Get Mystery Box with random crypto!

ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ tinsae_ze_ethiopia — ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ tinsae_ze_ethiopia — ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝
የሰርጥ አድራሻ: @tinsae_ze_ethiopia
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.44K
የሰርጥ መግለጫ

📢 ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ገዳማት ስርዓት ፣አሁናዊ ዜና እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ፡ ቅዱሳን መካናት እና ገዳማት ታሪክ
📢 የቅዱሳን ገድላት
📢 ቅዱሳን አበው ሊቃውንት
📢 ህዝበ ክርስቲያንን ማንቃት
📢 ቅድመ ኢትዮጵያ ትንሳዔ እና የኢሉሚናቲ ኅቡእ ማኅበር ኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡትን ሴራዎችን ማጋለጥ
ለውይይት
@Tinsae_ze_ethiopiaofficialgrp

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-05 07:28:18
1.5K viewsBereket, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 03:42:06
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በቅዳሴው "ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው፤ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው?፤ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?፤ይህ ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ኘው?ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስኪሞት አደረሰው በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት ፣አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ"ይላል
2.8K viewsBereket, edited  00:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 13:08:53 #ገብር _ኄር

መምህር አብርሃም በዕውቀቱ

መጋቢት ፳፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

በጎ አገልጋይ ለጌታው ታምኝ እንደመሆኑ ‹‹ገብር ኄር›› ይባላል፡፡ ይህም ስያሜ ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት እንደተሰጠ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ይገልጻል፡፡ የስያሜው መነሻ የሚገኘው ደግሞ በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው በማቴዎስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ (ማቴ.፳፭፥፲፬-፴)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የእገሌና የእገሊት ተብሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የኃላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ሐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡

በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሄዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት፣ ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ኃላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡

ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ኃላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ኃላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት፣ ሁለኃ አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ እንዲያተርፉበት መክሊቱን ሰጥቷቸው በሄደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሢሰሩ የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኃይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡

ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ፣ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን እንዳደረገበት ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረና በዚህ ከፊቱ ያዘነውን ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው እናነባለን፡፡

በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይርዳን።

ምንጭ:- ማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ የተወሰደ
1.9K viewsBereket, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 05:14:19 "እጅግ የምወዳችሁ ምእመናን ሆይ የጾም ጥቅሟ ምን ያህል የበዛ እንደሆነ ነፍሳችን ከዚህ ብዙ ጥቅምን እንደምታገኝ ከጌታችንና እና ከአገልጋዮቹ ተምረናል፡፡ ስለሆነም የጾም ወራት ሲቃረብ ግድ የለሽነትንና ሞራለ ቢስነትን ከእኛ አስወግደን ንዑድ ክቡር የሚሆን ጻውሎስ፡- የውጭው ሰውነታችን ይበልጥ ሲጠፋ የውስጡ ሰውነታችን ይበልጥ ይታደሳል’’ ብሎ እንዳስተማረን እጅግ ደስ ተሰኝተን ልንቀበለው ይገባናል ብዬ እማልዳችኃለሁ፡፡ /2ኛ ቆሮ 4፡16/

ጾም የነፍስ ምግብ ሥጋ ሰውነታችን እንዲወፍር እንደሚያደርግ ሁሉ ጾምም ነፍስን ያበረታል ፈጣንና መንፈሳዊ ክንፍን ይሰጣል፤ ወደ ሰማያዊ ምስጢር ገብታ በፅሞና እንድትያዝ ያደርጋታል የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ እንድትንቅ ያስችላታል፡፡

ቀላል ጭነትን የተሸከሙ መርከቦች ፈጥነው ባህሩን እንደሚሻገሩ እጅግ ብዙ ጭነትን የተሸከሙት ግን ባህሩንና ወጀቡን ቶሎ ማለፍ እንደሚያቅታቸው ሁሉ ልክ እንደዚሁ ጾምም ውስጣዊ ምስጢር እንድንገባ በዚያም ስላሉ አይነገሬ በረከቶችን እንድናስብ በዚህ ዓለም ላይ ያሉት ሁሉም ነገሮች እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥነው የሚያልፉ እንደሆኑ እንድንገነዘብ ታደርጋለች፡፡

ከዚሁ በተቃራኒ አብዝቶ መብላትና ራስን አለመግዛት ደግሞ አእምሯችን የጠፋ ሥጋችን የወፈረ ውስጣችን በእግረ ብረት የተጠፈረ በዚህ ሁሉ ተከበን እጅግ በከፉ ምግባራት የተያዝን የዘለዓለማዊ ሕይወታችን ጠላቶች ሆነን እንድንጓዝ ያደርጉናል፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! መብልንና ራስን አለመግዛት ተከትለው የሚመጡትን ኃጣውእ በማወቅ ከድኅነታችን ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ቸልተኞች አንሁን፡፡"

( ኦሪት ዘፍጥረት - በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)
1.4K viewsBereket, 02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 05:14:19 "ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጾም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጾም ጾምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፥21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጾምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡

ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም
1.1K viewsBereket, 02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 05:14:19 "እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
1.1K viewsBereket, 02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 05:13:21 ሕዝቡ {በርባን ይፈታልን ክርስቶስ ግን ይሰቀል }ማለታቸውን ስንሰማ ሁላችንም ማዘናችንና <ምን አይነት ክፉዎች ናቸው }ብለን መውቀሳችን አይቀርም ። ወዳጄ ሆይ እባክህን እሰኪ አይሁድንና ጲላጦስን ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያ ትምህርትቤት መምህር የነበረው ሊቅ <<በስጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈቶ ክርስቶስን አሰረው ።መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈቶ በርባንን አስሮታ ልይላል ።}} ወዳጄ ሆይ አንተ በሰውነትህ ላይ ፈተህ የለቀከው ማንን ነው ?በርባንን ነው ወይስ ጌታን ነው ?በርባንን ፈተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሃ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው ።<በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው >ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግ ና እጅህን መታጠብ አይበጅህም ። ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈተኽ በርባን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል ።!
{የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ስጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉት }}ተብሎ ተጽፏልና (ገላ 5፥24)

ምንጭ:- ሕማማት
1.2K viewsBereket, 02:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-11 13:06:52 እርስዎ ስለምን ይጨነቃሉ?


መሴ___ እግዚአብሔር እሥራኤልን እንዲምርለት ነበር። .... ዘፃ 32፥11-12

ዳዊትም___ የእግዚአብሔር የቃልኪዳኑ ታቦት በድንኳኑ ስለተቀመጡ። ....መዝ 131፥3-5

ኢያሱ___ እሥራኤልን በጠላት ፊት ስለመሸነፋቸው ነበር። ኢያ 7፥6-9

ሳሙኤል__ ስለ ታቦተ ጽዮን መማረክ ነበር። 1ኛ ሳሙ 4፥13

ኤርሚያስ__ በጠላት ስለተማረኩ ስለወገኖቹ እሥራኤል ነበር።
ሰቆ ኤር 1፥20

ነሕምያ__ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ መበዝበዝ ነበር።
ነህ 1፥4

ቅዱስ ጳውሎስም___ስለ አብያተ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ነበር።
2ኛ ቆሮ 11፥28
1.8K viewsBereket, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 12:08:12 #ፆመ_ነብያት ወይም #የገና ፆም #ዕሮብ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 ይፈታል //
#ሼርርርርርርር


ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።
=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።
#ፆመ_ድህነት

የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።
#ፆመ_ማርያም

የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።
#ፆመ_አዳም

የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡
#ፆመ_ፊሊጶስ

የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#ፆመ_ስብከት

የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡

ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።

ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል
ወለመስቀሉ_ክቡር
6.9K viewsBereket, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 22:10:27
በድንግል ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት Join የምትለውን ብቻ ይንኳት።
1.4K views| ፼ ωΑνЄ |, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ