Get Mystery Box with random crypto!

የብልጽግና ወንጌል የመጨረሻ ክፍል። ➥ የብልጽና ወንጌል አብዮታዊ ዲሞክራሲን አንዴት ተካው? ለ | ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

የብልጽግና ወንጌል የመጨረሻ ክፍል።

➥ የብልጽና ወንጌል አብዮታዊ ዲሞክራሲን አንዴት ተካው?

ለሕወሓት የሥልጣን ዘመን ማብቃት ምክኒያት ስለሆኑ ሁኔታዎች የተለያዩ ዐሳቦች ቢሰነዘሩ ብዙም አይገርምም። ምክንያቱም ሕወሓት ከሥልጣን የወረደበት አንድ ሚሊዮን የተለያዩ ምክንያቶች ስላሉ። ነገር ግን ሕወሓት ኢሕአዴግ ውስጥ የነበረው የሀሳብ (የሥልጣን ወይም የጉልበት ማለት አደለም) የበላይነት እየተሸረሽረ የሄደው አቶ መለስን በሞት አቶ በረከትን ደግሞ በሕውሓት ሰወች ሥልጣናችን ይወስድብናል ፍርሃት ካጣ በኋላ ነው። ይህ በኢሕኣዴግ ውስጥ የነበረ የዐሳብ የበላይነት ማጣት መሬት ወርዶ ከተለያዩ በጣም ብዙ ውጫዊና ውስጣዊ ምክያቶች ጋር ተዳምሮ ወደ ሥልጣን ማጣት ተቀይሯል።

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጥርት ያለ መርህ ያለው ነገሮችን በግልጽ ለመተንትን የሚያስችል የተስናሰለና በአግባቡ የተሰነደ ርዕዮተ አለም ባይሆንም መምህሩ የነበሩት አቶ መለስና ደቀ መዝሙርቶቻችው እንደ ዳዊት የሚደግሟችው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዐሳቦች የያዘ ያላለቀ ነገር ግን ካድሬ ለማሠልጠን የሚይስችል ማንዋል ነበር ማለት ይቻለል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማኅበራዊ መሠረት የሚለው መድብ (ገበሬው)ና ቡድኖች (ጭቁን ብሔሮች) እንደነበሩት ሁሉ ጠላት መደብና ጠላት ብሔር ማን እንደሆነ ለይቶ የሚያውቅ፤ ማኅበራዊ መሠረት የሚላቸው ቡድኖችን ጥቅም የሚያስከብር፤ ጠላቴ የሚለውን ብሔርና ሃይማኖት ደግሞ ሕልውና የሚያጠፋ ሕገ ምንግሥት፣ ፖሊሲ፣ አዋጅ፣ ደምብና መመሪያ የነበረው የፖለቲካ አስተሳሰብ ነው።

እነ አቶ መለስና አቶ በረከት ካድሬወቻቸውን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚያጠምቁበት ዘመን ለሥልጣናችን አያሰጉነም እናምናቸዋለን ያሏቸውን እነ ፓስተር ባደግና ፓስተር ገመቺስ ቀን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲጋቱ የሚውሉትን የደኢሕዴንና የኦሕዴድ ባለሥልጣናትን ማታ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ውስጥ የብአዴን ካድሬወችን ደግሞ ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስትዩት ውስጥ የብልጽግና ወንጌል፣ አውንታ ሃሳቢነት፣ አነቃቂ ንግግር፣ የብልጽግና ወንጌል ሥራ አመራር ጥበብ፣ ወዘተ ያስተምሩ ነበር።

አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ የተለያዩ የጥቅም ኔትውርኮች እንደ አሽን ሲፈሉ የፓስተር ባደግና የፓስተር ገመቺስ የማታ ትምህርት ተማሪዎችም የራሳችውን ጠንካራ ኔትውርኮች #ከሕውሓት ኔትውርኮች በተጓዳኝ መስርተዋል። በሥልጣንና በገንዘብ ያበዱት የሕውሓት ባለሥልጣናትም እርስ በርስ በሚያድርጉት የዐሳብም ሆን የሥልጣን መገፋፋት ትግል ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ የፓስተር ባደግንና የፓስተር ገመቺስን ስዎች በዐሳብ አመንጪነት ደረጃ እንዲሳተፉ አድርገዋል። ይህ ተሳትፎ ከተላላኪነት ያለፈ ሚና ላልነበራቸው ስዎች የሞራል ስንቅ ሰጠ፤ የሕውሓት ስዎችን ኢሕአዴግ ውስጥ መሞገት እንደሚቻል አሳየ። ከጊዜ በኋላም የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ የመወሰን የተሻለ ሚና ይገባናል ብሎ ደፈር ብሎ ወደ መጠየቅ እየተሽጋገረ ሂዷል።

በአማራ ክልልና ኦሮሚያ ውስጥ ባሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ አንቂወች በመታገዝ አገዛዙን ሲቃወሙ ብአዴንና ኦሕዴድ ካድሬዎች እሳት ከማጥፋት ይልቅ አይዟችሁ እያሉ ነዳጅ ወደ ማቀበል ተሽጋገሩ። #የአብዮታዊ_ዲሞክራሲ አንዱ ትርክት ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥር አብላጫ ያላቸው ሁለት ብሔሮች ግንኙነት "የጨቋኝና የተጨቋኝ ነው፤ እነዚህ ሁለት ቡድኖች ፍላጎቶቻቸው መቸም አይታረቁም፤ አብረው ሊሠሩ አይችሉም፤ የነዚህ ሁለት ብሔሮች ፉክክር እንደ ትግራይ ላሉ በቁጥር አናናሳ ብሔሮች ሲሳይ ነው" የሚል ነው። ነገር ግን ሕወሓት " #አምናቸዋለሁ፤ ለሥልጣኔ ስጋት አይደሉም" ብሎ ነገሮችን አልጋባልጋ ያደረገላችው ፓስተሮች ለዓመታት የብልጽግና ወንጌል ቤተክርስትያን ውስጥና ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት ውስጥ ያስተማሯችውን የኦህዴድና የብአዴን ካድሬውችን በማስተባበር #የአሜሪካንና_የአውሮፓ_ኅብረትን ቡራኬ በመቀብል ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝን ያለ ሕውሓት ፍቃድ ሥልጣን እንዲለቁ በማድረግ፣ ዐቢይ አሕመድን በማንገሥ፤ ሕዋሓትን ከአራት ኪሎ እንዲባረር አድርገዋል።

የብልጽግና ወንጌል አቀንቃኞች ሥልጣን ከመያዝ ባለፈ የብልጽና ወንጌል ለኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሔ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የብልጽግና ወንጌል መሠረታዊያን የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዴት ሊፈቱ እንደሚችሉ የሚያሳየው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደተጻፈ የሚነገረው መደመር የተሰኘ ዓለማዊ መጽሐፍ በሚሊዮን በሚቆጠር ቅጅ ታትሞ እንዲሰራጭ ተደርጓል። ገዥው ፓርቲም ስሙን በአደባባይ ወደ #ብልጽግና_ፓርቲ ቀይሯል።

አሁን ብዙ ወገኖች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የታወጀው እልቂት ስሜታዊ በሆኑና ማሰብ በማይችሉ ወጣቶች የተደረገ እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ። ይህ ሞኝነት ነው !
ቀድሞ በሕወሓት "ኦርቶዶክስና አማራን ማጥፋት" ተብሎ በሰነድ የተዘጋጀ አሁንም በብልፅግና ፓርቲ " #ሀብት_ማፍራትን_እንደ_ኃጢአት_የሚቆጥር_ሃይማኖት_ባለበት_ሀገር_ውስጥ_ብልፅግናን_ማስፈን_ፈታኝ_ነው " ተብሎ# በኦርቶዶክሳውያን ላይ መንግሥታዊ የግድያና የማጥፋት አዋጅ ከታወጀ ቆይቷል።

ከዚህ በታች ካያያዝኩት ሰነድ አንደኛው ብልፅግና ፓርቲ በ2012 ዓ/ም ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተዘጋጀ ሥልጠና ላይ የቀረበ ማሠልጠኛ ሰነድ ሲሆን በዚህ መንግሥታዊ ሰነድ ላይ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ለብልፅግና የማትመች የለውጥ ጎታች ተደርጋ ተስላለች።

ኦርቶዶክስንና ጠላት ብለው የፈረጁትን "ነፍጠኛ" ከኢትዮጵያ ምድር የማስወገዱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ኦርቶዶክስን የማጥፋት ሥራ በመንግሥታዊ መዋቅር በቅንጅት እየተሠራ ባለበት ሁኔታ መንግሥትን ደጅ መጽናት ሞኝነት ነው። አድዋ ላይ ድል የመታናቸው ጠላቶቻችን በኢትዮጵያዊያንን የቆዳ ቀለም ተሸፍነውና የሃይማኖት ካባ ለብሰው እንደ እባብ አፈር ልሰው ተነሥተዋል። አሁን ተደራጅተህና ወገብህን ታጥቀህ ጠላቶችህን ድባቅ ለመምታት መነሣቱ ብቻ መፍትሔ ነው።

በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያን ከሌቦች ለመታደግ እንነሣ!

ምንጭ፦ MikaelZethiop

ክፍል ፩ https://t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia/568
ክፍል ፪ https://t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia/570

https://t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia