Get Mystery Box with random crypto!

በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ | ትምህርት ሚኒስቴር

በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
................................................................................

ሚያዝያ 3/2015(የትምህርት ሚኒስቴር)፦ በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ የሚጀመር መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የአዲስ ወግ “የመደመር ትውልድን መቅረጽ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ በተደረገው መድረክ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በሁሉም አካባቢዎች ምቹ የትምህርት ቤት ከባቢ መፍጠር፣ የትምህርት ቤት አመራር ሥልጠና፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ማሻሻል ከዋና ዋና ሥራዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከ47ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ ከእነዚህም መካከል አብዛኛዎቹ ተገቢውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተገነቡ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ሕብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ዘመቻ ለማከናወን ዕቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዘመቻውም በቅርቡ ይፋ ተደርጎ ወደ ተግባር እንደሚገባ ጠቅሰው የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቁ ማድረግ የሚያስችል ሥልጠና እንደሚከናወን ገልጸዋል።