Get Mystery Box with random crypto!

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆ | ትምህርት ሚኒስቴር

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ
....................................................
ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም .(የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መውጫ ፈተናው ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው የሙያ ዘርፎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ፡፡

የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መውጫ ፈተናውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ መውጫ ፈተና ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የሚጠቀሙባቸውን እውቀት ክህሎትና አመለካከት በብቃት መያዛቸውን መለኪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት አሰጣጥ ላይ ያሉበትን ሁኔታ በማሳየት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የመውጫ ፈተናውን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንና አስፈላጊውን ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎንም ተፈታኞችን በእውቀትና በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው የመውጫ ፈተና ውጤት ፍትሀዊነትን የሚመልስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው የሚሰጥባቸውን የትኩረት መስኮች በመለየት የማጠናከሪያ ፕሮግራም እየተሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ደርዛ ናቸው፡፡

ጎን ለጎንም ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ተኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ላይ መጽደቁ ይታወሳል፡፡



ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et

ይከታተሉ
---------