Get Mystery Box with random crypto!

#የብልጽግና ወንጌል በኢትዮጵያ ➽ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ ጥብቅ መረጃ! 'ሴረኛው | ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

#የብልጽግና ወንጌል በኢትዮጵያ
➽ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ ጥብቅ መረጃ!

"ሴረኛው ፓስተር ባደግ ኃ/ማርያም ደሳለኝን፣ ደመቀ መኮነንን፣ ዓለምነው መኮነን፤ አርከበ ቁባይን፤ ዓለሙ ስሜን፣ ገዱ አንዳርጋቸውን፤ ለማ መገርሳንና በርካታ ጄነራሎችን እንዴት 'በክርስቲያን' ሥራ አመራርና ሐብት ፈጠራ ዘርፍ ዲግሪ ሠጣቸው?"

#አብይ_አሕመድ ወደ ሥልጣን እንደመጡ #መደመር እና #ብልጽግና በተባሉ ቃላት ሲያደነቁሩን መሰንበታቸው አይዘነጋም። እነዚህ ቃላት በየሚዲያው እስኪሰለቸን ከመነገራቸውም አልፈው፤ "መደመር" የተሰኘ መጽሐፍ በዐቢይ አሕመድ ተጽፎ የፓርቲ ደጋፊዎች ተገደው እንዲሸጡና እንዲገዙ ተደረገ። "ብልጽግና" የሚል ፓርቲ ደግሞ በየክልልና ሀገር አቀፍ ደረጃ ተመሠረተ። የነዚህ ሁለት ቃላት ምንጭ ግን ምን ይሆን? ዐቢይ አሕመድ የተባሉት የቀድሞው የስለላ ድርጅት ባልደረባ፤ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁለቱን ቃላት ከየት እንዳመጡት መረዳት አሁን ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን ለመረዳት ያግዛል።

ይህንን በሚመለከት "ድራዛ አበበ" የተባለ ሰው ረዘም ያለ ጽሑፍ ያስነብበናል። እኔም ጥቂት ማሻሻያዎችን ጨምሬበት ገለጻውን እንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ።

#ብልጽግና (prosperity) እና #መደመር (synergy) ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አደንቋሪ ቃላት (buzzwords) ቢሆኑም ዓለም ላይ የቴሌቪዥን ጥምቀት (televangelism) ከተስፋፋበት ከ1980ወቹ ጀምሮ ከቴሌቪዥን ጠማቂወች (televangelists) አፍ የማይወጡ ቃላት ናቸው። አብዛኛወቹ ዝነኛ የቴሌቪዥን ጠማቂዎች #የብልጽግና_ወንጌል በሚባል አስተምህሮ የሚያምኑ ፕሮቴስታንቶች ናቸው።

➥የብልጽና ወንጌል ምንድን ነው?

የብልጽና ወንጌል የሚባለው አስትምህሮ አንዳንዴ የጤናና የሃብት ወንጌል፤ አንድንዴ ደግሞ የመሳካት ወንጌል በመባል ይታወቃል። አስትምህሮው በአጭሩ የካቶሊክ፣ የኦርቶዶክስ እና ነባር የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖቸ ከሚያምኑብት የማቴውስ ዎንጌል 19፡24 “ባለጸጎች መንግሥተ ሰማያትን ከሚወርሱ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል /it is easier for a camel to go through the eye of a needle than for someone who is rich to enter the kingdom of God” ከሚለው እና ክርስትናን የድሆች፣ የተበደሉ፣ የተጨቆኑ፣ የተራቡ እና የታረዙ ሰዎች ተስፋነት በተቃራኒው እግዚአብሔር ባለጸጋ እንድንሆን፤ ገንዘብ እንድናክማች፤ ነግደን አንድናተርፍ፤ ጥሩ አንድንበላ፤ ጥሩ አንድንለብስ ይፈልጋል ወደሚል አስተምህሮ የሚለውጥ ነው። "የአግዚአብሔርን መንግሥት የሚወርሱት ድሆቸ፣ ምስኪኖች፣ ኀዘንትኞች፣ ደካሞች እና ያልተሳካላቸው ሳይሆኑ ባለጸጋወች፣ ብርቱወች፣ አነቃቂ ንግግር አዋቂወች፣ አውንታ ዐሳቢወች (positive thinkers) እና ኑሮ የሰመረላቸው ናቸው" የሚል ነው።

➥ባለጸጋወቹ የብልጽና ወንጌል ፓስተሮች

ባለጸጋነትን የሚያወድስውን 'ክርስትና' ለድሆች በመስበክ አንዲሁም አንድ ቀን የማርቆስ ወንጌል ትምቢት ይፈጸምልኛል ከሚሉ ምስኪኖች በሚሊዮን ዶላሮች በመሰብስብ የግል ቦይንግ አውሮፕላን የገዙ የብልጽግና ፓስተሮች በጣም ብዙ ናቸው። የብልጽግና ወንጌልም እነዚህን የሃይማኖት አባቶች ይሄን ያክል ገንዘብ ማከማችት እንደ ጽድቅ ሥራ እንጂ ከአንድ 'ክርስቲያን አባት' እንደማይጠበቅ ያልተገባ ተግባር አይቆጥረውም። ለአብንት እስኪ የሚቀጥሉትን ሦስት ባለጸጋ የብልጽግና ፓስተሮች ሐብት እንመልክት፦
1. ኬን ካፕላንድ/Kenneth Copeland፡ 760 ሚሊዪን ዶላር
2. ቲዲ ጄክስ/TD Jakes፡ 200 ሚሊዮን ዶላር
3. ዴቪድ ኦየዲፖ/ David Oyedepo: 150 ሚሊዮን ዶላር

የብልጽና ወንጌል እና የቴሌቪዥን ጥምቀት (televangelism) በኢትዮጵያ

#ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መካነ እየሱስ፤ መሠረተ ክርስቶስ፣ ቃለ ሕይወትና ሙሉ ወንጌል የመሳሰሉት ነባሮቹ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያኖች የተከታዮቻችው ቁጥርና የገቢ ዐቅማቸው እየቀነሰ ሲሄድ ራሳቸውን ሐዋሪያና ነብይ ብለው የሚጠሩ የብልጽግና ወንጌል ፓስትሮች ግን የተከታዮቻቸው ቁጥር በሚሊዮኖቸ እይጨመረ ሄዷል። እንደ ዮናታን አክሊሉ፣ እዩ ጩፋ፣ እስራኤል ዳንሳ፣ ታምራት ታረቀኝና ብርቱካን ጣሰው የመሳስሉት የብልጽግና ፓስተሮች ትልልቅ ስብሰባወችንና ቴሌቪዥንን በመጠቀም ለሚሊዮኖች ታምር እንሠራለን፣ ከእግዚአብሔር ጋር እናገናኛለን፣ ክህመማችሁ እንፈውሳለን፣ ብልጽግናና ጸጋ እናስገኛለን እያሉ በነጻንት ይሰብካሉ። ግብር የማይከፈልበት በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያለ ከልካይ ይሰበስባሉ። የኛ ሀገር ኬን ካፕላንድ የሆኑት እስራኤል ዳንሳና ዮናታን አክሊሉ ለባለጸጋ ፓስተርነት ስኬት የበቁት ከመሬት ተነስተው ሳይሆን ለዓመታት ከነሱ የተሻለ የትምህርት ዝግጂትና ከውጭው ዓለም ጋር ጥብቅ ቁርኝት ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በተሠራ የረጅም ዓመታት ሥራ ነው። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፓስተር ዮናታን 20 ሺህ ዮሮ ጳጉሜ 1፣ 2011 ዓ/ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ "መልካም ወጣቶች" የተሰኘ ሃይማኖታዊ ፕሮግራም ላይ ሲያበረክቱ ገንዘቡን ከየት አመጡት? ለምን ይሄን ያክል ገንዘብ ለአንድ 'የሃይማኖት አባት' ሰጡ ብሎ የጠየቀው ሰው ትንሽ ነው።

ቀጣይ ተከታታይ ክፍሎች በሰፊው ➥#የብልጽግና ወንጌልና ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ስርገት በሚል ጠለቅ ያለ ትንታኔ ስለሚኖረን ይህን ቻናል ይከታተሉ። @Tinsae_Ze_Ethiopia


ጸሎተ ለማርያም ወስእለታ ወአድኅነነ እመዓተ ወልዳ
ጸሎተ ለማርያም ወስእለታ ለህዝበ ክርስትያን እመዓተ ወልዳ
ጸሎተ ለማርያም ወስእለታ ለሀገሪትነ ኢትዮዽያ እመዓተ ወልዳ

ቅድመ ኢትዮጵያ ትንሳዔ
ስለሳልሳዊ ቴዎድሮስ
የኢሉሚናቲ ሴራዎችን ማጋለጥ
ህዝበ ክርስቲያንን ማንቃት

https://t.me/Tinsae_Ze_Ethiopia