Get Mystery Box with random crypto!

የብልጽግና ወንጌል ቀጣይ ሁለተኛ ክፍል ➥የብልጽግና ወንጌልና ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ስርገት ሕወ | ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

የብልጽግና ወንጌል ቀጣይ ሁለተኛ ክፍል

➥የብልጽግና ወንጌልና ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ስርገት

ሕወሓት ለፕሮቴስታንቶች ቀና አመለካከት ነበረው። ሕወሓት መሀል ሀገር ውስጥ ባይተዋር በነበረበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ከፕሮቴስታንቶች ውጭ የተማረና የከተማ ሰው አያምንም ነበር። በሕዋሃት ባለሥልጣናት ዘንድ "ፕሮቴስታንቶች እንደ ትግራይ ሕዝብ በደርግ ተጨቁነዋል ብናቀርባቸው ይጠቅሙናል፤ ለሥልጣናችን ስጋት አደሉም" የሚል አመለካክት ነበር። በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችም ዘንድም "ሕወሓት የእምነት ነጻነት እንዲከበር አድርጎልናል" የሚል ዕሳቤ ስለነበራቸው ለሕውሓት ቀና አመለካክት ነበራቸው። ብዙ የተማሩና በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ኢሕአዴግን ተቀላቅለው ሕውሓትን መሀል ሃገሩን አላምደዋል።

የብልጽግና ወንጌል ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በደምብ ታስቦበትና በተጠና መልኩ እንዲገባ ያደረጉት ሁለት #ከአሜሪካን ሀገር የመጡ ፓስተሮች ናቸው። በፈረንጆች አቆጣጠር 2001 ዓ/ም ጀምሮ ነው ፓስተር #ባደግ በቀለ ከካሊፎርንያ ግዛት፤ ፓስተር #ገመችስ ደስታ ከአተላንታ ጆርጂያ የተለያዩ ፕሮጄክቶችን በመቅረጽ የኢሕአዴግን ጽ/ቤት ማንኳኳት የጀመሩት። በወቅቱ የነበሩ ባለሥልጣናትም ሁለቱ ፓስተሮች ይዘዋቸው ለመጡት ፕሮጄክቶች አረንጓዴ መብራት በማብራት ረድተዋቸዋል።

ፓስተር ባደግ በቀለ በካሊፎርንያ ግዛት ለረጂም ዓመት የኖሩና ቅዱስ ኢማኑኤል የሚባል የብልጽግና ወንጌል ማስተማሪያ ቤተክርስትያን ባለቤት ሲሆኑ የዶክትሬት ዲግሪያቸውንም የሠሩት እዛው ካሊፎርንያ ውስጥ የሚገኘው የብልጽግና ወንጌላውያን ዩንቨርሲቲ የሆነው አዙሳ ፓስፊክ (Azusa Pacific) የተባለ ተቋም ውስጥ ነው። ፓስተር ባደግ በአሁኑ ወቅት የዳሎል ኦይል፣ ስድስት ኪሎ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዮት፣ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ዓለም ጤና የሚገኘው የፕሮፌሰር ባደግ በቀለ አካዳሚ ባለቤት እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ባንኮችና ኩባያወች ባለድርሻ ናቸው።

ፓስተር ባደግና አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ "የኢትዮጵያ ፕሮጄክት" የሚል ፕሮግራም ቀርጸው በወቅቱ ሁለተኛ ዲግሪ ለመያዝ የማይቆፍሩት ድንጋይ ያልነበረውን የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በሥራ አመራር የሁለተኛ ዲግሪ ለማሠልጠን ፍቃድ ያገኛሉ። ስድስት ኪሎ የኦሮሚያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት መሬት ተስጥቷቸው ትልቅ ሕንፃ ገንብተው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናትን #የመጀመሪያ_ዲግሪ ያላችውንም #የሌላችውንም በሥራ አመራር ዘርፍ በማስተርስ ፕሮግራም ማሠልጠን ይጀምራሉ። ሥልጠናው የሚሠጠው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆንም ዲግሪውን የሚሠጠው አሜሪካን ሀገር ውስጥ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከጠ/ሚ #መለስ_በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአንድ ወቅት የፓስተር ባደግና አዙሳ ፓስፊክ ተማሪወች ሁነው ነበር። ለምሳሌ ያክል የቀድሞው ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን፣ መከላከያ ሚ/ር ለማ መገርሳ፤ የብልጽና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው ዓለሙ ስሜ፤ የቀድሞው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚ/ር ድኤታ ኤርምያስ ለገሰ፣ እንዲሁም ኢሕአዴግ ሹመት ሲሰጥ የትምህርት ዝግጂት በሥራ አመራር ሁለትኛ ዲግሪ የሚባልላቸው ቁጥራችው በጣም በርካታ ካድሬወች የፓስተር ባደግ ት/ቤት ምሩቃን ናቸው።

ፓስተር ባደግና አሱዛ ፓስፊክ ዩኒቭርሲቲ እነዚህን ሁሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት 'በክርስቲያን' ሥራ አመራርና ሐብት ፈጠራ ዘርፍ የማሠልጠን ዕድሉን ያገኛሉ.። እነዚህ የፓስተር ባደግ ተማሪ ባለሥልጣናት ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ሥልጣኑን የተቆጣጠሩት የሕወሃት ሰዎች ዐሳብ ለማፍለቅ ሲቸገሩ፣ የድርጅቱን ካድሬውች ሰብስበው የሚመሩበት መሪ ዐሳብ ሲጠፋ ከፍትኛ የሆነ ውዥንብር ሲመጣ፣ #የፓስተር_ባደግ_ተማሪዎች የሆኑት እነ ኃ/ማርያም፣ ደመቀ፣ ዓለምነው፤ አርከበ፤ ዓለሙ፣ ገዱ፤ ለማ፣ ዓብይ የድርጅቱ #ዐሳብ_አፍላቂውች ሆኑ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ግብርና መር ኢኮኖሚ፣ ገበሬው ነው ማኅበራዊ መሠረታችን የሚሉ አይነኬ ዐሳቦች የሀገሪቱን የፖለቲካ ሙቀት ተከትሎ ኢሕአዴግ ውስጥ አከራካሪ ዐሳቦች ሆኑ። “We have produced more than 30 mayors, Deputy Prime Ministers, 15 ministers and state ministers in Ethiopia.” ይላል የፓስተር ባደግ በባለቤትንት የሚመሩት ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዮት አካዳሚ ድረ ገጽ። እንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከ መኖሩም የማያውቀው አንድ ሃይማኖታዊ ተቋም 1 ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 2 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ፣ 15 ሚኒስትሮችንና 30 ከንቲባወችን ና በርካታ ጄኔራሎችን በክርስቲያን ሥራ አመራር ዘርፍ አስተምሮ አስመርቋል።

ሁለተኛው የብልጽግና ወንጌል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የበላይ ዐሳብ ሆኖ እንዲወጣ ትልቅ ሥራ የሠሩት ከአትላንታ ጆርጂያ የመጡት ፓስተር ገመቺስ ደስታ ቡባ ናቸው። #ፓስተር ገመቺስ #ሊድስታር ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪስ (Lead star International Ministries) የተባለ በተለያዩ የብልጽግና ወንጌል ማስፋፍያ ዘርፎች ላይ የተሰማራ ተቋምን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ። ሊድስታር ዋን ሚኒስትሪ ትሪ ፍሮንትየርስ (One Ministry Three Frontiers) በሚል መሪ ቃል ስር የብልጽግና ወንጌል በተለየዩ ቋንቋዎች የሚሰበኩባችው በርካታ "ቤተክርስትያኖችን"፣ የቴሌቪዝንና ሬድዮ ጣቢያወችን እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ያሉት ትልቅ ተቋም ነው። ለመጥቀስ ያክል #LTV የተባለው ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያና ሊድስታር ኮሌጂ በፓስተር ገመችስ ባለለቤትነት የተያዙ ናቸው።

ፓስተር ገመቺስ #የዓለም አቀፍ የኦሮሞ ቤተክርስትያኖች ኅብረት (Worldwide Union of Oromo Churches) #ፕሬዘዳንትም ናቸው። ለኦሮሞ ፖለቲካ ባላችው ቅርበት ምክንያት ከብዙ የኦሕዴድ ባለሥልጣናት ጋር ቅርበትና ጓደኝነት ለመፍጠር የቻሉ ሲሆን #ከጠ/ሚ_ዐቢይ አሕመድ፣ #ለማ_መገርሳና #ሽመልስ_አብዲሳ ጋር ስላላቸው ቅርብ ጓደኝነትና የፖለቲካ አማካሪነት ሚና በኤል ቲቪ (LTV) አቅራቢዋ ቤቲ ታፈሰ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ማብራራታቸው አይዘነጋም። #የኦሕዴድ_ከፍተኛ_ባለሥልጣናት ሁሉም ማለት ይቻላል #ፓስተር_ገመቺስ_ደስታና_የሪፍት_ቫሊ_ዩንቨርሲቲ_ባለቤት_የሆኑት_አቶ_ድንቁ_ደያሳ የፈጠሩት #የሃይማኖትና_የጥቅም ትስስር (ኔትወርክ) አባላት ናቸው። ይህ የሃይማኖትና የጥቅም ትስስር ሙስሊም ኦሮሞወችን ያገለለ በመሆኑ የኦሮሞን ፖለቲካ ለሁለት እንዲሰነጠቅ በማድረጉ የኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ በባሰ ሰላም የራቀው አካባቢ እንዲሆን አድርጎታል።

እነዚህ ከላይ የጠቀሱት የፓስተር ባደግና የፓስተር ገመቺስ የሃይማኖትና የጥቅም ትስስሮች በጣም ጠንካራ የሆነ የውጭ የሃይማኖትና የፖለቲካ አካላት ድጋፍ ያላቸው ሲሆን በዚህ ጽሁፍ ከተጠቀሱትና በስማቸው ከተመዘገቡት ተቋማት በተጨማሪ የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት ሁነው እንደተመዘገቡት አቶ ገምሹ በየነ ዓይነት ሰዎች ስም የተመዘገቡ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ኔትወርክ ነው።

የብልጽግና ወንጌል የመጀመሪያው ክፍል t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia/568

https://t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia