Get Mystery Box with random crypto!

የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲያካትት ተደርጎ መዘጋጀት | ትምህርት ሚኒስቴር

የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲያካትት ተደርጎ መዘጋጀት አለበት
፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ
............................................
ሚያዚያ 03/2015 ዓ.ም.(የትምህርት ሚኒስቴር)፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በትናንትና ውሎው የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲያካትት ተደርጎ በጥንቃቄ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) እንዳሉት ረቂቅ አዋጁ የዩኒቨርሲቲዎችን አካዳሚክ ነፃነት የሚያጎናፅፍ ቢሆንም ከመንግሥትም ሆነ ከግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎች ላይ ቅሬታ እንዳይፈጥር የዩኒቨርሲቲዎችን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የኅብረተሰቡን ፍላጎትም ያካተቱ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡