጎርፍ ተከበው እንደነበር ተገልጿል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ቦታዉ በመገኘት ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሰማናንያ አምስቱንም ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በጎርፍ ከተያዙበት ክፍል ዉስጥ በሰላም ማዉጣት መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረው ክረምቱ የሚበረታ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱና ከሚመለከታቸዉ ተቋማት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER