Get Mystery Box with random crypto!

ጥራት ያለው ተማሪ የማያፈሩ፤ ማኅበረሰቡን የማይጠቅሙ ዩኒቨርስቲዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ተጠቆመ ጥራ | Ministry of education®

ጥራት ያለው ተማሪ የማያፈሩ፤ ማኅበረሰቡን የማይጠቅሙ ዩኒቨርስቲዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ተጠቆመ

ጥራት ያለው ተማሪ ማፍራት የማይችሉ፣ ደረጃውን የጠበቀ ምርምር የማያካሂዱና የአካባቢውን ማኅበረሰብ የማይጠቅሙ ዩኒቨርስቲዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጠቆሙ።

ሚኒስትሩ ከዋቸሞ ፣ ወራቤና ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ተመራማሪዎችና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ይህንን የገለጹት።

ዩኒቨርስቲዎች ዓለም አቀፍ ውድድሩን ለመሸከም የሚያስችል ዕውቀት የሚፈራባቸው ቦታዎች መሆናቸውን የጠቆሙት ፕ/ር ብርሃኑ ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ሁኔታ ዩኒቨርስቲዎች ጥሩ ዕውቀት ያላቸው ተማሪዎች ማፍራት ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዜጎች እንኳን ማፍራት አልቻሉም ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ የውይይቱ ዓላማ በትምህርት ዘርፉ ያሉ ችግሮችን ምንነት በመለየት ችግሮችን ለመፍታት የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ በየዩኒቨርስቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች የመነሻ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽና ማብራርያ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER